Wednesday, January 28, 2009

በእሳት እና በፈላ ዉሃ እያቃጠሉ መረመሩኝ

የወያኔዎች ገበና ማሕደር
በእሳት እና በፈላ ዉሃ እያቃጠሉ መረመሩኝ

የህዝባዊ ሓርነት ትግራይ ሰለባ የሆኑት ከአቶ ገዛ ረዳ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ
ምንጭ ደጀን ራዲዮትርጉም ጌታቸዉ ረዳ
;“…በወቅቱ “ኢድዩ” ወደ አካባቢዉ በብዛት ሰራዊቱን ይዞ እየገሰገሰ በፍጥነት ስለመጣ በድንገት ስለደረሰባቸዉ ወያኔዎች ተደናገጡ። ኢዲዩ መጥቶብናል እና እንግደላቸዉ ብለዉ እኛን ለመግደል ወያኔዎቹ ሌሊትኑ ወደ ታሰርንበት ዳስ ክፍል ገቡ እና አስወጥተዉ በተራ አስሰለፉን።“አዛዉንቱ አቶ ገብረሊባኖስ መዝገቦም ሲመረምሩዋቸዉ ሰዉነታቸዉ በሞላ በእሳት እያቃጠሉ እየደበደቡ ስላደከሙዋቸዉ / መራመድ ስለማይችሉ ልንሸከማቸዉ አንችልም ብለዉ አቶ ገብረሊባኖስ መዝገቦን በእንቅልፋቸዉ ተኝተዉ እንዳሉ በሦስት ጥይት ገደሏቸዉ። የገዛ ታጋያቸዉም በሃይለኛ ወባ ተይዞ ተኝቶ ስለነበር አሱንም አንሸከመዉም ብለዉ በጥይት ገደሉት…።”    አቶ ገዛኢ ረዳ

አቶ ገብረሊባኖስ መዝገቦ የ አቶ ጌታቸዉ ረዳ አማች ናቸዉ።
ቃለ መጠይቁን ያዘጋጀዉ ዶክተር ሃይለማርያም አበበ ተርጉሞ ወደ ጽሁፍ መድረክ ያዘጋጀዉ ጌታቸዉ ረዳ

ደጀን ራዲዮ፦
ጤና ይስጥልኝ በመጀመርያ ሰላምታየን አቀርባለሁ አቶ ገዛኢ ረዳ። የደጀን ራዲዮ እንግዳ ሆነዉ በተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ የደረሰበዎት ግፍ በመላዉ ዓለም ለሚያዳምጡን የትግርኛ ፕሮግራም አድማጮች ለመግለጽ ፈቃደኛ ሆነዉ በመቅረብዎ በራዲዮ ጣቢያችን እና በደጀን ራዲዮ አድማጮች ስም አመሰግናለሁ።አቶ ገዛኢ ረዳ የትግራይ ተወላጅ ነዎት፡ በትግራይ ክፍለ ሃገር ዉስጥ ወያኔዎች ሲያዙዎት የመጨረሻዉ ስራዎ በምን ስራ ላይ ተሰማርተዉ ይኖሩ ነበር?

አቶ ገዛኢ ረዳ፦ ትዉልዴ የትግራይ ተወላጅ ነኝ።በመንግስት ስራ ገና በወጣትነቴ ጀምሬ ለብዙ ዓመታት በአገር አስተዳደር ጽ/ቤት ዉስጥ በልዩ ልዩ ክፍሎች ተመድቤ ሰርቻለሁ።መጨረሻ ወያኔዎች ሲይዙኝም በትግራይ ክፍለሃገር በአገር አስተዳደር ሚኒስቴር ሥር በሽሬ አዉራጃ በምኖርበት በዋናዉ ከተማዋ በእንዳስላሴ ከተማ በአዉራጃዉ አስተዳደር ጽ/ቤት ዉስጥ ነበር ስራየ።

ጥያቄ፦ ወያኔ ገና ወደ መንግስትነት ከመምጣቱ በፊት በረሃ ዉስጥ እንዳለ በጣም ክፉ ምርመራ እና የተለያዩ ስቃዮች በእርስዎ ላይ እንደፈጸሙበዎት ሰዎች ነግረዉኝ ነበር፡ ወያኔዎች ይሄነን በደል ለማድረስ ያነሳሳዉ ምክንያት ምንድነዉ? በደል ደረሰብኝ የሚሉት ምን ዓይነት ግፍ ነበር ተፈጽመዎበታል የሚባለዉ?

አቶ ገዛ ረዳ፦ በእርግጥ ወያኔ በእኔ ላይ መጥፎ ግፍ ፈጽሟል። ይህ በደል በእኔ ብቻ ሳይሆን በጣም ቁጥራቸዉ እጅግ ብዙ የሆኑ ታዳጊ ወጣቶችና ሽማግሌዎች ከኔ በላይ እጅግ የከፋ ግፍ የተፈጸመባቸዉ የትግራይ ተወላጆች ስላሉ የደረሰብኝ በደል በግፍ ተሰቃይተዉ ከተገደሉት ሰዎች ሲነጻጸር የሰዉ ልጅ የማይችለዉ በላየ ላይ ግፍ ቢፈጸምብኝም ተሰቃይቼ በተጨማሪ የጠየቁኝን ገንዘብ ከፍየ ሳልሞት በሕይወት ተርፌ የእኔ ታሪክ እና አብረዉኝ በግፍ ሲሰቃዩ ያየሗቸዉ ሰዎች ስቃያቸዉን እና ታሪካቸዉ ከራሴ ታሪክ ጋር አብሬ ለዓለም ሕዝብ ለመግለጽ ለታሪክ ምስክርነት በመብቃቴ አምላክ ምስጋና ይድረሰዉ እላለሁ። የደረሰባቸዉ በደል ለሕዝብ ሳይገልጹ ያለፍርድ በግፍ የተገደሉት ሰዎች ዛሬ በሕይወት ከእኛዉ ጋር ባለመኖራቸዉ ግን በጣም ያሳዝናል።

ጥያቄ፦
የተያዙበት ምክንያት መነሻ ቢያብራሩልኝ እና የትስ ነዉ ወያኔዎች አርስዎን አግኝተዉ ሊይዝዎት የበቁት?

አቶ ገዛኢ፦
መጀመሪያ ደርግ ወደ ስልጣን ሲወጣ፤ እኔ እና ስማቸዉ አሁን ልጠቅስ ያልፈለግኳቸዉ ጓደኞቼ ሆነን ደርግን ለመጣል በምስጢር ተነጋግረን ተደራጅተን ነበር።በከተማዉ ዉስጥ በወቅቱ የወያኔ አባላትም ይንቀሳቀሱ ነበር። እኛ የራሳችን እነሱ ደግሞ የራሳቸዉ እንቅስቀሴ በማድረግ የየግላችን በማካሄድ ጸረ ደርግ እንቅስቃሴ እናካሂድ ነበር። እኛ በወቅቱ ወያኔዎች ወደ በረሃ ከመዉጣታቸዉ በፊት አድያቦ በሚባል በረሃ ታጋዮቻችን አሰማርተን ትግል ጀምረናል። ኢድዩ ከመባላችን በፊት የድርጅታችን መጠሪያ “ጠራናፊት” ነበር የሚባለዉ።ጠራናፊት በሗላ ቆይቶ ወደ ኢዲዩ ተቀላቅሎ ‘አዲዩ’ ተባለ። ይህንን ትግል ወያኔዎች በረሃ ከወጡ በሗላ የጠራናፊት እንቅስቃሴ እንዳለ እና አባሎች መሆናችንን አዉቀዋል።እንግዲህ እየወነጀሉን ያሉት እናንተ ከከተማ ወጣቶችን እየመለመላችሁ ወደ ጠራናፊት ትልካላችሁ በሚል ነዉ እንዲይዙን መነሻ የሆናቸዉ። በእርግጥ በወቅቱ እኛ ደርግ አልነበርንም፡ጸረ ደርግ ሆነን ተደራጅተናል።በእርግጥ ተንቀሳቅሰናል “መብታችን” ነዉ። ይህ በመሆኑ በወያኔ መጠየቅ አልነበረብንም።በእነሱ ዉንጀላ ጠራናፊትን ማደራጀት “ጸረ ወያኔነት” ስለሆነ ጸረ-ወያኔ ነህ ብለዉ ነዉ የያዙኝ። ጥያቄ፡- በጠራናፊትም ሆነ በማንኛዉም ድርጅት መደራጀት የናንተ የግለሰዎች የምርጫ መብት ነዉ፡ ለምን አስከዚህ ድረስ ሊገፉበት አነሳሳቸዉ?

አቶ ገዛኢ ረዳ፡- እንቅስቀሴዉ በጣም አስግቷቸዉ ነበር።ተሓህቶች ሕዝቡን መቅጣት፤ ማስፈራራት፤ መግደል እና ማሰቃየት ስለጀመሩ በተናጠል ገበሬዉንም እያስገደዱ ማታገላቸዉን ስላየ፤ ኗሪዉ ሕዝብ ወደ ጠራናፊት እየሸሸ የመደራጀት ፍላጎቱ እየበረታ መሄዱን ስላስተዋሉ የጠራናፊት አባሎች መሆናችን ስላወቁ፤ እኛኑን ለመያዝ መነሻቸዉ ይሄ ነዉ እንጂ ሌላ ምንም ወንጀል በእነሱ የፈጸምኩት ነገር የለም። ኢድዩ ሃገራዊ ነዉ። ባሕሉን ሃይማኖቱን ጠብቆ ሕዝቡን መስሎ የሚጓዝ ድርጅት ስለነበር እነሱ አልወደዱትም። እና ሊይዙኝ የቻሉት በዚህ ነዉ።

ጥያቄ፡- የት ነዉ ሊይዝዎት የቻሉት?

አቶ ገዛኢ፦
ዕለት 20 በሕዳር 1969 ዓ.ም ከሰዓት በሗላ አብቶባስ ተሳፍረን በማግሰቱ 21 የዓመቱ የአክሱም “ሕዳር-ጽዮን” በዓል የሚከበርበት ዕለት ስለነበር ከሽሬ/እንዳስላሴ ከተማ እኔ እና ጓደኞቼ ሆነን ወደ አከሱም ከተማ ስንጓዝ “ላዕላይ ቆራሮ”- ዉስጥ “ማይ ጋሕጋሕ” በሚባል ቦታ በአዉራ ጎዳናዉ እመንገዱ ላይ አድፍጠዉ መሽገዉ ቆዩን። “ቁም!” በማለት ነጂዉን አዘዙት። እኔም ሾፌሩን “ዝምብለህ ቀጥል!! ቀጥል!!” እንዳልኩት ጉዞዉን ሊቀጥል ሲል “ቦምብ” ወርዉረዉ በጭስ አፍነዉ አስቆሙት። ታሳፋሪዉ በሙሉ እንዲወርድ አዘዙት። ወረድን።እኛን እመንገድ ዳር አስቀምጠዉ መንገዱን ዘጉት። 50 ከሚሆን ከታገተዉ ተሳፋሪ መሃል “እኔ” እንደዚሁም “ገብረጻድቅ ወልዱ” እና “ፍስሃ” የተባሉ ጓደኞቼን ሦስታችን ለይተዉ በማስቀረት ሌሎቹን ለቀቁዋቸዉ። ከቦታዉ ፈንተት አድርገዉ ትንሽ ወንዝ ያለበት ጣሻማ ወደ ሆነ ስፍራ በመከወል ለጊዜዉ እዛዉ ቁጭ በሉ አሉን። ጌዘዉ እየመሸ ሲሄድ “እባካችሁ አቡቶቡሷ ጥላን እንዳትሄድ ነገ በዓለማርያም “ሕዳር-ጽዮን” ነዉ እና ለመሳለም ነዉ አክሱም ስንሄድ ያስቆማችሁን እና ልቀቁን” ብልን ለመንናቸዉ። (እስከዚህ ጨካኞች መሆናቸዉን አላወቅንም። እባካችሁ አቡቶቡሱ ጥሎን እንዳይሄድ አልን እንጂ እኛ ይህ ሁሉ መካራ ይመጣብናል አላልንም ነበር)።ሲመሽ፤ አቡቶቡስዋም ጥላን ሄደች፡ እኛም ይዘዉን “ማይ ድማ” ወደ ሚባል ቦታ ወስደዉ ከብት እና ፍየል በሚኖርበት በረት “ነጭ-አመድ እና እበት” ያለበት በረት ዉስጥ አስገብተዉ “እዚህ ተኙ” ብለዉ እንደከብት በረቱን ዘጉብን እና አዳሩን እዛዉ አደርን።

ከእዛ በማግስቱ ጥዋት ሌሊት “ማይ ቡር” ወደ ሚባለዉ የማርያም ህዳር-ጽዮን በዓል ወደ ሚከበርበት ቤተክርስትያን ወሰዱን። ከዚያ ወደ ሰመማ ወሰዱን። ከሰመማ ወደ ዓዲ ዳዕሮ ወሰዱን። ከዓዲ ዳዕሮ ወደ ዓዲ ነብርኢድ ሄድን። ዓዲ ነብርኢድ ስንደርስ አቶ “ፍቕረ አርአያ” የተባለ ወጣት ገበሬ አስረዉ ከእኛ ጋር ጨመሩት። እንደዚያ እያልን ወደ “ባድመ” ደረስን። በእነዚህ ገጠሮች ስናለፍ አዳራችን ቤት ባልታጣ “ሆን ብለዉ” በብርድ እንድንሰቃይ እና እንድንታመም ብለዉ እከብቶች እና ፍየሎች በረት ነበር አጉረዉ እንድተኛ የሚያዝዙን። በደረስንባቸዉ ቦታዎች ሁሉ ወጣት ዋጣቱን እየያዙ ነበር እየለቀሙ የሚጓዙት። አስረዉ ሲያመጡዋቸዉ፤-ሁለቱን እጆቻቸዉ አጥብቀዉ ስለሚያስሯቸዉ፤ “ዓይኔ ሊፈነዳ ተቃርቧል! እጄ! ልቤ ሊፈነዳ ነዉ! ጣቴ ሊቆረጥ ነዉ!” “እባካችሁ ፍቱልኝ! ወይም ላላ አድረጉልኝ! ፤ልሞት ነዉ! ስለ ፈጠራችሁ አምላክ!” በማለት ይለምኗቸዋል። ለመታሰራቸዉ ምክንያት ደግሞ “ኢዲዩን ለመቀለቀል አቅዳሃል፡ የኢዲዩ አዝማሚያ ታሳያለህ…” እያሉ ናቸዉ የሚዩዝዋቸዉ። መጀመሪያ ከአፍ ጋህጋሕ ስንያዝ ሦስታችን ብቻ ነበርን።ቀስ በቀስ ወደ 30 እስከ 40 የምንሆን እስረኞች ደረስን። እነኚህ ከየቦታዉ የለቀሙዋቸዉ አብዛኛዎቹ ገላቸዉ በግርፋት የተላላጠ የተጎሳቆሉ አስረኞች ናቸዉ። ከባድመ ወደ “ጉንበት” ወደ ተባለዉ ስፍራ ወስደዉ አሳረፉን። እዛ ስንደርስ በጣም የሚያስፈራ የመቶ እና የሦስት መቶ ኣመት ያደረገ የሬሳ የመቃብር ክምር-ይታያል።ያስፈራል፤ይዘገንናል። ባድመ ስንደርስ መጀመሪያ ስንያዝ እንደነበረዉ ሁሉ አሁንም እንድንተኛበት ያዘዙን ስፍራ የነጭ አመድ ክምር ያለበት አስከ “የእግርህ-ባት” ድረስ የሚዉጥ አመድ ላይ “ተኙ” ብለዉን እዛዉ “ሳል” እያሳለን አደርን። ጥዋቱን ከምኝታችን ስነሳ ሁላችንም ፊታችን “ነጭ-አመድ” ለብሶ አመድ መስለናል። በተንቀሳቀስን ቁጥር አመዱ ከልብሳችን “ቡን-ቡን” እያለ ይበንናል። ሲይዙኝ ከአዲስ አበባ የገዛሁት ጥቁር ሱፍ ልብስ ወደ አክሱም ስሄድ ለበዓሉ ብየ ለብሼዉ ስለነበር ሱፍ ልብሴ በአመድ ተበላሽቷል።

ከዚያ በሚቀጥለዉ ቀን ወደ አስርቤት ወስደዉ ከሌሎች ጋር ቀላቀሉን። ስንቀላቀል ወደ 40 አስከ 50 አስረኞች እዛዉ ቆዩን። ስትመለከታቸዉ በጣም የሚያስደነግጡ ፍጡራን፡ ገላቸዉ ያለቀ፤አጥንት ብቻ የቀሩ፤ ቆዳቸዉ ተጣብቋል።የደከመ ዓይናቸዉ ሲንከባለል እናያለን። ጸጉራቸዉ አልቋል።በንዴት በብስጭት እና በጸሃይ ብርሃን እጦት ተቃጥሏል።ቆዳቸዉ ወደ ቢጫነት ተለዉጧል።በምርመራ ግርፋት እና በእሳት ሰዉነታቸዉ ተቃጥሎ “ቁስለዉ” ተገሸላልጠዋል።ለማየት በጣም የሚያስፈራ እና የሚያስደነግጥ ተርዒት ነበር ያየነዉ። አነዚህ አስረኞች፤መነሳት መቆም አይችሉም። “እንደምናችሁ እንኳን ደህና መጣችሁ”፡ ሲሉን መናገር አቅቷቸዉ “ድምፃቸዉ” በጣም እጅግ በጣም “ሎሆሳሳ” “ቀጭን ድምጽ” ብቻ እንደምን ብለዉ ለመናገር ይሞክራሉ።እኛ ደነገጥን። እኛም እንደነሱ የምንሆን አልመሰለንም “የምን ተአምር” ነዉ እያየነዉ ያለን ብለን የምንናገረዉ ነገር ጨንቆናል።በብረቱ ድንጋጤ ተዉጠናል።አነሱም በዛ ቀጭን ድምጻቸዉ “አቤት- አግዚኦ! እናንተም ወደ እዚህ ሲኦል መጣችሁ? ብለዉ ስለኛ አዘኑ”። ታጋዮቹ መጡ እና “አንድ ክንድ የም’ታክል” በክንዳቸዉ ለክተዉ/ “አንተ የምትተኛበት ቦታ እዚህ ነዉ፤ ያንተም እዚቹ ነች”፦ እያሉ የምንተኛባት ስፍራ አስታዉቀዉ ለክተዉ ሰጡን። መተኛት የምትችለዉ እነሱ ለክተዉ በሰጡህ የምኝታ ስፍራ ነዉ። እዛችዉ ሲኦል ያየሁባት የዳስ አስር ቤት 6 ወር ታስሬ አለሁ።

ጥያቄ፡- ሰዉነታቸዉ በግርፋት እና በጸሃይ እጦት የተሰቃዩት ሁኔታቸዉን ስታዩ በጣም ያስደነግጣል ያሉዋቸዉ እነኚህ እዛዉ አስር-ቤት ያገኛችሗቸዉ ሰዎች የዕድሜ ክልል ምን ያህል ነዉ?

አቶ ገዛኢ፡- ህጻናትም አሉ! ህጻን፤ ሽማግሌ የሚባል ነገር አይለዩም። ሲያስሩ እና ሲገረፉ ማን ምን አይሉም። በጣም አረመኔዎች ናቸዉ። ከሚገረምህ ነገር ተይዘዉ ተደብድበዉ ብዙ ጊዜ ጸሃይ ስለማይሞቁ አእምሮአቸዉ ስተዉ ያበዱ የዓዲ ዳዕሮ፤የዓዲ አዉዓላ እና ከሌሎች ስፍራዎች የተያዙ አእምሮአቸዉ ስተዉ ያበዱ ወጣት ተማሪዎች ነበሩ።

ጥያቄ፡- በድብደባዉ ምክንያት ነዉ አእምሮአቸዉ የሳቱት?

አቶ ገዛኢ ረዳ፡- በድብደባ እና ምንም ባለሰሩበት ነገር እየተለጠፈባቸዉ ለብዙ ጌዜ አስረዉ መላወሻ ስላሳጧቸዉ በጭንቅ በሃሳብ በብስጭት ኣእምሮአቸዉ ሳቱ።ያለቅሳሉ! ራሳቸዉ ስተዉም የማይሆን ነገር ሲዘላብዱ፤ሲናገሩ ትሰማቸዋለህ።

ጥያቄ፡- ወደ አስር ቤቱ ከተወረወሩ በሗላ እርስዎንስ ምን አደረጉዎት።

አቶ ገዛኢ ረዳ፡- ጠራናፊት ነበርክ አሉኝ። አዎ እኔ ጠራናፊት ነበርኩ አለኩዋቸዉ። ይሄም በከተማ ዉስጥ ያሉት አባሎቻችሁ ያዉቁታል።አብረን እናወራለን እንዝናናለን ወዳጆች ነን። ነገር ግን በናንተ ድረጅት ላይ ያደረስኩት ጥፋት፤ ፤አበሳ ወይም በደል የለም። ከተማ ሆነህ ሰዎች ወደ በረሃ እንዲሄዱ ወደ ድርጅትህ ስንቅ ታቀበል ነበር፤መረጃም ታስተላልፍ ነበር፡ ብለዉ ወነጀሉኝ። ከዚያ በሗላ ማስፈራራቱን ቀጠሉበት።ከቃል ጥያቄ ምርመራ በሗላ በማግስቱ ጥዋት “ተነስ” ብለዉ ወስደዉ አጠገብ ካለዉ አንድ ዛፍ ሰር አስረዉ ከዛፉ ጋር አጣብቀዉ አሰሩኝ። በዙሪያየ የእንጨት ማገዶ ከመሩብኝ።…

ጥያቄ፡- እርስዎኑን እንዲያቃጥሉዎት ነዉ?

አቶ ገዛኢ፦
አዎ! እኔን ለማቃጠል። ቀጭን እንጨት እና የሚቀጣጠል ሳር ዙርያየ ደርድረዉበታል። ሊያቃጥለኝ የቆመዉ መርማሪየ ሰዉየ እጁን ዘርግቶ በመለካት “አንድ ክንድ” ከለካ በሗላ እኔን ከዛፉ ጋር የፍጢኝ አስሮ ማገዶዉን በዙርያየ ከምሮ የፍጥኝ እንደታሰርኩ ከዛፉ ዙርያ ኩምትር ብየ እንድቀመጥ አዘዘኝ። በአንድ ክንድ ርቀት በዙርያየ የተከመረዉ ሳር እና ቀጫጭን እንጨት በሳር አቀጣጥሎ እሳት ለኮሰበት። እንጨቱ መጀመሪያ ጭስ ማዉጣት ጀመረ፤ ሳሩም መቀጣጠል ጀመረ ጭሱ አፈነኝ። ጭሱ ሲያፍነኝ ማስተንፈስ አልቻለኩም ጨነቀኝ። ጥልቅ ባሕር ዉሃ ዉስጥ ጠልቀህ ተዉጠህ መዉጫ እናዳጣ ሰዉ ነዉ ትንፋሽ አጥሮኝ የተሰማኝ። ጭሱ በዙርያየ እንደ ጉም እየተልመለመለ ሲነሳ መርማሪየ ቆሞ አሳቱ ይበልጥ እንዲቀጣጠል ቆሞ ይቆጣጠራል ፤እኔኑም ያየኛል። ጭሱ ወደ እኔ እየገፋ እየበራታብኝ “አፈነኝ”። ሲያፍነኝ መሳል፤ማስተንፈስ አልቻልኩም። በጣሙን ጨነቀኝ። ነፋሱ በርትቶ ጭሱን ካስወገደዉ በሗላ፡-እንጨቱ እየተቀጣጠለ ወደ አሳት ተቀይሮ መንደድ ጀመረ። ነፋሱ ነበልባሉን በሁሉም አቅጣጫ ወደ እኔ ዙርያየ ይገፋዉ ስለነበር ገላየን መለበለብ ጀመረዉ። እጄ የፍጥኝ ታሰሬአለሁ። አግሬ እጄም መላወስ ስለማልችል፤ ወላፈኑ አሰቃየኝ። ሙቀቱ የቃጠለዉ ወላፈን ነብሰ ስጋየን አሰቃያት። ከጎን እና ከሗላ እየለበለበኝ ካለዉ ወላፈን ለመሸሽ እግሬን ወደ ፊት ለመዘርጋት ብሞክር ወደ ባሰ እሳት ይጠጋል። የማደርገዉ ጨነቀኝ። እጄ የፍጥኝ በጥብቅ ስለታሰረ፤ ያለሁት “ቁጭ” ብየ አግሮቼን “ኩምትር” አድርጌ ነዉና ወደ ግራ ስል ወደ ቀኝ ወደ ሗሊት ማምለጫ የለኝም። ወደ ሗላየ እንዳላፈገፍግም ከዛፉ ጋር የፍጢኝ ተጣብቄ እንዳልንቀሳቀስ ታስሬአለሁ። ወዴት ልግባ! ወዲያዉኑ ሰዉነቴ ቆዳየ በመላ አካላቴ “ቱት.. ቱት.. ቱት.. ብሎ ዉሃ ከረጢት ቋጥሮ አበጠ።

ጥያቄ፡- ጋላዎ ዋሃ ቋጥሮ ነዉ?

አቶ ገዛኢ ረዳ፡- አዎ! መላ አካላቴ እሳቱ ስለለበለበኝ ሰዉነቴ ዉሃ ቋጠረ። ወዲያዉኑ እንደተሰበረ እንስራ “ቧ!!!!” ብሎ የቋጠረዉ ዉሃ ፈሰሰ!

ጥያቄ፡- “በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ”! ከዚያ ጥያቄ፡- በሗላስ?

አቶ ገዛኢ፡- ከዚያ በሗላ፤ “ዕረፍት!” አሉኝ። አምላክ ዕረፍት አይስጣቸዉና! ያሰሩኝን ፈቱልኝ። ሲፈቱኝ ወደ መሬት ተንጋለልሁ እና ተዘረጋሁ። ሰዉነቴ ወደ መዛል ሲል “ተነስ!” አሉኝ። አእምሮየ የት እነዳለሁ አይታወቀኝም -ነገር ግን ትንሽ ትንሽ ይታወቀኛል። ተነስ ብሎ እንደገና ሳሩን በእሳት አቀጣጥሎ መሬት ላይ ተዘርግቼ እንዳለሁ “የተቀጣጠለዉ የሳር እሳት” እንደ ቀጤማ በላየ ላይ ወርዉሮ በትኖ እፊቴ ላይ ረጨብኝ ።

ጥያቄ፡- ወይ ጉድ! ወይ ጉድ! በስመ አብ! በስመ አብ! ምን ተአምራት ነዉ!? እሺ ይቀጥሉ።

አቶ ገዛኢ ረዳ፡- በሗላ -አሳቱን ገላየ ላይ ሲበትነዉ፡ “ከስቃይ ሰመመን” ባንኜ “እናንተ ሰዎች ከእኔ የምትፈልጉት ነገር ምንድ ነዉ? ለምን አትገድሉኝም ከዚህ ሁሉ? አልኳቸዉ። እኔ እናንተን በጣላትነት የተነሳሁበት ቀን የለም፡ እኔ ደርግን ነዉ የተቃወምኩት እንጂ ወያኔን አልተቃወምኩኝም። ወንጀል አለህ የምትሉት ካለ አምጡልኝ፤ በወንጀሌ ልቀጣ፡ ካልሆነ ግን አታሰቃዩኝ ብየ ብማጠናቸዉ ሊሰሙኝ አልፈለጉም።መጀመሪያ አሳቱን ለኩሰዉ ሲለበልቡኝ ነጭ ጭስ እየተምዘገዘገ ወደ እላይ “ቦለል” ማለት ሲጀምር ገና አይቸዉ “አቤት! አቤት! ቅዱስ ሚካኤል! ሳልሞት በምድር በሕይወቴ እያለሁ “ገሃነመ እሳት” አሳየከኝ!? ማረኝ አምላኬ ብየ ጸሎት ሳደርስ” መርማሪዎቼ *ከት-ከት* ብለዉ *ሳቁብኝ*።“ምንድ ነዉ የምትለዉ?” ብለዉ ተሳለቁብኝ። *ቅዱስ ሚካኤል ፍርድህን ላክልኝ፤ምሕረቱን ላክልኝ* ነዉ ብየ ጸሎት እያደረስኩ ያለሁኝ ስላቸዉ፦ እንደ ገና “ከት-ከት” ብለዉ ተሳሳቁብኝ። “ቧልጪት መሳይ ሁለት የድንጋይ ኮረት ከመሬት ለቅመዉ” *ኮረቶቹን እርስ በእርስ እያጋጩ ፤ ቅዱስ ሚካኤልህን በዚህ የድንጋይ ብልጭታ ይታያሃል?” በማለት ተሳለቁብኝ።ከዚያ አሳት ስቃይ አስወጥተዉ ወደ ቦታየ ወሰዱኝ። በስቃይ እንደሰነበትኩ ቁስሌም አልዳነም፦ እንደገና በሁለት ታጋዮች ታጅቤ ወደ አንድ መርመራ አቀረቡኝ። መርማሪዉ “አሁንስ ተማርክ ወይ?” ብሎ ጠየቀኝ። ቁስልህ ዳነ? ብሎ ጠየቀኝ። እኔም ይሄዉ እንደምታየዉ ነዉ፡ ቁስሌ እንኳን ሊድን የቁስሉ ስቃዩ እየበረታብኝ ሄዷል አልኩት። አሁንሳ ተማርክ? አለኝ። “ጥሩ ትምርት ተምሬአለሁ አዎ!” አልኩት።ታዲያ ተምሬአለሁ ካልክ የምታምነዉን አምነህ ንገረን አለኝ? የሰራሁት ነገር ስለሌለኝ የማምነዉ ነገር የቱ እነደሆነ አልገባኝም። ምን ጥፋት በደልኩኝ? ወንድሞቼ ለምንድ ነዉ በደሌን የማትነግሩኝ? ጠራናፊት ነኝ ብያችሗለሁ። ከዚያ በላይ የምታዉቁት ካለ ንገርኝ እነጋገርበት ካልሆነ አታሰቃዩኝ። አልኩት።የለም የምታዉቀዉ ነገር አለ፡ታዉቃለህ!አለኝ።የምታዉቁት ነገር ካለ ለምን አትነግሩኝም? ስለዉ፦ የተማርክ መስሎን ነዉ እንጂ ገና አልተማርክም እና ትገባታለህ ብሎ “ታጋዮቹን ዉሰዱት!” ብሎ ወደ መግረፊያ ቦታ ወስደዉ አግሬን ወደ ላይ ጭንቅላቴን ወደ ታች ዝቅዝቅ ከጣራ ጋር አስረዉ በማንጠልጠል የቀኝ “ሆድ እግሬን” ከዉስጥ ገልብጠዉ ”በጎማ ጠበጠቡኝ!ጠበጠቡኝ!” ።ሙልጭ አደርገዉ ነብሰ ስጋየ አስከምስት ገረፉኝ። ጎማዉ በጣም ያሳምማል። ጎማዉ ዉስጥ ጠጣራ በትር የሚመስል አለዉ። ሆድ እግሬን ጠብጥበዉ ጠብጥበዉ ደም አስኪፈስ ድረስ ገሸላለጡኝ። ሰዉነቴ ሃይለኛ ትኩሳት እና ላብ ተወብቄአለሁ። ከጉልበቴ በታች “ድምብል ብል” ብሎ ተነፍቶ አብጧል። አግሮቼ ለረዥም ጊዜ መዳን አልቻለም። አስከዚች ደቂቃ እና ቀን አስከዛሬ ድረስ ያመኛል። መሮጥ ቀርቶ ረዥም መንገድ መራመድ አልችልም።ስቃዩ ብርቱ ነዉ። ሆድ እግሬ በጎማ ለረዢም ሰዓት ስለገረፉኝ ወደ “ዉስጥ ጎርጉዶ” ስጋ መሙላት አቅቶት አ ጥንት እና ጅማት ስለቀረ፤ ፈጠን ብየ በመርገጥ ረዢም ጉዚ ለመራመድ ከሞከርኩኝ ያመኛል። ጣቶቼም በጎማ ስለጠበጠቡኝ በጣም ብዙ ስቃይ እያሳለፍኩ ነዉ ያለሁት።

እና አንደዚህ ዓይነት ስቃይ በእኔ ብቻ ሳይሆን ቁጥር ስፍር የሌለዉ ያለ ምንም ጥፋት እና ፍትሃዊ ፍርድ/ቤት መአት ብዙ ሰዎች በእሳት እየተለበለቡ ብዙ ግርፋት እና ስቃይ ደርሶባቸል። አንዚህ ሰዎች “አዛዉንት አያዉቁ”፤”ቤተስብ የሚባል ነገር እያዉቁም” ከባህላችን ዉጭ የሆነ የጭካኔ ምርመራ አካሂደዋል። አረመኔዎች ናቸዉ። አነዚህ ህዝባቸዉን የካዱ ናቸዉ። ከትግራይ ሕዝብ አብራክ ወጥተዉ በሕዝቡ ላብ ተምረዉ፤እዉቀት ገብይተዉ፡በአካባቢዉ ልምድ እና ወግ አድገዉ፡ተመልሰዉ ያሳደጋቸዉን ያስተማራቸዉን ያጎረሳቸዉ እና የተንከባከባቸዉ ህብረተሰብን የሚያጠቁ “ክፉ ሰዎች” “አጋንንት” ናቸዉ።የሰዉ ልጅ ሕሊናም የላቸዉም። ብዙ ሰዉ ደብድበዉ ከጥቅም ዉጭ አደርገዋቸዉ አበላሽተዋቸዋል።
ጥያቄ፡- አቶ ገዛኢ ዕድሜዎ አባት አዛዉንት ነዎት። በእሳት ተቃጥሎ በሕይወት መትረፍ፤ በእዉነቱ የእግዚአብሔር ድርሳን የጸለዩለትን የለመኑትን ቅዱስ ሚካኤል በክንፉ አጥልሎዎታል። ይህ በሰዉ ልጆች ላይ የተፈጸመ ጭካኔ በትግራይ ተወላጆች ላይ የተፈጸመ ወንጀል፤ ላልሰማ ላላወቀዉ ሕዝብ እንዲነግሩ በማለት መርማሪዎቹ የተሳለቁበት አምላክ “ቅዱስ ሚካኤል” የከሞት በር በእግዚአብሔር አምላክ ታአምር ያዳነዎት መሆኑን ነዉ አንጂ የሰዉ ልጅ በእንደዚህ ዓይነት አረመኔነት ተደብድቦ በ እሳት ወላፈን ተቃጥሎ መትረፍ በእዉነቱ የሚገርም ተአምር ነዉ፡ከመላት ምን ማለት ይቻላል!ከዛ ከድብደባዉ በሗላስ ምን አስከተለ?

አቶ ገዛኢ ረዳ፡- መቸም ይህ በእኔ ላይ የተፈጸመዉ ግፍ በእኔ አልተጀመረም በእኔም ላይም አልቆመም።ብዙ አስረኞች፤ያለ ጥፋት ተደብድበዉ በእሳት ተቃጥለዉ መላ ሰዉነታቸዉ “ደም” እና “መግል” ቋጥሮ “ለቁስል” እና “ለዘላቂ ስቃይ” “ለአእምሮ መታወክ” ከመዳረጋቸዉ በላይ በየቀኑ በእዉነቱ ከ3 አሰከ 4 አሰከ 7 ወይንም 8 ድረስ ከተለያዩ ቦታዎች የሰበሰብዋቸዉ አስረኞች ይገደላሉ። ሊገድልዋቸዉ ሲፈልጉ፤ ጥዋት ጥዋት “ተሰናበትዋቸዉ” ይሉናል። እየጠሩ ሲወስድዋቸዉ የሚገደሉት ሰዎች “ለወንድሜ ንገሩልኝ፤ለእናቴ ለአጎቴ ንገሩልኝ”- “ደህና ሁኑ” ከእንግዲህ ወዲህ አንገናኝ ይሆናል! “እግዚአብሐር ከእናንተ ጋር ይሁን”! እያሉ ይሄዳሉ። በጣም ከሚያሳዝን ነገር፤ “አቶ ገብረሊባኖስ መዝገቦ” የተባሉ የተከበሩ ትልቅ ጨዋ ሰዉ በሽሬ አዉራጃ ዋና ከተማ በእንዳስላሴ ከተማ ኗሪ ፤ የሆኑት እኒህ ሰዉ ፤ያዉራጃዉ ግምጃ ቤት ሂሳብ ሹም ሆነዉ ሲሰሩ፤ በወቅቱ ደርግ ትላልቅ የአገሬዉ ታዋቂ ሰዎች የሚባሉ ሰብስቦ “በረሃ ድረስ ሄዳችሁ “ምንድነዉ ነገሩ? ብላችሁ” አስኪ ነገሩ በሰላም የሚፈታ ከሆነ በሰላም ለመፍታት እንዲቻል በረሃ ድረስ ያሉበት ቦታ ሄዳችሁ የወያኔ መሪዎችን አነጋግራቸሁ ለዕርቅ አነጋግሯችዉ። በሽምግልና የሚታይ ከሆነ እንሞክረዉ እና አስኪ ሄዳችሁ ህዘቡን ወክላችሁ አነጋግሯቸዉ” በማለት እሳቸዉ እና ሌሎችም እንደዚሁ “ባላምባራስ ተወለደ ገብረስላሴ” የተባሉ የእንዳስላሴ ከተማ ጭቃ ሹም፦ሌላም ገስጥ ኪዳነማርያም የተባለ የ ትልቅ ባላባት ልጅ ከሽማግሌዎቹ ጋር ለሽምግልና ተመርጦ አብሮ ሄዶ ነበር (ልጁ በወቅቱ አባትየዉ ከሚኖሩበት ከተማ ሄደዉ ወያኔዎች የገደሏቸዉ መሆኑንም ጭራሽ አልሰማም፤ኣላወቀም ነበር)። ሽምግልናዉ ስላልወደዱት “አይሆንም ብለዉ ወደ መጡበት ከመመለስ ፈንታ እነሱንም ያለ ምንም ወንጀል ይዘዉ አስቀርዋቸዉ”። የታሰሩት ቀደም ብለዉ እኛ ከተማ ዉስጥ እያለን ከመያዛችን በፊት ነዉ። አብረዋቸዉ የነበሩ ሌሎች አስረኞች ጭምር ታስረዉበት ከነበረዉ “ግህነም” ከተባለ “የጋሀነመ እሳት አስር ቤት” መጥተዉ እኛዉ ጋር አብረን ተቀላቅለናል። ልክ እኔን በእሳት አቃጥለዉ እንደለበለቡኝ አነሱም ሰዉነታቸዉ በሙሉ በእሳት ተቃጥሎ ለብልበዋቸዋል። ገላቸዉ ቁስል ደም እና መግል ብቻ ሆነዋል። በተለይ አቶ ገብረሊባኖስ መዝገቦ እኔ በእሳት ከተጠበስኩት በላይ ተጠብሰዋል።ምክንያቱም በጀርባቸዉ ደምም መግልም ይንዠቀዠቃል። መተኛት አይችሉም- የቁስሉ መጠን ለዓይን ይዘገንናል።አቶ ገብረሊባኖስ መዝገቦም ሆኑ ባለምባራስ ተወልደ ገብረስላሴ በጣም ደግ የተከበሩ ባላባቶች ናቸዉ።ባላምባራስ ተወለደ ገብረስላሴም የአከባቢዉ፤የሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ማዕረግ/አድባር ነበር ማለት ይቻላል። ባላምባራስ ገብረስላሴ ወደ ምርመራ ሲወስዱት “አይዞህ ቆመንም ያዉ ሞት ነዉ፡ ብንሞትም ያዉ ሞት ነዉ- በርታ” ያልዋልክበት አበሳ ንገረን ቢሉህ ያላደረግከዉ ነገር በጭንቅ “አዎ” ብለህ አትመንላቸዉ፡ብየዉ ወስደዉ ደጋግመዉ እንደገና በእሳት እየለበለቡ እየደበደቡ ሲያሰቃዩት፡መከራ ሲበዛበት“የሚሉት ሁሉ ኣዎ! አላቸዉ”። ቀጥለዉም ለወጣት “ገስጥ ኪዳነማርያም “እዚህ የመጣኸዉ አባትህን ስለገደልንልህ የደም ብድር ለመመለስ ነዉ ወደ እኛ አዚህ ድረስ ደፍረህ የመጣኸዉ?” አሉት። አሱ ደግሞ አባትየዉ በእነሱ እንደተገደሉም ጭራሽ አላወቀም ነበር። ሌላዉ ደግሞ ከዓድዋ ወደ ሰለኽለኻ የተባለች ትንሽ ከተማ እህቱን ለመጎብኘት መጥቶ የነበረ አንድ ታዳጊ ወጣት ልጅ ይዘዉት አብሮን ነበር። “አንተ ደግሞ እዚህ የመጣኸዉ ከምንጠጣበት ወንዝ መርዝ ልትጨምር ነበር የመጣኸዉ? ብለዉ፤ እሱንም በ እሳት ለብልበዉ ገርፈዉ አሰቃይተዉ እንድንምርህ ከፈለግህ “አዎ” ማለት አለበህ ብለዉት “አዎ” አምናለሁ ብሎ ባልዋለበት ነገር አሳምነዉ አክስቱን ለመጠየቅ ወደ ሰለኽለኻ አብሮት ከዓድዋ ወደ ሰለኽለኻ የመጣዉ “ብርሃነ መስቀል ጎሽም” እንደገና መሓመድ የተባለዉ ወጣት ልጅ በአንድነት በአንድ ቀን ሁሉንም ወስደዉ ረሸኗቸዉ። ወስደዉ ከረሸንዋቸዉ በግምት ወደ 30 ወይም ወደ 35 የሚሆኑ ሰዎች መካከል ናቸዉ።ዝርዝር ስማቸዉ ቆይቼ ልገልጽልህ ነዉ። የጭካኔያቸዉ መጠን የሰዉ ፍጡረነትክን ያስጠላል። ትግሬነትክን ያስጠላል።በወቅቱ ያ ግፍ ስትመለከት “የትግራዋይነት ትርጉም ሃዘን መሆኑን ይሰማሃል”። ይህ ጭካኔ የሚያራምዱ ባዕዳን ሳይሆኑ ከምድሪቱ ከእኛዉ ትግራይ መሬት የተወለዱ የአምላክን ክብር የሚንቁ ከአብራካችን የወጡ የትግራይ ተወላጆች ያሳደግናቸዉ የምናዉቃቸዉ ልጆቻችን ናቸዉ” ይህ ሁሉ ግፍ በሕዝብ ላይ እየፈጸሙ ያሉት። ለምሳሌ የአማራ ተወለጅ የሆኑ በተለያዩ ምክንያቶች የተያዙ ነበሩ።ይለቁዋቸዋል። ትግሉ ለትግራይ ተወላጅ እንጂ እነዚህን አይመለከትም። ትግሬዎች የመታገል ግዴታ አለባቸዉና ይሄነን ያልፈጸሙ ፤ለቅጣት እና ለሞት መዳረግ አለበት ይላሉ።የትግራይ ሰዉ በእሳት ተቃጥሏል፡ አልቋል። ሌላ ቀርቶ የፈላ ዉሃ እየደፉብህ ይመረምሩሃል። ሳንጃን እሳት ዉስጥ አሙቀዉ ገላህን ይጠብሱሃል። የጓንዴ ሳንጃ በጣም ትልቅ ነዉ። ሳንጃዉ በሃይለኛ የእሳት ፍም ያኑሩት እና እሳቱን እያፋሙ ሳንጃዉ በከፍተኛ ግለት ያግሉታል። የጓንዴ ሳንጃ ነዉ። ሳንጃዉ እንደጋለ ወደ እሳትነት ተለዉጦ ብረቱ ቀይ ሆኖ ሲፍም የጋለዉ ሳንጃ ያነሱ እና የእስረኛዉን ገላ በጋለዉ ሳንጃ ይጠብሱታል።እያቃጠሉ፡ ደም በደም አስኪሆን ዉሃ አስኪቋጥር ድረስ “አግዚኦ!!” እያለ ቢማጸንም ሰሚ የለዉም-ያቃጥሉታል።-ጭካኔዉ-በጣም-ብዙ-ነዉ።

ጥያቄ፡-አቶ ገብረሊባኖስ መዝገቦስ በእሳት ያሁሉ ስቃይ ካስቃዩዋቸዉ በሗላ ከእስር ተለቀቁ ወይንስ እንዴት ሆኑ?

አቶ ገዛ ረዳ፡- አልተፈቱም። ገደልዋቸዉ! ሰዉየዉ ሲገድሏቸዉ፤ አረመኔነት በተላበሰ እርኩስ አገዳደል ነዉ የገደሏቸዉ። እነሱ እንደነገሩን ከሆነ፡ በወቅቱ “ኢድዩ” (ኢድሕ) ወደ አካባቢዉ በብዛት ሰራዊቱን ይዞ እየገሰገሰ በፍጥነት ስለመጣ በድንገት ስለደረሰባቸዉ ያካባቢዉ ወያኔዎች ተደናገጡ። ኢዲዩ መጥቶብናል እና “እንግደላቸዉ” ብለዉ እኛን ለመግደል ወያኔዎቹ ሌሊቱኑ ወደ ታሰርንበት የዳስ እስር-ቤት ገቡ።ገቡ’እና አስወጥተዉ በታራ አስሰለፉን።

ጥያቄ፡-ምን ሊያደርጓችሁ?

አቶ ገዛ ረዳ፡- ሊፈጁን! ሊገድሉን አስበዉ የነበረዉን እንደገና ይቆዩ ብለዉ ሃሳባቸዉን ለወጡ። እንደ ገና ተነጋግረዉ ሃሳበቸዉን ለዉጠዉ ወደ አንድ ሸለቆ መሳይ አስገቡን።

ጥያቄ፡- ለምን?

አቶ ገዛኢ፦
ሊገድሉን። መልሰዉ ሃሳባቸዉን ለወጡ እና እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ አቆዩን። እኛን በሰልፍ መዳዳዉ እንድንቀመጥ ካደረጉ በሗላ አቶ ገብረሊሰባኖስ መዝገቦ በጠበሷቸዉ የእሳት እና የግርፋት ስቃይ ስለበዛባቸዉ “መቆምም መነሳትም መራመድም ስለማይችሉ አካላቸዉ ኩፉኛ ስለተጎዱ እንደ አንዳንዶቻችን ቆመዉ መራመድ ስላማይችሉ፡ አሳቸዉ እና ሃይለኛ የወባ በሽታ ይዞት ታምሞ በጠና ተኝቶ ሲሰቃይ የነበረ አንድ የእነርሱ ታጋይም (ትዉልድ ቦታዉ እንትጮ ወረዳ) ሁለቱን እዛዉ ገደሏቸዉ።

ጥያቄ፡- እንዴ! የገዛ ታጋየቸዉም ጭምር?

አቶ ገዛኢ፦
አዎ! የራሳቸዉ ታጋይ። እኛ ጋር አልታሰረም፡ ከአጠገባችን ካለዉ መጠለያ ዳስ ነበር ራቅ አድርገዉ አስተኝተዉት ሲታከም የነበረዉ። ታጋያቸዉ ነዉ። የገዛ ታጋያቸዉም ጭምር ገደሉት። ወባ ይዞት ተኝቶ እንጂ እስረኛ አይደለም። አቶ ገብረሊባኖስ መዝገቦም ተኝተዉ እንዳሉ በጥይት ገደሏቸዉ ። በሦስት ጥይት ተኩሰዉ እዛዉ እንዳተኙ ገደሏቸዉ።እጅግ ዘግናኝ ፤ጭካኔ ያለበት፤አስደንጋጭ አገዳደል ነዉ። የነሱ ታጋያቸዉም በመታመሙ ከእኛ ጋር መጓዝ ስለማይችል አሱንም ገደሉት። በጣም መልከ መልካም ረዥም ቁመና የነበረዉ ወጣት ነበር።በጣም አረመኔዎች ናቸዉ።

ጥያቄ፡- በጉዞ ላይ እንዳይሸከሙት በማለት ነዉ?

አቶ ገዛ ረዳ፡- አዎ! እንዳይሸከሙት።እነሱን በጭካኔ መንገድ ከገደሏቸዉ በሗላ፤መረብ ዉስጥ “ማይ ላም” ወደ ተባለዉ ቦታ ወሰዱን። ከባድ ችግር ገጠመን።ሕሊናችን ባየነዉ ጭካኔ ተጎድተናል፡በዚያ ላይ እዛ ድረስ ለመድረስ ትልቅ ችግር ነዉ የገጠመን። መንገዱ በጣም ሃሩር ነዉ፡አሸዋማ ነዉ።አሸዋዉ አያስኬድም፡ከባድ ነዉ።ብዙዎቹ ደከሙ። መራመድ አልቻሉም፤እሩቅ ጉዞ ነዉ።አንዳንዶቹ አእምሮአቸዉ ተዳክሞ ነበር፤በሃይለኛ የራስ ምታት የተሰቃዩም ነበሩ።በስንት መከራ አንዳንዶቻችንን እየጎተቱም እያስፈራሩም መንገዱን እንድንገፋ አደረጉ። እጀግ ከደከሙት መሃል “ሃለቃ ጥላሁን ረዳ” የተባሉ (የትዉልዳቸዉ “ዓዲ አዉዓላ”) ደክመዉ መላወስ ስላቃታቸዉ፡”እንግደለዉ- ከዚህ ሰዉ ጋር ስንንቀራፈፍ ጊዜ አናጠፋም” በማለት ሊገድሏቸዉ ሲዘጋጁ፤ እንደ አጋጣሚ ሆኖ “የድርጅቱ ሃላፊዎች” በዛዉ ሲያልፉ ድንገት ስለተገናኙ፤ “የደከመ ሰዉ አለን እና ልንገድለዉ ወስነናል፤ምን ይመስላችሗል?” ብለዉ ጠየቋቸዉ። “ጥፋታቸዉን አረጋግጣችሁ ለሞት የተፈርዶባቸዉ ናቸዉ?” ብለዉ ጠየቋቸዉ፡ “ገና አልተፈረደባቸዉም” ሲሏቸዉ- “ይቆዩ አትግደሏቸዉ ብለዋቸዉ ከተሰነባበቱ በሗላ፦ ሊገድሏቸዉ ተዘጋጅተዉ የነበሩት አቶ ጥላሁን ይግዛዉን “ እንደ ጀምቢል ዕቃ በአንዲት ቀጭን እንጨት በገመድ አስረዉ ዥወዙዌ አንጠልጥለዋቸዉ ወደ መረብ ቀጠልን።

እዛዉ አሰልቺዉ በረሃ የዉሃ ጥም ይዞን ለአመሉ ለራሳቸዉ ይዘዉት ከነበረዉ “ኮዳ/ብራሾ” ዉሃ ከንፈራችንን እና የደረቀዉ ምላሳችን እንድናረጥብ አቀመሱን። ሃለቃ ጥላሁንም በዛች እንጨት አንጠልጥለዋቸዉ ሲጓዙ በጣም፤ እጅግ በጣም ስለተዳከሙ፤ እንረፍ ብለዉ በአንድ ቦታ አዳር አደርግን እና አረፍን።ቦታዉ “የኤርትራ ቦታ ነዉ”፡ላዕለዋይ ባርካ ይባላል። እዛዉ እንደደረስን ማታዉኑ በሰልፍ “ለሁለት ምድብ” ከፈሉን።ከዚህ ወዲህ ያላችሁት ወደ “ቀይ ኮከብ” ትሄዳላችሁ፤ ይሄኛዉ ምድብ ደግሞ ከእኛ ጋር ጉዞ ትቀጥላላችሁ፡ ብለዉ ስም ዝርዝር ጠርተዉ ለያይተዉ ሌሊቱን አዳር አደረግን። ከእኛ ለይተዉ ያሳደሯቸዉን ሰዎች ሌሊቱን ከተኙበት ቀስቅሰዉ በማስወጣት “ፈጇቸዉ!!። ትንሳኤ ቀን ነበር፤ በዓዉደ አመት ዕለት በጥዋቱ ፈጇቸዉ! የፈጇቸዉም ቦታ ካረፍንበት ስፍራ ብዙም አይርቅም። ሁሉንም ረሸኗቸዉ።ሃያ አመስቱን (25) ሰዎች በጥይት ደብድበዉ ገደሏቸዉ። ሲረሽኗቸዉ፤የተኩሱ እሩምታ ይሰማናል።25ቱን ሰዎች በጥይት ደብድበዉ ከገደሏቸዉ በሗላ በላያቸዉ ላይ “ቅጠል አርከፍክፈዉባቸዉ እዛዉ ጥለዋቸዉ ሄዱ”።
ጥያቄ፦ ሳይቀብሯቸዉ፤አመድ ሳያለብሷቸዉ?

አቶ ገዛ ረዳ፡- አልቀበሯቸዉም! ገዳዮቹ ጋኔል ስለተጫናቸዉ ስራቸዉ ሁሉ የጋኔል ነዉ። “በተርታ ተሰለፉ!” እያሉ ነዉ ሲገድሉም ምን ሲሉም ሲሄዱም “በሰልፍ ነዉ፡ ሲገድሏቸዉም አስሰልፈዉ በመደዳ ጥይት እናደርከፈከፉባቸዉ ነዉ ወድቀዉ እንዳሉ ‘እርጥብ ቅጠል’ በላያቸዉ ላይ ጣል-ጣል አድርገዉባቸዉ ሄደዉ ነዉ ሳይቀበሩ የተገኙት።ሬሳቸዉም የተገኘበት መንገድ- ግጦሽ ሲግጡ የነበሩ ከብቶች ሬሳዎቹ ከወደቁበት አካባቢ ሲደርሱ “ምን መጣብን ብለዉ ደንግጠዉ” ወደ ሗሊት ሲሸሹ፦እረኞቹም “ምን አይተዉ ነዉ እነኚህ ከብቶች የተደናገጡት?” በማለት ከብቶቹ ከሸሹበት ስፍራ ተሰብስበዉ ሲሄዱ የተረሸኑትን የ25ቱን ሰዎች ሬሳ መደዳዉን በሰልፍ ወድቀዉ እርጥብ ቅጠል ተርከፍክፎባቸዉ ሲያዩ “እረኞቹም ደንግጠዉ” ዜናዉን ይዘዉ እየረጡ በመክነፍ “ለኤርትራ ጀብሃዎች” ስለ ሁኔታዉ ነገርዋቸዉ። ጀብሃዎቹ ምን እርምጃ እንደወሰዱ እና እንዳስከተሉ ወደ ሗላ እመለስበታለሁ። ከተረሸኑት መሃል ለጊዜዉ ማስታወሻየ ስላልያዝኩ በሕሊናየ የማስታዉሳቸዉ ሰዎች “ተወልደ ገብረስላሴ” የሚባሉ ቅድም የነገርኩህ የሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ጭቃ ሹም የነበሩ አዛዉንት ሰዉ፤ አበበ ገብረማርያም የተባሉ የዓዲ አዉዓላ ልዩ ስሙ “ዓዲ ብዕራይ” የተባለዉ ኗሪ የሆኑ በጣም ሃይማኖተኛ ጸሎት እና ቅዳሴ እንጂ ሌላ ባሕሪ ያልነበራቸዉ ቸር የእግዚአብሔር ሰዉ፤ የ16 ዓመት ዕድሜ ነበረዉ ታዳጊ ወጣት (የሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ኗሪ) “ብርሃነ መስቀል ጎስም” የተባለ፡ እና የ12 ዓመት ዕድሜ የነበረዉ መሓመድ የተባለ ከዓድዋ አክስቱን ለመጎብኘት ወደ ሰለኽለኻ መጥቶ ይዘዉት ነበር ያልኩህ ልጅ እሱንም አብረዉ ገደሉት። ከሚገርመዉ ነገር “መሓመድ” ልጅ ስለነበር “እናቴ ናፍቃኛለች እና መሄዴ ነዉ እያለ እያለቀሰ፦ሲጎተጉታቸዉ የነበረ ህጻን ልጅ። ለምንድ ነዉ እኔን እዚህ ያመጣችሁኝ እናቴ የምትኖረዉ እዚህ አይደለም እና ልቀቁኝ” እያለ ሲወተዉታቸዉ የነበረ፤ ልብ ያልሰራ ገና ያልጠና ህጻን ነበር።

ወደ ሗላ ልመለስህ እና እረኞቹ ወደ ጀብሃ ሄደዉ ሲያመለክቱ፤ ጀብሃዎችም ሁኔታዉን ለማየት ወደ ስፍራዉ ሲሄዱ 25ቱም ሬሳዎች ወድቀዉ አይዋቸዉ። ጀብሃዎቹ የአካባቢዉን እረኞች አና ታጋዮቻቸዉን ሰብስበዉ እንደ ደምቡ “ድቤ-አመድ አለበሷቸዉ”። ይህን ካደረጉ በሗላ፤ ወደ ተሓህት ታጋዮች ዘንድ በመሄድ “ምን ጉድ ነዉ የሰራችሁት? በሽማግሌዎች እና ህጻናትን አንዴት እንደዚህ ዓይነት ነገር ትፈጽማላችሁ? ነዉር አይደለም ወይ-? ስትፈልጉ ለምን በገንዘብ እና በሌላ አትቀጥዋቸዉም ነበር? ህጸናቶቹስ ቢሆን አስተምራችሁ ከድርጅታችሁ ጋር ማሰለፍ አይሻልም ነበር ወይ? በማለት “ለትግራይ ሕዝብ ያልራራችሁ ለእኛም የምትረቡን አይመስለንም እና በአስቸኳይ ከቦታችን ለቅቃችሁ ዉጥልን”። በማለት በእዛዉ አካባቢ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት የወያኔ ታጋዮች በሙሉ አካባቢዉን “እንዲለቁ አደረጉ”። ይህ መረጃ እኛን ሲጠብቁ ከነበሩ ሁኔታዉ ሊቀበሉት-ያልቻሉ፤በጣም እጅግ በጣም ከዉስጥ አንጀታቸዉ ያረረ፤ያዘኑ የተሓህት ታጋዮች ናቸዉ ምስጢሩን የነገሩን።

በዚህ ምክንያት እኛንም ከቦታዉ አብረናቸዉ እንድንለቅ ሆነ። ከዚያ በሗለ ይግዛዉ ደስታ የሚባል ወላጅ አባቱ ዓድዋ አዉራጃ ዉስጥ የታወቁ የባላባት ልጅ የቀኛዝማች ወይም የግራዝመች ደስታ ሃይሉ የተባሉ ልጅ ነዉ። ይግዛዉ በጣም ብርቱ የሚያምር ቁመና ያለዉ ጥቁር መልከመልካም ወጣት ነበር። ይግዛዉ እነሱን (ተሓህትን) አይቀበልም። ይከራከራቸዉ፤ይቃወማቸዉ ነበር። አይታዘዛቸዉም። እሱንም ገደሉት። ሊገድሉት ሲታገሉት፡ ታግሎአቸዉ፤ አሱም አንድ ገድሎ አንድ አቁስሎላቸዉ ነዉ የሞተዉ። እጁ ታስሮ ሊገድሉት ሲወስዱት “እጆቹን አንደታሰረ፤ ታግሎአቸዉ፤በገዛ ካራቸዉ ወግቶ ገድሎአቸዉ ሲያመልጥ እሱን ለመያዝ እንደ ጅግራ በጥይት ሲያባርሩት፤አምልጥዋቸዉ ሲቶኩሱበት፤ በአጋጣሚ አንዲት ጥይት መትታዉ ስለነበር ከቦታዉ ካመለጠ በሗላ ወዴት እንደተሰወረ ስላጡት ከጊዜ በሗላ አሞራ በሰማይ ከብበዉ ሬሳዉን እያንዣበቡበት የተመለከቱ ታጋዮች ወደ ስፍራዉ ሲሄዴ “ይግዛዉ ደስታ” በተመታባት ጥይት ሬሳዉ ወድቆ አገኙት። ይግዛዉ ደስታ የታወቁት የዓድዋ ተወላጅ የደጀች ሃይሉ የልጅ ልጅ ነዉ።በጣም ዘግናኝ ሁኔታ ነዉ ያለፍነዉ። የተገደለዉ ሰዉ ብዙ በጣም ስፍር ቁጥር የለዉም። ብዙ፤እጅግ ብዙ ነዉ።

ጥያቄ፦ የእረስዎ ነገር መጨረሻ ምን ላይ ደረሰ?

አቶ ገዛኢ፦ መጨረሻ እኔን ጠርተዉ $15,000 (አስራ አምስት ሺሕ ብር) የገንዘብ ቅጣት እንድትከፍል ተፈርዶብሃል እና ወደ ቤተሰቦችህ ደብዳቤ ልከህ ገንዘቡን እንዲከፍሉልህ ላክላቸዉ አሉኝ። እኔም እንዴ! 15 ሺሕ ብር የሚባል ገንዘብ ከየት ላምጣዉ? ብየ ብጠይቃቸዉ፦ “ትከፍላለህ- ትወጣለህ፦ አትከፍልም፦ አዚቹ ትቀራታለህ!!” አሉኝ። ዉሳኔዉ “የተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ ዉሳኔ ነዉ! የተጋድሎ ሓርነት ህዘቢ ትግራይ ዉሳኔ- የዉጣ ዉረድ ገበያ አያዉቅም””። አሉኝ . እንግዲህ ከላችሁ’ማ ወደ “ዓዲ ዳዕሮ” ዉሰዱኝ እና እዛ የሚያበድረኝ ሰዉ ባገኝ ልፈልግ” ብላቸዉ። እዛዉ እማ ጠላት ይዞታል አንወስድህም፡ አሉኝ።በሗላ ወደ ባለቤትህ ደብዳቤ ላክ አሉኝ። እኔም ደብዳቤ ጻፌ ላክኩላት። ስጽፍላት የሁኔታየ ጉዳይ፡ የገንዘቡ መጠን፡ ጽፌ ላኩሁላት። ሦስት ልጆቻችነን የምትጠዉርባት አንዲት ንግድ ሆቴል ነበረችን፡እና ሆቴሉን ሽጣ ፤አልበቃ ብሏት በላዩ ላይ ከሰዉ ከወዳጅ ተበድራ ጨምራ የጠየቁትን $15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) ይዛ “ሰለኽለኻ” ወደ ተባለ ትንሽ ከተማ ድረስ መጥተሽ አስረክቢ ስላሉዋት፤ ሄዳ ከፈለቻቸዉ። የከፈለችበት የ$15,000 አስራ አምስት ሺሕ ብር ደረሰኝ ለታሪክ እንዲሆነኝ ብየ አስከ አሁን ድረስ ደረሰኙ በእጄ ይገኛል።ገንዘቡን እንደተከፈላቸዉ ላዕላይ ባርካ አጠገብ ከነበረዉ ከታሰርንበት ቦታ ፈትተዉ ለቀቁኝ።በማይ ምነ አድረጌ “ ማይ ደገላ” የሚባል በሰመማ አድርገን ወደ እንዳስላሴ ሽሬ አዉራጃ ዋና ከተማ ገባሁ።

ጥያቄ፦ በእዉነቱ አቶ ገዛኢ በጣም ለጀሮ እና ለሕሊና እጅግ የሚከብድ ፍዳ፤ “ዉጉዝ ከመአርዌ” የሆነ ጭካኔ በእርስዎም ሆነ በ ተቀሩት ሕዝባችን የደረሰዉ የጭካኔ ግፍ፡ የደረሰበዎት ለዓለም ለሰዉ ልጆች ለመንገር ታድለዉ አምላክ አብቅተዎታል። በሌሎቹ የትግራይ በረሃ አካባቢዎች “ጣት” ፈልፍለዉ እየመዘዙ በማዉጣት በሰዉ አንደበት ለመግለጽ ለህዋሳት የሚከብድ የጭካኔ ምርመራ ሲፈጸም ነበር ይባላል። ይህም አርስዎ ከነበሩበት የተለየ ሌላ ሰዋራ ቦታ ነዉ ይባላል፤፡ ይህ ድበቅ ቦታ ያዉቁታል ? ታስረዉበት ነበር?

አቶ ገዛኢ ረዳ፡- የግፉ እና የእስርቤቱ ዓይነት ብዙ ነዉ። ይህ አሁን ይካሄድ ነበር ወይ ብለህ የጠየቅከኝ ጭካኔ ዓይነት እማ ስንቱ ብየ ልዘርዝር ብየ ነዉ እንጂ በእኔም እኮ የደረሰብኝ ሌላ ጭካኔ ያልነገርኩህ ብዙ አለ። እኔን የፍጥኝ አስረዉ ቁጭ ብየ ሲቆፍሩት ያየሗቸዉ ለመቀበርያየ የቆፈሩት ጉድጓድ እንድቀበርበት ከሞት አፋፍ ገብቼበት እንዳየዉ አደርገዉኛል። ያዉም ጉልበቴ በድብደባ እና በምግብ እጦት ደክሞ ስለነበር ጉልበት ስላልነበረኝ ራሳቸዉ ቆፈሩልኝ እንጂ፤ ሌላ ጊዜ ግን ራሳቸዉ ሟቾቹ ናቸዉ መቃብራቸዉን እንዲቆፍሩት የሚያዝዋቸዉ። ጉድጋዱን እንደቆፈሩ ፤”እዛዉ ቆይ!” ብለዉ እዛዉ ረሽነዉ አፈር አልብሰዉ ይቀብሯቸዋል። መቸስ ያልደረሰበት ሰዉ- አሁን እየተነጋገርንበት ያለዉን ይህ ሁሉ አረመኔነት “እዉነት አይመስለዉ ይሆናል”” ምክንያቱም ከሰዉ ልጅ ጭካኔ እጅግ ያለፈ ግፍ ስለሆነ ‘መቀበል ያዳግተዋል። በተለይም ከራሱ አብራክ የወጡ የገዛ ልጆቹ በወላጆቻቸዉ እና በጎረቤቶቻቸዉ ይህ መሳይ ግፍ ሲፈጽሙ ያላየ ሰዉ ማመን ያዳግተዋል። ነገር ግን ግፉ በተግባር በእኔም በሺዎቹ የተፈጸመ ነዉ።ለምሳሌ እኔ በእሳት ብቻ ሳይሆን በፈላ ዉሃ ሳይቀር እየደፉብኝ ግፍ ተፈጽሞብኛል። እንደነገርኩህ ለእርድ እንሚቀርብ በግ እግሬን ከጣራ ጋር አስረዉ ጭንቅላቴን እና እጆቼ ዝቅዝቅ አንጠልጥለዉ እግሮቼ በጎማ ጠብጥበዉ ክፉኛ አሰቃይተዉኛል። ይህ ሁሉ ካደረጉ በሗላ መጨረሻ ነገ ስለምንገድልህ- (ነገ ስለምትሰዋ) ኑዛዜ ለቤተሰብህ ጻፍላቸዉ አሉኝ። እኔ የምጽፈዉ ኑዛዜ የለኝም፡ አለኩዋቸዉ።ለምን? አሉኝ። እኔ ያለችኝ ባለቤቴ እንዲት እቤት ያለችዉ እሷ ብቻ ነች፡ በለቤቴም የማታዉቀዉ ሌላ የምስጢር ኑዛዜ የለም፦ልጆቼም ያሉኝ እነሱ ብቻ ናቸዉ እና ከዚህ ዉጭ ልዩ ኑዛዜ የለኝም፤ የምጽፍበት መክንያት የለኝም አለኩዋቸዉ። ንብረት በሚመለከትም ቢሆን ልጆቼ የምታስተዳድርባት ሆቴል አለችን፤ከዚህ ዉጭ ምንም የተደበቀ ለኑዛዜ የሚያደርስ ምስጢር የለኝም አለኩዋቸዉ። እንደገና ሊደበድቡኝ ማስፈራራት ቃጣቸዉ። ነገር ግን አልደበደቡኝም።

የሆኖ ሆኖ ነገ መስዋዕት መሆንህ ስለማይቀርልህ ከመገደልህ በፊት ብትጽፍ ጥሩ ነዉ ካልሆነም መገደልህ አይቀርልህም ሲሉኝ፡_ እኔም ይህች አሁን ያልኩዋትን በወረቀት ጽፌ ሰጠሗቸዉ። ያኔ ሌሊቱን “ሳዝን” “ጸሎት- ሳደርስ” “ሳለቅስ” ነኝ ያደርኩት እና ጥዋት በማግስቱ አቶ ገዛኢ ረዳን ይቀስቅሷቸዉ፦ ብለዉ አስቀድሜ ተገደሉ ብየ ስማቸዉ ካነሳሑዋቸዉ ሰዎች ዉስጥ አንዱ የሆኑት አቶ አበበ ገብረማርያም የተባሉ እኔን እንዲቀሰቅሱኝ አድርገዉ ቀሰቀሱኝ። ያኔ ሌሊት ተአምር የተሞላበት ሕልም አይቼ ነበር። ህልሜን ብነግርህ ይቻላል?

ደጀን፦ አዎ! ይቀጥሉ፦

አቶ ገዛኢ ረዳ፦ እሺ። አንድ የካህን ጥምጣም ያደረገ ግርማ ያለዉ ቄስ፡ በጣም ነጭ የሆነ ጋቢ ነጠላ ደርቧል። ከታሰርንበት ቦታ ካጠገቧ ኣንድ ትንሽ ተራራ የምትመስል ዳገት ነገር አለች። በዛች ዳገት ቁልቁል ወደ እኛ ተጣድፎ በመዉረድ፡ አኛ ታስረንበት በነበረዉ አስር ቤት መስኮት አንገቱን ብቅ አርጎ በማስገባት “ዝም በል!ግድየለም ትወጣለህ! አለኝ። ያን ጊዜ ይሄንን ቃል ስሰማ “አይ ጊዜዉ አጭር ነዉ፤ጊዜ የለም ሰዉ የለም፤ አሁን ታዲያ በመጨረሻዋ ሰዓት በምን ተአምር ከሞት አፋፍ ልድን እችላለሁ አምለኬ ሆይ? ብቻ ስልጣንህ እና ተአምራትህ ሰፊ ነዉ እና ሕይወቴ ባንተ ስር ነች፡ ከሞትኩም ነብሴን ተረከባት ከዳንኩም ተአምራትህ ብዙ ነዉ ላንተ የሚሳነዉ የለም “ተአምራትክን ለዓለም እነግራለሁ“ብየ ትንሽ ስለደከመችኝ “ዓይኔን ገርበብ አድረጌ እንቅልፍ ሊወስደኝ ሲል “አበበ! አበበ! ቀሰቅሰዉ ቀስቅሰዉ!! አሉዋቸዉ አቶ አበበን። እኔም ስለሰማሗቸዉ፤ እሺ ግዴላችሁም እነሳለሁ ብያቸዉ ተነሳሁ። “ስትገድሉት ልብሱን ግፈፉት/አስቀሩት። ሱፍ ልበሱን ጓዶች ወደ ዉጭ አገር ለስራ ሲሄዱ / ከሰዉ ጋር መገናኛ እንዲሆናቸዉ ልብሱን አስቀሩት፡ ይጠቅመናል።” ብለዉ ልበሴን ከላየ ላይ ለመግፈፍ ወስነዉ እንደነበር አንዲት ታጋይ ነግራኛለች። ሊገድሉኝ ሲያስነሱኝ ልብሴን ከሰቀልኩት ቋት ለማዉረድ ስሞክር “ተወዉ! ተወዉ!” አሉኝ። እኔ ደግሞ “እቺን ልብሴን ከገላየ በደም ታጥባ ትወስዷት እንደሆነ እንጂ ከቶ በምንም ተአምር አልሰጣችሁም ብየ እልክ ያዘኝና “አይሆንም አልሰጥም!” አልኳቸዉ (ሞት ላይቀረኝ!)። ሞት አይቀረኝም እና ብየ አልተለማመጥኳቸዉም!! ልብሴም ቀደም ብየ እንደነገርኩህ ፤ከአዲስ አበባ አስሰፍቼ ያመጣሁት ለሕዳር ጽዮን ለብሼዉ እንድዉል ወደ አክሱም በዓሉን ለማክበር ቤተክርስቲያኒቱን ለመሳለም ስጓዝ ነበር የያዙኝ። እምቢ ብያቸዉ ልብሴን ኮቴን ብቻ ያለ ከነቲራ ያለ ክራባት እና ሸሚዝ ለብሻት እንደለበስኩዋት ወደ አንድ ስምጥ ሸለቆ ወሰዱኝ። መቃብርህ ቆፍር አላሉኝም። አኔ በወቅቱ እንኳን ጉድጓድ ለመቆፈር ነብሴ አልቋል። ትንሽ ቀላል ዕቃ እንኳ ለማንሳት አቅም የለኝም።ግን መቃብሬን እራሳቸዉ ጉድጓዱን ቆፈሩት። በዛ ወቅት- እጆቼ የፍጥኝ በጣም በሃይል አጥብቀዉ ስላሰሩኝ “ጣቶቼ እና ጥፍሮቼ ደም ስለቋጠሩ፡ይነዝረኝ፡ይጠዘጥዘኝ ጀመር። ዓይኔ ሊወጣ ልቡ ሊፈነዳ ትንሽ ስለቀረኝ ስቃዩን ስለበረታብኝ መግደላችሁ ላልቀረ ትንሽ ከስቃዩ እንዳርፍ “እጆቼን ትንሸ ላላ” አድርጉልኝ አሉኳቸዉ። ከታጋዮቹ አንዱን ስሙን ጠርቼ፤ ‘እባክህ “መሰለ” ገመዱን ከእጆቼ አላላልኝ’ ብየ ስለምነዉ። “መሰለ ወልዱ” ይባላል “የዓድዋ ልጅ ነዉ””። እባክህ በፈጣሪ ስለዉ “አንተ ሰዉ! አንጀትህ በካራ ብንጫወትበትም ከእንግዲህ ወዲህ ሕይወትህ ምን ይረባሃል?፤አሁን መሞትህ ነዉ! አሁን ታርፈዋለህ፤ትገላገላለህ መቀበሪያ ጉድጓድህ እየቆፈርነዉ ነዉ! -ጉድጓዱ ያዉም ጉልበት የለህም ብለን እንጂ አንተ ነበር መቃብርህን መቆፈር የነበረብህ፤ ግን ትልቅ ሰዉ ነዉ ብለን አክብረንህም ነዉ”” አለኝ፡ እኔ ደግሞ፤-ካከበርከኝ ጥይት ከማርከፈከፍህ በፊት እጄን ላላ አድርግልኝ አልኩት። ቆፍረዉ ሲጨርሱ- ጠሩኝ። ወደ ጉድጓዱ ወስደዉ “ግባ!” ብለዉ ከተተኝ። እጆቼ የሗሊት በመታሰሩ ቁጭ ማለት ስለማልችል ጀርባየ የጉድጓዱን ግድግዳ አንዲደገፍ ወደ ጥግ እንድጠጋ አስተካክለዉ ራሳቸዉ አስጠጉኝ። ሃይማኖተ ቢሶች ስለሆኑ፤ ጸሎታቸዉ “ዝክረ ሰማዕታት” የሚሉት ነገር አላቸዉ፡ “ሰጥ በል/ተጠንቀቅ ብለዉ “ዝክረ ሰማዕታት” አድረገዉ “አንገታቸዉ ሰበር በማድረግ የፊት ግምባራቸዉ ሁሉም ወደ መሬት ደፋ ደፋ አደርገዉ ጸጥ ሲሉ ፦ እኔምአቡነ ዘበሰማያት ትቀደስ ስምከ ትምጻእ መንግስትከ ለይኩን ፈቃድከ” ብየ የግል ጸሎቴን ለማድረስ ስጸልይ “መሰለ ወልዱ” የተባለዉ ታጋይ “ምንድነዉ የሚለፈልፉት?” አለኝ። “አምላኬ ንጹህ ነኝ እና በንጽህናየ ተቀበለኝ” ብነዉ ጸሎትየን ለፈጣሪየ እያደረስኩ ያለሁ”። አልኩት። እሱም “ ዞር በል! በማለት ቀለደብኝ እና ተመልሶ አንገቱን ወደ መሬት በመቀልበስ “የነሱን ሃይማኖት “ዝክረ ሰማዕታት” ጸሎቱን ለመጨረስ አንገቱን ሲደፋ “ አለምሰገድ” የተባለ ታጋይ እየሮጠ ከሩቅ “መሰለ! መሰለ! መሰለ! አትግደሉት ይቆይ! ይቆይ! ምርመራ ገና ይደረጋል እና አቆዩት አትግደሉት አቁሙ! ብሎ ከሩቅ በሩጫ እየተጣራ መጣ። ከጉድጓዱ አስወጡኝ።

በወቅቱ ሸሬ እንዳስላሴ ከተማ የጎረቤቴ ልጅ የሆነ “ወዲ ሊላይ የሚሉት “ንጉሰ ሊላይ” የሚባል ወጣት በደህና ጊዜ እሱ እና ጓደኞቹ ተማሪዎች ሆነዉ ለሕዝብ ትያትር ሲያሳዩ እኔም ፎቶግራፍ በማንሳትም ሆነ የወጣቶች ስፖርት ክላቦች ለማዳበርም ገንዘብ ሲፈልጉ እየረዳሁ ወጣቶቹን ሳበረታታ ስለነበር ፦በዚያ ጊዜ ልጁ ያከብረኝ እና እንደ ወላጁ ሲያየኝ ስለነበር ፡_ ከሚገርመዉ ነገር ሊረሽኑኝ “ኡዚ ጠመንጃ” ይዞ ከተመደቡት ዉስጥ አንደኛዉ “ንጉሰ ሲሳይ” ስለነበረ፡ ወዲያዉኑ አለምሰገድ የተባለዉ ታጋይ “አቁሙ! ቆዩ!” ሲላቸዉ ወዲያዉኑ ንጉሰ ወደ ጉድጓዱ በመግባት ገመዱን ከእጄ ሊፈታልኝ ሲሞክር፦ የተቀሩት ገመዱን በካራ ቁረጠዉ፤በጥሰዉ! ብለዉት ገመዱን በካራ በጥሶ ከፈታኝ በሗላ “ታጋዮቹ በሙሉ ፊታቸዉ እንደ ብርሃን ወጋገን ሲበራ አየሁዋቸዉ”።ግዴታ ስለታዙ አንጂ ከዉስጥ የኔን መረሸን እንዳልወደዱት ከሞት ስድን ያሳዩት እፎይታ ለመረዳት ችያለሁ።በሗላ ወደ ጣብያችን መልሰዉ ወሰዱኝ። ምነዉ ስላቸዉ “ሌላ ምርመራ እናደርገልሃለን እና ትቆያለህ፡ ሲሉኝ “ለምን ገድላችሁ አትገላግሉኝም እና ከዚህ መከራ ልገላገለዉ” አልኳቸዉ።

ታሪኩ በጣም ዘግናኝ እና ረዢም ነዉ። እና የጠየቅከኝ ጥያቄ ልክ ነዉ በእያንዳንዳችን የተለያዩ ፍዳዎች ተፈጽመዉብናል። ለእኔም እንደዚህ ዓይነት ስቃይ አድርሰዉብኛል፡ለማለት ነዉ።አነዚህ ሰዎች “የትግራይ ሕዝብ ጠላቶች ናቸዉ፡ ርሕራሄ የሚባል የማያወቁ የቤተሰብ የዘመድ ወዳጅ የባህል የሃይማኖት ጠላት አረመኔዎች ናቸዉ።

ጥያቄ፦ ክብር አቶ ገዛኢ፤ የትግራይ ሕዝብ ሃይማኖተኛ፤ ህግ አክባሪ በአርአያ ስላሴ የተፈጠረ ፍጡር በሰዉ እጅ መገደል ነዉር ነዉ የሚል ማህበረሰብ ነዉ። እኔም ሆንኩኝ አብረዉኝ ያደጉት ጓደኞቼም ጭምር የተማርነዉ ታላለቅ ሰዎች ወላጆቻችሁ አዛዉንትን ሃይማኖታችሁን አክብሩ ሲሉ ነዉ ያስተማሩን-ትምርት ቤትም ገብረገብነት ስንማር የተማርነዉ የምናዉቀወ ባህላችን ነዉ።እነዚህ አሁን በእንደዚህ ዓይነት አረመኔ ስራ የተሰማሩ ትላለቅ አዛዉንት አባቶች በእሳት የሚጠብሱ ደፋሮች ከየት እንደበቀሉ ለራሴ ይገርመኛል? ይሄ ጉድ ስሰማ “እነዚህ ሰዎች እዉን ከትግራይ የበቀሉ ናቸዉ? ብየ እጠይቅና፤ የኛ ናቸዉ ብየ አፌን ሞልቼ ለመናገር ዛሬ ያዳግተኛል። ሞሶሎኒ እንኳ እረስዎ ከደረሰበዎት አረመንያዊ ጥቃት በላይ አልፈጸመም። ይሄ አረመኔ ስራ ሲደርስበዎት “አነዚህ “ከትግራይ ሕዝብ አብራክ የወጡ ናቸዉ፤ የኛ ናቸዉ” የሚል በሕሊናዎ ያድርበዎት ነበር?

አቶ ገዛኢ ረዳ፡- በእዉነቱ በወቅቱ ይህ ዓይነቱ ጭካኔ ሲደርስብን አንኳን ከትግራይ የተገኙ ወጣቶች ናቸዉ ለማለት ቀርቶ ሰዉ መሆናቸዉም ተጠራጥረን “ከጋኔል ከሲኦል ወደ መሬት የሰዉ ልጅ ለመከራ እንዲዳርጉ የወረዱ አጋንንት ናቸዉ ነበር ያልናቸዉ። እንኳን እና የኛ ናቸዉ፤የእነ እገሌ ልጆች ናቸዉ ለማለት ቀርቶ በተአመር ወደ መሬት የወረዱ መናፍስት ነበር የምናስባቸዉ። እነሱን ስናይ እያንዳንዱ አስረኛ የሚያሳየዉ ጭንቀት ፍርሃት (ነብሰከ ታአምር ቀታሊሃ) - ልክ አንደ ጋኔል ነበር የሚታዩን። የሰዉ ባሕሪ ርቋቸዉ ስለነበር ሰዉ ፍጡራን አልነበሩም። በቃላት ለመግለጽ በጣም ያዳግታል። የነሱን ጭካኔ ለመረዳት በጭንቁ ውስጥ ካላለፉበት በቃላት ለመግለጽ በእወነቱ ይከብዳል።

ጥያቄ፦ ይህ ሁሉ ግፍ ሲያሰልፉ፡ ጉድጓድ መቃብርዎ አይተዉ ገብተዉ ወጥተዉ አሁን ወደ ሗላ መለስ ብለዉ ሲመለከቱት ይህ ሁሉ የመንፈስ ብርታት ከየት አገኙት ጭካኔዉን ማስፈራራቱን አንዴት ሊቋቋሙት ቻሉ?

አቶ ገዛኢ፡- መቸም አነሱም ብዙ ጊዜ ይነግሩኝ ነበር ፡ ምን ብርቱ ሰዉ ነህ ይሉኝ ነበር። ብዙ ተደራራቢ ጭካኔ ደርሶብኛል። በአምላክ ብርታት ብርታቱን ሰጥቶኝ ነዉ የተረፍኩት። ምግብ እንኳ የምነበላዉ ምግብ “ምግብ አይምሰልህ!”፦ እንጀራ እንዳይመስልህ- አነሱ ራሳቸዉ ጋግረዉ ነበር የሚያመጡልን። ደረቅ ነዉ። አፈር የነካዉ ነገር ነዉ፡ ከላዩ ላይ አፈሩን ምኑም በእጃችን እያነሳን እየለየን ነዉ የምንገምጠዉ (እንጀራ አይሉት! ቂጣ ነገር አይሉት!) እንደ ዋልካ/ዋለሃ “ድንኩል” ነገር ነዉ። እጅህ ላይ እያለ ይፈረካከሳል። ላምባ ስለሚጨምሩበት፤ ስትቀምሰዉ “ላምባ፤ላምባ ይላል””። ወጡ “ሽሮ” አይይደለም፦ የሟሽላ ዱቄት ነዉ። ጨዉ እና በርበሬ ተጨምሮበታል።እሱን እንደ ወጥ ስለሚሰጡን “ተቅማጥ” ይለቅብሃል። ይሄ ዓይነት አመጋገቡም “ሆን ብለዉ” እኛን “ለመቅጣት” የሚያደርጉት ነዉ። ይህ ሁሉ ሲመግቡን፦ አብረዉን የነበሩ ወንድሞቻችን ሲገድሏቸዉ፤ በሚቀጥለዉ ማታ ወይንም ነገ የኔ “ተራ” ትሆን? እያልን በፍርሃት በጭንቀት ስለምንኖር “ስለምግቡ አስከፊነት” ብዙም የምናስብበት አልነበረም። ጭንቀታችን “መቸ ይሆን የኔ ዕጣ?” ነበር ቀዳሚዉ ጭንቀታችን። እኔ ከዚህ ሁሉ መዓት እወጣለሁ ብየ አልገመትኩትም። ከሞት ጉድጓድ ፈትተዉ ሲያስወጡኝም ታጋዮቹ “አንተ ምን ዓይነት ወፍራም ቆዳ ነዉ ያለህ? ከፊትህ ፍርሃት ለምን አታሳይም? ሌሎቹ ታጋዮቻችን ሳይቀሩ ለመገደል እየተገፉ ሲሄዱ “እያለቀሱ! እየተማጠኑ! ነዉ የሚሞቱት አንተ ግን ልዩ ነህ፤ አእምሮህም እንደተቀሩት አልሳትክም” እያሉ እነሱ ራሳቸዉ ሳይቀር ይገረሙ ነበር። ሆኖም ነገሩ አልሞትኩም ብየ አልዋሽም! ሆኖብኝ ነዉ እንጂ “ሰዉነቴ ሁሉ አልቋል፡ተጎሳቁያለሁ፤በእሳት ነበልባል ተለብልቤአለሁ” እንድሞት ብቻ ነበር የምለምናቸዉ።

ጥያቄ፦ እንደገና ቀደም ብየ ልጠይቀዎት አስቤዉ የነበርኩት ሌላዉ ሊያስረዱን የፈለግኩት የወያኔ ዕስር ቤቶች ግፍን በተመለከተ፤ ነፋስም ሆነ የጻሃይ ብርሃን የማይገባበት የጉድጓድ እስር ቤቶች እንደነበሩ የተለያዩ የራሳቸዉ ታጋዮች ይናገራሉ።በእነዚህ ጉድጓዶች ትላልቅ አዛዉንት ወጣቶች በቅማል እና በሌላ ለመሳሰሉት ጨካኝ ስቃይ ተዳርገዋል ይባላል። አርስዎ ስለዚህ የሚያዉቁት ነገር አለ?

አቶ ገዛኢ፦ አዎ አለ። የጉድጓድ እስርቤቶች በብዛት እኔ በነበርኩበት ምዕራባዊ ቆላ አካባቢ አልነበረም። ነገር ግን በጎንደር አካባቢ “ቃሌማ” ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ልዩ የጉድጓዱ መጠርያ “ግህንም” (ጋሃነብ) የሚባል በረሃ አለ። አዚያ ዉስጥ ለዉስጥ የተቆፈሩ ጉድጓድ እስር ቤቶች እንዳሉ እንሰማ ነበር። ሌላዉ በተከዜ አካባቢም እንደዚሁ ተፈጥሮ የቆፈራቸዉ ጭለማማ የሆኑ አለታማ ሰፋፊ ጉድጓዶች (ባዓቲ- ምሽጎች) ዉስጥ ሰዎች የታሰሩበት እንደነበሩ እንሰማለን። እንደምነሰማዉ፦በአካባቢዉ ስትደርስ ከእላይ ሆነህ በእግርህ የምትረግጠዉ መሬት ከስሩ የጉድጓድ አስር ቤት መኖሩን አታዉቅም፡ጭራሽ አያስታዉቅም ሲሉ እንሰማለን። የጉድጓድ አስርቤቶቹ በጥበብ እንደማይነቃባቸዉ ተደርገዉ ነበር የተሰሩት። በተምቤን አዉራጃ ዉስጥም እንዳላቸዉ ይነገራል። አዎ- ግብረ ክፋት-ጭካኔ ሲፈጠር አብሮአቸዉ የተፈጠረ ነዉ የሚመስለዉ። ስራቸዉ ሁሉ አያስታዉቅም።

ቅማልን በተመለከተ፦በቅማል መሰቃየታችን እኔ ብቻ ሳልሆን አስረኛ በሙሉ ተሰቃይቷል። መተኛት መቀመጥ ማረፍ አትችልም።ሌት ተቀን መፏከት ነዉ።ሰዉነታችን ልብሳችን በቅማል ተወሯል። ሰዉነታችን ጸጉራችን ቅማል ተልቶ ወደ መሬት ይንጠባጠባሉ። እግዚኦ የሚያሰኝ ስቃይ ነዉ። የቅማል ነገር ሲነሳ በዛዉ ላይ ቁስላችን በእሳትም በፉል ዉሃም በግርፋት ድብደባም ያመረቀዘም ያላመረቀዘዉም ደም የሚተፋዉ ቁስላችን ላይ ቅማሎቹ ተልተዉ ተጨምረዉበት ሲበሉን፤ሲያሳክኩን ስቃዩ አይጣል ነዉ።

በዚህ አጋጣሚ ላመሰግናት የምፈልጋት “ታጋይ ለምለም ገሰሰዉ” የተባለች የአቶ ገሰሰዉ አየለ (ስሑል) (ወያኔን ከመሰረቱት አንደኛዉ) የተባለች ልጃቸዉ ድሮ እንዳስላሴ ሽሬ ከተማ ዉስጥ ከቤተሰቦቻም ጋር ትዉዉቅ ስለነበረን በታጋዮች ዘንድ ተወዳጅም ስለነበረች ፤እሷ በነበራት የዋህ አዛኝ ልብ እና አስተዋይ ሕሊና ወደ እሰር ቤቱ እየመጣች በቅማል የተወረረዉ ከናቴራየ እና ጸጉር ራሴ ጸሀይ ላይ አዉጥታ በመቅመል እና በማስጣት እጅግ ሰብአዊ ርሕራሄ በማሳየቷ፤ በእዛ በጭለማ በክፉ ጊዜ እንደዚህ ዓይነት አስገራሚ ሰብአዊ ዕርዳታ ስላደረገችልኝ ምስጋናየ በዓለም ሕዝብ ፊት ሳመሰግናት እወዳለሁ። በእዉነቱ ድሃ ሆኜ እጄ በማጠሩ እንጂ ብድሯን ለመመለስ ምን እንደማደርግላት አስካሁን ከባድ ሸክም ሆኖብኛል። ድንገት በዚህ ዓለም ካለች እና የምታዉቋት ሰዎች ካላችሁ- በዚህ አጋጣሚ “ምስጋናየን አድርሱልኝ” ።በጣም ፤በጣም ዉለታዋ እግዚአብሐር ይክፈላት።ወለታዋ አስካሁን አልረሳዉም! እና የቅማሉ ነገር ከልክ ያለፈ ስለነበር አይወራም ብሎ ማለፉ ይሻላል።

ጥያቄ፦ በወቅቱ ልጆች ነበሩዎት?

አቶ ገዛኢ ረዳ፡- አዎ ትንንሽ ሦስት ልጆች ናቸዉ። ግፋ ቢል ዕድሚያቸዉ ከ7 ዓመት አይበልጥም።

ጥያቄ፦ ሕጻናት ያለ ጧሪ እንዲያድጉ፤ አባታቸዉ ከመንገድ ጠልፈዉ ወደ በረሃ ወስደዉ ፤ህጻናት ያለ አባት አስቀርተዉ፡ የልጆች አባት በእሳት መጥበስ፤መበደል፤ግፍ መፈጸም ነዉሩነቱ ወያኔዎች አልታያቸዉም። ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈጽሙ እነዚህ ሰዎች ነጻ እናወጣለን የሚሉት ማንን ነዉ። ምንስ እያሉ ነበር በወቅቱ ስብከት የሚያሰሟችሁ?

አቶ ገዛኢ ረዳ፦ ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ የትግራይ ህዝባችንን ከጨቋኙ ከአማራ ነጻ ለማዉጣት ነዉ ።ትግላችን ጸረ-አማራ፤ጸረ መሳፍንት ስርዓት ነዉ። ሕዝባችን ነጻነት ለማዉጣት ነዉ። ይሉን ነበር።

ጥያቄ፦ የ7ዓመት ዕድሜ ከዚያም በታች የሆኑት የታዳጊ ህጻናት አሳዳጊ አባት ከመንገድ ጠልፈዉ ሲለዩዋቸዉ፤ እነሱ ከሚሉት ነጻነት ቅራኔ አልገባም ወይ?

አቶ ገዛኢ፦ አዎ! በእርግጥ ይጻረራል እንጂ። ለነጻነት የቆመ ሃይል “ልጅ ከወላጁ” “አባት ከህጻናት ልጆቹ ከሚሰቱ” ጠልፎ ወስዶ ለስቃይ መዳረግ እነሱ ከሚሉት የነጻነት ትርጉም የተለየ ነዉ። ሰብአዊ ፍጡር በእሳት መቀቀል በፈላ ዉሃ ማሰቃየት የሰዉ ልጆች ነጻነት የሚጻረር ነዉ። የልጆች ጉዳይ ካነሳህ ላይቀር አንድ ታሪክ ልጨምርልህ። አስረኛዉን ለመግደል ሲፈልጉ፦በነጻ ተፈትተህ ወደ ቤትህ እንለቃሃለን፡ ትሄዳለህ ይሉዋቸዉ እና፡ ዉሃም ሻሂም ይሰጡዋቸዋል። ከእስር ቤቱ አስወጥተዉ ራቅ ያለ ከሰዉ ዕይታ ትንሽ ሰወር ካለዉ ጎድጓዳማ ስፍራ ይወሰዱ እና በራሳቸዉ በአንገታቸዉ ላይ የሚያጠልቁት ከአቡጀዲ የተሰራ ከረጢት የስገቡላቸዋል። ዓይናቸዉ ዓያዩም፡ በከረጢቱ ይሸፍኗቸዋል። ሁሉንም በራሳቸዉ የምትገባዉ ከረጢት አስገብተዉ አንገታቸዉ ላይ ይቋጠራል። ዓይናቸዉ፤አፋቸዉ፤ ፊታቸዉ እንዳለ በሙሉ ይሸፈናል ማለት ነዉ። ተር…እንዲሉ በመደዳ አሰልፈዉ ያስቀምጧቸዋል።ከዚያ ይረሽኗቸዋል።ከመገደላቸዉ በፊት ግን ለእስረኛዉ እና ለአካባቢዉ ኗሪ አስረኞቹ እገሌ እገሌ ነገ ጥት ወደ ቤቱ እንለቀዋለን በማለት ያስወራሉ። ከእሰር ሲወስዷቸዉ ሻይ ዉሃ መንገድ ስንቅ እንዲሆንህ ብለዉ ነዉ ከሰዉ ፊት የሚሰጡት። እንግዲህ አስረኛዉ ወደ ከተማ ድንገት ቢለቀቅ እነ እገሌ የት ደረሱ ተብለዉ ሲጠየቁ ፡እሱ እማ ከተፈታ ቆይቷል” በማለት ያልሆነ ወሬ ለሕዝቡ እንዲሰራጭ ለማድረግ እንዲያመች ነዉ።

ላንዳንዶቹ ደግሞ ወደ ትግል ፈቅጄ መስዋዕት ለመሆን ስለወሰንኩ፤ ከአገሬ ከሕዝቤ በላይ ምንም ነገር የለም እና ግማሹን ንብረቴን ላንቺ አስቀርተሽ ግማሹን ለምታገልለት ድርጅት ለህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ በምስጢር እንድታስረክቢአቸዉ በማለት ሟቹን በግድ አስገድደዉ ደብዳቤ እንዲጽፍ ያደርጉታል። ያችን ደብዳቤ ይዘዉ ሄደዉ ከተነጋገሯት በሗላ ቀጠሮ ይዘዉ ዕቃዋን አንዳለ ግማሹን ንብረት ይወስዱታል። ማንኪያ ሳይቀር ይወሰዳሉ።ብረት ድስት፤ ምንም የሚቀራቸዉ ነገር የለም።ይሄ ለሚረሽኑት ሰዉ ሲሆን ነዉ። ወደ ኢዲዩ ወደ ደርግ ወደ ማንም ድርጅት ገብቷል ከተባለ ወደ ቤቱ ሄደዉ ያለዉን ንብረት በሙሉ ሙልጭ አደርገዉ ወስዱታል።ከብቱ ፍየሉ ምኑ ምናምኑ እንዳለ ይወስዱታል። ህጻን ልጅ ሚሰት አለዉ አይሉም።ለባለቤቱ ድርሻዋ የሚባል ነገር የለም፤ እንዳለ ይወረሳል።

ለምሳሌ ዓዲ ሓገራይ በተባለ አካባቢ ገ/ጻድቕ ጽጌ የተባለ ወጣት ገበሬ (ሐኔታ ጽጌ ይባላሉ ወላጅ አባቱ የአዲያቦ ኗሪ ናቸዉ) ወንድሙ ሐኔታ አስመላሽ ጽጌ ወረዳ ገዥ ነበሩት። ትዉልዳቸዉ“ኤርትራዉያን ናቸዉ ነገር ግን ዕድመያቸዉ በሙሉ አድቦ ዉስጥ ነዉ የኖሩት ሁሌም የተከበሩ ኢትዮጵያዉያን ናቸዉ።ገብረጻድቕ የጭነት መኪና አለዉ፤በጣም ሃብታም ገበሬ ነዉ። ገብረጻድቕ ጽጌን ወስደዉ ረሸኑት። አሱን ገድለዉ፤ወደ ቤቱ ሄደዉ ንብረቱን ግማሽ ወሰዱት።ከግማሽ ንብረቱ መወረስ በላይ ባለቤቱን እቤቷ ድረስ ሄደዉ $12,000 (አስራ ሁለት ሺሕ ብር ክፈይ አልዋት። አሁን በእጄ $6,000 ብር ብቻ ነዉ ያለኝ እና ተበድሬ ልከፍል ጊዜ ስጡኝ ስትላቸዉ፤ አሁኑኑ ካልከፈልሽ አብረሺኝ ከእኛዉ ጋር ወደ በረሃ ትሄዳለሽ ብለዉ አስገድደዉ ወሰዷት። ሲወስዷት በሰዉ መልእክት ልካ ተበድራ የጠየቁትን $12,000 (አስራሁለት ሺሕ ብር) ከፈለቻቸዉ። ከዚህ በላይ ቆላ በራሃ ዉስጥ የነበሩት ወደ 500 የሚጠጉ ከብቶቹ፤ላሞቹ በሙሉ ሰብስበዉ ወሰዷቸዉ። ለወደፊቱ ታሪኬን ለማስቀመጥ ያግዘኛል ብየ የያዝኩትን በግል የመዘገብዩት ማስታወሻ አንድ ቦታ ተወሰደብኝ እንጂ አሁን በአእምሮየ ያልያዝከኳቸዉ በሰዉ ልጆች ላይ የፈጸሟቸዉ ግፎች ብዙ ነገሮች እነግርህ ነበር ።

ጥያቄ፦ አርስዎ ክፈል የተባሉት $15፣000 ብር ከፍለዉ ሲለቀቁ ከእነሱ ጋር በምን ተለያያችሁ?

አቶ ገዛኢ ረዳ፦ አንድ ማሃላ ነበረኝ። ከእንደዚያ ዓይነት ጭካኔ እና ግፍ በሗላ ከአንግዲህ ወዲህ የሰዉ ልጆችም ሆኑ እኔ ሰላም የተሞላበት ኑሮ እንኖራለን የሚል ሃሰብና ግምት በኣእሙሮየ ጭራሽ አልተቀረጻም። የኔ አላማ- ባለቤቴን እና ልጆቼን ዓይን አይቼ እነሱን ተሰናብቼ ፤ናፈቆቴን ገልጨ እነዚህ በትግራይ ሕዝብ ሕየወት የሚቀልዱ አረመኔዎች ለመፋለም ቁርጥ አላማ ያዝኩ። ሕሊናየ በፍጸም ዕረፍት ሰላም አጣ። ከሲኦሉ እንደወጣሁ ወደ ልጆቼ እና ባለቤቴ ወደ ቤቴ በገባሁባት ቀን ፤መለቀቄን ለአዉራጃዉ አስተዳዳሪዉ ለማመልከት ስሄድ፤ በወቅቱ የትግራይ ክፍለ ሃገር ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት ኮሎኔል ቃለ ክርስቶስ አባይ የተባሉ የትግራይ ሰዉ (በትዉልዳቸዉ ዓድዋ) ከ አዉራጃዉ አስተዳዳሪ ጽ/ቤት አብረዉ አገኘሗቸዉ። ያኔ በወሬ መምጣቴን ሰምተዉ ስለነበር፡ እኔን ስያዩ “እንኳን ደህና መጡ ይግቡ” ብለዉኝ ቁጭ እንዳልኩኝ “እንዴት በትላለቅ አዛዉንቶች አዋቂዎች የህጻናት ልጆች አባት እንደዚህ መሳይ ጭካኔ ይፈጸማል? ለሕዝብ እንቆረቆራለን እያሉ ይህ ዓይነት አረመኔ ስራ በኗሪዉ ሕዝብ ላይ ሲፈጽሙ በጣም ለህሊና ይከብዳል!” ብለዉ ኮለኔሉ አዘኑ።የደረሰብኝ ስነግራቸዉ፤ በጣም ነበር ያዘኑት። ከዚያ በሗላ ኮሎኔሉ ያመጣቸዉን ጉዳይ ለማከናወን የከተማዉን ሕዝብ ስብሰባ ጠርተዉ በማግስቱ ሲያነጋግሩ፤- ኮሎኔሉ “ንግግራቸዉ እንደፈጸሙ የተወደዳችሁ ወንድሞች እህቶች ሆይ፦ የዚህ ከተማ ኗሪ የሆኑ አቶ ገዛ ረዳ የተባሉ ከናንተ መሃል አሁን ካሉ እባክዎትን ይነሱ” ብለዉ ሲጠዩቁኝ ያኔ እኔ አንድ ነገር በህሊናየ ታወሰኝ። ኮሎኔል ቃለክርስቶስ አባይ የደረሰብኝ ግፍ ለሕዝቡ ገልጸዉ በተጨማሪ እኔዉ ራሴ የደረሰብኝን እንዳበራራ ሲጠይቁኝ፦ እንዳለሰማሁ ዝም አልኩ (ሲለቁኝ ከማንም ሰዉ፤ ደርጅት፤ ግለሰብ፤ ወይንም መንግስት ጋር የደረሰብህ ነገር ብታወራ እርምጃ እንወስድብሃለን ብለዉ ስላስጠነቀቁኝ)። ከ3 ቀን 4 ቀን በሗላ ወያኔዎቹ “የሰጠንህን ማስጠንቀቂያ ባለመጠበቅህ ፤ባንተ ላይ እርምጃ የምነወስድብህ መሆናቸንን እንድታዉቀዉ በማለት ደብዳቤ ላኩልኝ። 450 ብር የገዛሁት የእጅ ሰዓቴን 8ግራምየሚመዘን የአንገቴ ሃብል 23 ግራም የጣት ቀለቤት በሙሉ ከተማ ከገባህ በሗላ ይላክልሃል ብለዉኝ የነበረዉን ንብረቴን አስቀሩት።አልላኩልኝም። ከደብዳቤዉ ላይ የላኩልኝ መልእክት የሚለዉ 1-እርምጃ ይወሰድብሃል 2- የተያዘዉ ወርቅ አንልክልህም- ዉርስ ሆኗል።የሚል በባለቤቴ ዘመድ በሆኑ ሰዉ አስልከዉ እንዲደርሰኝ አደረጉ።ሕይወትህ ከእንግዲህ ወዲህ አትኖርም ስላሉኝ። እኔም ጊዜ እንደሌለኝ እና እነዚህ አረመኔዎች እንደሚገድሉኝ ስላወቅኩ፤ ቤተሰቦቼን ተሰናብቼ የነበረኝን ጠመንጃየን ይዤ ወደ በረሃ ወጥቼ ከኢዲዩ ጋር ተቀላቀልኩ። በወቅቱ የኢድዩ ድርጅት የኔን ሁኔታ ስላወቁ መልዕክት ልከዉ ታጋዮች አስልከዉ ከተማ ዉስጥ ገብተዉ ነዉ ያስወጡኝ።ለመጀመሪያ ጊዜ ዓዲ ዳዕሮ ወደ ሚባል ቦታ ሰቀቀን በሌለበት ሙሉ ነጻነት ተሰምቶኝ ያለፍርሃት ገባሁ። ከዚያ በሗላ ከኢዲዩ ጋር ስታገል ቆይቼ፤ ዓዲ ዳዕሮ ዉስጥ ሰልለዉ ነብሰገዳይ በመላክ በጥይት መትተዉ አቆሰሉኝ።ከእዚያ በሗላ ለሕክምና ወደ ሱዳን ተላክኩኝ።ሱዳን ስታከም፤ ቆይቼ ፤ራስ መንገሻ ሥዩም ከሱዳን ወደ ወልቃይት እንድመጣ አድርገዉ ከዚያም ታጋዩ ወደ ሉግዲ ወደ ሱዳን ጠረፍ እንድዞር ተደረገ። እንዲህ እንዲ ሲል ትግሉ እና ታጋዩ ጠንካራ ቢሆንም መቸስ የአመራር ድክመት ይመስለኛል ሳይሳካ ቀረ።እኛም በየ ዓለማቱ ተበትነን ለስደት ተዳረግን።

ጥያቄ፦ አቶ ገዛኢ፦እንደሚያወቁት የወያኔ ማንነት ከማንኛችንም በላይ አዉቀዉታል።ሕዝባችን እያሉ የሚነግዱበት ሕዝብ ክብር የተጋፉ አዛዉንቶች እና ታዳጊ ህጻናትን እየረሸኑ አገር ያዋረዱ ፡ወላጆቻችን አሉላ እና ዮሃንስ በደማቸዉ ቆስለዉ ሞተዉ ከጥንት ከዘመነ አክሱም ጀምሮ ተከብሮ የቆየዉን የባሕር በራችንን ያስረከቡንን ድምበር፤ ካለሕዝብ ፈቃድ አስገንጥለዉ አገራችን ወደብ አልባ አደረጓት።ዛሬ አገር እና መንግስት ማስተዳደር ተያይዙታል። እነኚህ ሃይማኖት የሚዳፈሩ ጸረ ባሕላችን የዘመቱ ሰዎች ወደ እዚህ ደረጃ ይደርሳሉ የሚል ግምት ነበረዎት?

አቶ ገዛኢ ረዳ፦ አስተዳደር የሚካሄደዉ ሰብአዊ ክብር እንዲጠበቅ ሲደረግ ነዉ። ባህል ሃይማኖት ሲከበር ነዉ። ሰዉን በ እሳትየሚጠብሱ አረመኔዎች ወደ አስተዳደር ችሎታ መገመት ሕሊና ላለዉ ማየቱ ቀላል ነዉ።ሃይማኖት ላልከዉ ታሪክ ላነሳኸዉ ግን አንድ ነገር ማለት እችላለሁ። በረሃ ላይ እያሉ የቤተ ክርስትያን ሰፊ ግቢ መጨፈሪያ አድርገዉት ነበር። ቤተክርስትያን ግቢ ዉስጥ ሺጃራ ያጨሱ ነበር። የገዳማት የቤተክርስትያን ቅዱስ መጋራጃ “እየቀደዱ የጨዉ እና የበርበሬ መቋጠርያ ያደርጉት ነበር” አስሰፍተዉ ልብስ ይለብሱት ነበር።ለምሳሌ ሸራሮ መድሃኒ አለም ቤተክርስትያን ዉስጥ ያለዉ ሰፊ ግቢ እንደዚህ ዓይነት ተግባር ፈጸመወበታል።

ሌላ ቀርቶ ካህናት ቀሳዉስት በግድ ጠመንጃ ታጥቀዉ ወደ ጦርነት እንዲሳተፉ ተደርጓል። ዘፈን፤ጭፈራ ሲደረግ ቄሶቹን ወደ ፊት በማሰለፍ ጭፈራዉ እንዲመሩት ይደረጋል። የሕዝብ ስብሰባም ጭፈራም ቄስ እንዲከፍተዉ ይደረጋል። ካህናት መነኮሳት ክላሽን እንዲታጠቁ ተደርጎ የእግዚአብሄር መልክት ትተዉ በጦርነት ሕይወትን በመግደል ተሰልፈዉ “ቄሶቹ” በቤተክርስትያን ደምብ እና ማዕርግ “ቀሲስ ወይም አባታችን” እገሌ- ከመባል ይልቅ “ጀግኖች” እየተባሉ የሰማዩን ስራ ትተዉ የምድሩን ስራ እንዲሰሩ ተገድደዉ ቀሳዉስት እና መነኮሳት በጀግኖች ተታኳሾች ማዕረግ ሲሰየሙ “የዓለም መጨረሻ- ምጽአተ ዓለም መሆኑነ ነዉ”። የህ ግፍ የሰሩ አሁን አስተዳደር ዉስጥ መንግስት ዉስጥ ገባን ሲሉ በእወነቱ ለሕሊና ይጎረብጣል። ተጋሩ ወላጆቻችን ያገራቸዉን የኢትዮጵያ ዳር ድንበር አስከብረዉ በክብር የቆሙ ባለታሪኮች ነበሩ። እነዚህ ግን የአባቶቻችንን ክብር የረገጡ ጠላቶች ናቸዉ። አሳፋሪ ታሪክ ነዉ የገባንበት ዘመን። ለምን እንዲህ ሊሆን እንደቻለ ብዙ ሰዉ ግራ ገብቶታል። በዘነመናዊ የታሪክ መጻህፍት እና በመጽሃፍ ቅዱስ የተነገረላቸዉ ያገራችን ባለታሪክ የትግራይ ጀግኖች፡ ዛሬ “ታሪክ አፍራሾች” “አገር ሻጮች” “የወላጆቻቸዉ ጀግንነት አራካሾች” እንድንባል አደረጉን። የኢትዮጵያ የትግራይ ድምበር ሕዝቡን ሳያማክሩ በገዛ ፈቃዳቸዉ ሸንሻኝ፤ሰጪ እና ከልካይ ሆነዉ በሕዝብ ታሪክ እና በትግራይ ተወላጆች ስም አስጸያፊ ተግባሮች በመፈጸማቸዉ በምድር ታሪክ እና ይህን ዓለም በፈጠረ አምላክ ፊት ተወቃሾች እና ተከሳሾች ናቸዉ የሚል እምነት አለኝ። ይህ ዕድል ሰጥተህ ጭሆቴን እና ብሶቴን ለዓለም ህዝቦች እንዳስሰማ በማድረግህ እግዚአብሔር ያክብርልኝ። አመሰግናሉ። http://www.Ethiopiansemay.blogspot.com

Tuesday, January 27, 2009

የወያኔዉ ሜጀር ጀነራል አበበ ተክለሃይማኖት እና

የወያኔዉ ሜጀር ጀነራል አበበ ተክለሃይማኖት እና የዓረናዉ ፓርቲ ምክትል መሪ አዉዓሎም ወልዱ የተሳተፉበት ወንጀል ከጌታቸዉ ረዳ ክቡራን የኢትዮጵያ ሰማይ ብሎግ አንባቢዎች፡ ወያኔ የተባለዉ ድርጅትን በከፍተኛ ስልጣን ሲመሩ ኖረዉ በተለያዩ ምክንያቶች ከድርጅቱ የተሰናበቱ እና የተቀሩትም ድርጅቱን በመምራት ላይ የሚገኙ መሪዎች ቀደም ብየ ለብዙ አመታት መቃወሜ ግልጽ ነዉ። የእነዚህ አረመኔ ግለሰቦቹን ማንነት ሳያዉቁ የወያኔ አጨብጫቢዎች በመሆን ግማሾቹ በአምባሳደርንት ግማሾቹ በገንዘብ አዋጪነት ፤ከፊሎቹ በየፓልቶኩ ላንቃቸዉ አስኪደርቅ በስሜት ስለወያኔ ቅዱሳን ሃዋርያትነት በመስበክ ለብዙ ኣመታት ራሳቸዉን ሲያሞኙ ታዝበናቸዋል። እነኚህ ደጋፊዎቻቸዉ ለምን እንደሚደግፉዋቸዉ የተለያዩ ራሳቸዉ ምክንያቶች አሉዋቸዉ። አባት እናት ወንድሞቻቸዉ ገድሎዉባቸዉም “በ ባሪያነት ሙሉ መንፈሳቸዉ ለማገልግል ፈቀደኞች የሆኑ በተለያዩ ምክንያቶች ራሳቸዉን ለወያኔ ሸጠዉ ለማገልገል ያደሩ የዋህ “ዕዉራን ንቦች”በየቦታዉ እንዳሉዋቸዉ የምታዉቁት ጉዳይ ነዉ። በንቅዘት የተበከሉ ወንጀለኞች እና ባንዳዎች የሚመሩት ይህ ድርጅት ለምን እነደሚከተሉት ይየተለያየ ምክንያታቸዉ ያፈለገዉ ይሁን፤ መሪዎቻቸዉ ከሰሩት ወንጀል እና ሰብኣዊ ጥሰት ተጠያቂነት ሊከላከሉላቸዉ የተቻላቸዉን ያህል ታች እና ላይ ቢሉም ፤ከቶዉንም ታሪክ የዘገበዉ አረመኔ የገበና የወንጀል ማህደራቸዉ ሊከዉሏቸዉ ግን አይቻላቸዉም። በቅርቡ የወያኔዉ የአየር ሃይል ኮማንደር/አዛዥ የነበረዉ ጀኔራል አበበ ተክለሃይማኖት (ጆቤ) በረሃ ዉስጥ የወንጀለኛዉ የወያኔ ድርጅት ታጋይ ሆኖ ትግራይ ዉስጥ በሽሬ አዉራጃ በረሃዎች የወያኔ እስር ቤት (ባዶ ሽድሽተ-06) ሃላፊ ሆኖ ተመድቦ ሲሰራ ገበሬዎች ፣ የከተማ ወጣቶች እና አዛዉንት ኗሪዎች በእሳት እየለበለበ ያሰቃያቸዉ የወንጀል ድርጊቶቹ እና በወቅቱ አብሮት ከእርሱ ጋር የነበረዉ የኤርትራ አምባሳደር ሆኖ በወያኔ ተሹሞ የነበረዉ ከመለስ ጋር ከተጣሉ በሗላ ደግሞ የገብሩ አስራት ምክትል የድርጅት ሃላፊ ሆኖ “ዓረና ትግራይ” የተባለዉ ሌላ ብሄረተኛ ቡድን በመምራት ላይ የሚገኘዉ የበረሃ ስሙ “አዉዓሎም ወልዱ” ትከክልኛ ስሙ “ትኩእ ወልዱ” አስረኞችን ከተቀፈደዱበት አስር ቤት እያስወጣ ስም ዝርዝር በመጥራት አስረኞቹን ተሰናበቷቸዉ እያለ በግፍ በመረሸን የሰሩትን ወንጀል ለሕዝብ ይፋ ስለሚሆን እንድትከታተሉን ስናሳስብ፡ በትግራይ ሕዝብ ላይ የተለያዩ ሰብኣዊ ግፎችን ፈጽመዉ ስማቸዉ ለጊዜዉ ለማዉጣት ባለን ምክንየት የተያዙ ስም ዝርዝሮች ስላሉ፤ የሕግ ባለሞያዎችን እስክንፈልግ ድረስ በትዕግስት እንድትከታተሉን ኣሳስባለሁ። በወላጆቻችን ደም ቀልደዉ ሞኞችን ቢአሞኙም “ዛሬ በስመ ዲሞክራሲ እና በብሄረተኝነት”መጋረጃ መደበቅ ለጊዜዉ እንጂ ከታሪክ ግን መደበቅ ከቶ ኣይቻልም። ጌታቸዉ ረዳ የኢትዮጵያ ሰማይ የህዋ ሰሌዳ አዘጋጅ

Tuesday, January 20, 2009

የትግራይ ሕዝብ ሆይ!

የትግራይ ሕዝብ ሆይ! ገዛኢ ረዳ አቶ ገዛ ራዳ፡ ወያነ ትግራይ በእሳት እና በፈላ ዉሃ ሰዉነታቸዉን በማቃጠል ኢሰብአዊ ምርመራ አካሂዶባቸዉ የአካል ጉዳት ከደረሰባቸዉ አንዱ የትግራይ ተወላጅ ናቸዉ። ከእኝህ አባት አዛዉንት ጋር በትግርኛ የተደረገዉ የቴሌፎን ቃለ ምልልስ፤ በቅርቡ ለሕዝብ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ለንባብ ስለሚቀርብ-እንድትከታተሉን እያሳሰብኩ፦ ከዚህ ቀጥሎ አቶ ገዛኢ ረዳ ለትግራይ ሕዝብ ያስተላለፉትን ራሳቸዉ የጻፉትን አጭር መልዕክት ሕዝቡ እንዲያነብበዉ አስተላልፈናል።

የትግራይ ሕዝብ ሆይ! ወያኔዎች ትግራይን ነጻ እናወጣለን በማለት አዛዉንቶችን፤ታዳጊ ህጻናትን፤ የዜጎች እና የአገሪቱን ክብርን በተለያየ መልክ እና በተለያየ ጊዜ የተዳፈሩ መሆናቸዉን ከእንደ እኔ የመሳሰሉት የወያኔ አረመኔ ጭካኔ የደረሰባቸዉ ሰለባዎች የሚሰወር አይደለም።
የትግራይ ህዝብ ሆይ!
ስለ ወያኔዎች አረመኔነት ከእኔ እና እንደ እኔ የመሳሰሉት የዓይን ምስክሮች በላይ ሌላ ሰዉ ሊነግርህ ከቶ አይችልም። ቢሞከርም ሙሉዉን አረመኔ ገበናቸዉ እንደ ራሳችን ሆኖ ጭካኔአቸዉን እና ያደረስቡን ስቃይ ዘርዝሮ የሚያስረዳህ ክፍል አይሆንም።ለዚህም ነዉ ቃሌ ለሕዝብ እንዳስተላልፍና ስሞታየም በአንዳንድ የተባረኩ ኢትዮጵያዉያን የትግራይ ልጆች በኩል እንድታዳምጡት የፈለግኩት።
የደረሰብንን ግፍ ለሕዝብ እና ለዓለም መግለጽ አልቻልንም። ለዓመታት በዉጭ አገር ብንኖርም የደረሰብንን ኢሰብአዊ ግፍ ለዓለም የሚያስተጋቡልን ወገኖቻችን ካሉ በጣም እጅግ ጥቂት እና ከሁለት ሦስት የተባረኩ ሰዎች በላይ አይሆኑም።እነሱን እያመሰገንኩ የተቀረዉ ምሁር ግን በእኛ በዜጎች ላይ የደረሰብን ግፍ ሊመለከትልን ፍላጎቱም ጥረቱም አላሳየም።ለምን?
የትግራይ ህዝብ ሆይ! በስምህ እየነገዱ ነጻ አዉጥተንሃል የሚሉህ ታሪክ አርካሽ ጥቂት ግለሰቦች፤ በጣምኑ ደፍረዉሃል! በጣም ታግሰሃቸዋል። ጀግንነትህ አትንኩኝ ባይነትህ እንዴት አስቀማኸዉ? በሚለዉ ጥያቄ ልጀምር።የሞቀዉ ወኔህንስ እንዴት እና ለምንስ በረደ? ቁጡነትህ እንዴት ዛለ? “ወይ ኣነ!!!) (እኔ ወንዱ!!!) የሚለዉን የቁጣ ስሜትህ ወዴት ጠፋ?
ቆፍጣና ቀበቶህስ እንዴት በእነዚህ ሊላላ ቻለ? ወደ ሗላ መለስ ብለህ በ እነዚህ ጉዶች የተደረጉት ነዉራማ ስራዎች ብታስታዉሰዉ-እጅግ አሳፊሪ ተግባሮች ተፈጽመዋል።ሃይማኖትህ ደፍረዉታል፡ቅዱስ ገዳማት እና ቤተክርስትያናትን የፖለቲካ መስበኪያ፤ የዘፈን እና የመጨፈሪያ መድረክ ሆነዉ ሲራከሱ፡የቤተክርስትያን ቅዱስ መጋረጃ እየተገነጠሉ የጨዉ እና የበርበሬ መቋጠሪያ ሲሆን፤ቀሳዉስት እና መነኮሳት ሲገደሉ፤ ጠመንጃ አንግተዉ በግድ ወደ ጦር ሜዳ እንዲሄዱ እና መንፈሳዊ መመሪያቸዉን እንዲጥሱ ተደርጎ የሃይማኖት ማአዲዎችህ በየምክንያቱ ተመናምነዉ እንዲጠፉ እርስ በርስ እንዲጋጩ ተደርጓል።
ይህ ሁሉ ዝምታህ አስከመቸ ነዉ? ይህ ሁሉ ቻይነት የወንድ ሃሞትክን ተሟጥጦ ነዉ ወይስ መጠን የሌለዉ ቻይነትን ማሳየት ነዉ? ምን ያህል የወንድነት ሃሞትህ ቢፈስ ነዉ ከማሃልህ ዉስጥ እየኖሩ እነዚህ አረመኔዎች እንዲህ እያፌዙ የሚኖሩት? ለመሆኑ- የምትወዳትን የቃል ኪዳን ሚሰትህን ሲነጥቁህ ዝም ማለት እንዴት አስቻለህ? ሽማግሌ አባትህ እናትህ ወንድም እህት አጎትህ አክስትህ ጓደኛህ ጎረቤትህ በኢሰብአዊ ጭካኔ ተደብድቦ በፈላ ዉሃ እራሱ ላይ እየተደፋበት፤ በእሳት ተቃጥሎ፤ ተለብልቦ፤ ሽባ ሆኖ ተሰቃይቶ፤ ለሞት እና ለአካለ ጎዶሎነት ሲዳርጉት እያየህ ታሪካቸዉን በጀሮህ እየሰማህ ዝምታዉ ምን ይሆን? አዛዉንት የሚደፍሩ፤ ህጻናትን የሚገድሉ፤ እነዚህ አረመኔዎች በማሃልህ ቁጭ ብለዉ፤ ተጠያቂነት በሌለዉ ነጻነት ተደላድለዉ ሲያፌዙብን ዝምታዉስ አስከመቸ ሊቀጥል ይሆን?
ዛሬ ከሃላፊነት ቢሸሹ እና ቢደበቁም- ነገ “መስከረም-ይጠባል!” ብርሃን ሲታይ ከእግዚአብሔር እና ከፍትሕ የሚያመልጥ ከቶ የለምና አስከዛዉ ግን በእኛ በትግራይ ተወላጆች ላይ በወያኔዎች የተፈጸመብንን አረመኔአዊ ግፍ ሕዝቡ እንዲያዉቀዉ እና ፍትሕ እንዲጠይቅልን እና እነዲተባበረን መልእክታችንን እናስተላልፋለን። ኢትዮጵያ በነጻነት ለዘላለም ትኑር ገዛኢ ረዳ አቶ ገዛኢ ረዳን ለማነጋገር ለማንኛዉም ጥያቄ መልስ ለማግኘት “የኢትዮጵያ ሰማይ” የሕዋ ሰሌዳ ዋና አዘጋጅ የሆኑት አቶ ጌታቸዉ ረዳን በሚከተለዉ አድራሻ በመገናኘት መልስ ማግኘት ይቻላል። getachre@aol.com http://www.Ethiopiansemay.blogspot.com

የትግራይ ሕዝብ ሆይ! ከአቶ ገዛኢ ረዳ

Thursday, January 15, 2009

Quote of the Year

"Lately, the political carpet it stands on for long time is being pulled under its feet. It is now shopping around to sell its worn out garment by stitching it with new treads. The salesmen are all over the place looking for a bailout to save the bankrupted model... like they say-Good will hunting.. There are other toxic factions who facilitate the bailout in order to save it from total meltdown. Of course there are some who want to believe the unbelievable. I say –GO AHEAD MAKE MY DAY... ETHIOPIA SHALL PREVAIL!!" The above quote was taken from an Ethiopian writer by the name Ato Germame Neway. January 2009 Detail:-

This quote was taken from assimba.org/Debteraw.com websites discussion forum when arguing his position against OLF preachers and their sympathizers who present themselves as genuine Ethiopians under the political trade mark called “ DEMOCRACIA”. (http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/)

Monday, January 5, 2009

Stop Racism! Appeal To All Ethiopian Websites

ለተከበራችሁ
የኢትዮ ላዮን
አሲምባ
ደብተራዉ
ማህደር የህዋ ሰሌዳ አዘጋጆች
የአስተዳደር ጥያቄ አቤቱታ።
ከጌታቸዉ ረዳ
(http://ethiopiansemay.blogspot.com/)አቤቱታዉ በቋሚነት በየጊዜዉ በድረገጻችሁ “ኦቦ አራዳ ሻዉል” (Obo Arada Shawl) በሚል የብዕር ስም ስለሚጽፈዉ ኤርትራዊዉ “ራስ ሃይሉ” መጠርያ ስሙ “ተወልደ” የተባለዉ ግለሰብ ነዉ። ግለ ሰቡ በእድሜዉ ወደ 70ኛዉ አመቱ የተጠጋ አዛዉንት ቢሆኑም፤ በጸረ ኢትዮጵያነቱ ለአንድነት በሚታገሉ እወቅ ኢትዮጵያዉያን ታጋዮች በእነ እንጂነር ሃይሉ ሻዉል፤ በእነ ዶ/ታየ ወልደሰማያት፤ በእነ ፕሮፌሰር አለሜ እሸቴ ፤ፕሮፌሰር መስፍን አርአያን እና በጣም በርካታ እ-----------//- በተለያየ መልኩ በስመ ዲሞክራሲ አንድነታችንን ለመፈታተን ዘረኝነትን የሚያስፋፉ ከሚዲያዎቻችን ከመቅጽበት አቋም በመዉሰድ መድረኩን ነፍገን እናስወግድ፡ ወቅ በሆኑ በሞት የተለዩ ጀግኖች ጥንት ኢትዮጵያዉያን አርበኞች ሳይቀር ስም በመለጠፍ እና በማንኳሰስ በተለያዩ ፎረሞች እና በሰሌዳችሁ ላይም የኢሕአፓ ደጋፊ አባል ወይንም የአመራር አባል በሚያስመስለዉ አቀራረቡ በተለይም የኢሕአፓዉ “የጸጋየ ደብተራዉ” ስም በየጊዜዉ በመጥራት ለጸረ ኢትዮጵያ ተልእኮዉ በመጠቀም ኢትዮጵያዊ ጸሃፊ ለመመስል ኢትዮጵያዉያን እና የኢሕአፓ አባላትን በጣም በተካነ አቀራረብ በማሞኘት ጸረ ኢትዮጵያ አንድነት ሲያስተጋባ ቆይቷል። ይግረማችሁ ብሎ ደግሞ በቅርቡ የኦነግ ወታደሮች አዛዉንት እና ህጻነት አማራ እና ትገሬ ገዳዮች መሆናቸዉ በሰነድ ተሰንዶ እያለ የነጻነት እና የዲሞክራሲ ታጋዮች ናቸዉ። ማለቱን ተያይዞታል።
በግሌ የሰዉየን ማንነት እና አጻጻፍ ከተጠራጠርኩ ቆይቻለሁ።ብዙዎቹ ግን የነቁበት አልመሰለኝም። ሰዉየዉ በፕሮፈሰር አለሜ እሸቴ (Opne letter to Professor Aleme Eshete the Crisis and the deportation of Hagos G/Yesus)) እና በእዉቁ ምሁር በፕሮፌሰር ሓጎስ ገ/የሱስ ላይ የሰነዘረዉ ጽሁፍ (በአሲምባ እና በማህደር ሰሌዳ ላይ) ተመልክቼ በዉይይት ፎረማችሁ ላይ ባቀረበዉ ጽሁፍ አስተያየቴን ስሰጥ እንደተለመደዉ የኦሮሞ ነጸነት ግምባር ብሎ ራሱን የሚያታልለዉ ወንጀለኛዉ “ኦነግ”ን በመደገፍ የጻፋቸዉን መልክቶቹ ለእናንተ እና ለመላዉ ኢትዮጵያዉያን አንባቢዎች እንድታነብቡት ከዚህ ቀጥየ አቀርበዋለሁ ። ጽሁፉ በአሲምባ.ኦርግ ወይንም በደብተራዉ.ካም የሃሳብ መለዋጫ ሰሌዳ ላይ የጻፈዉ ቅጅ ነዉ።
On January 2, 2009 at 5:32 am obo arada shawl Said -To Getachew:-You should accept that you are not alone to born out of two nationalities or nations. Geta plus Redaie i.e Lord and Helper don’t match. What a confusion! You cannot be a master and a servant at the same time. Or you should give us a separate explanation GETA for who or SERVANT for whom? I am sure you are not a master to OLF or a servant to ePLF. After the Revolution of 1974 and which is still going on, you seem to be lost in the 18th Century. I am so sorry for you. Please, open your heart for solutions not for problems. I suggest you start by learning the ABC of DEMOCRACIA. I see that YOU and EPLF/TPLF army boast of 18,000 OLF soldiers were captured. The 18,000 were not soldiers of dictatorship but soldiers of DEMOCRACIA.
I just want to remind you that the OLF leadership chose to accept for four posts of a) Agriculture b) Education c) Development and d) Information. This is not difficult to figure out how smart the OLF leaders were. Mind you, they did not want to share power from the Defense, Foreign or Trade. They were looking for long term what we call DEMOCRACIA -building a bridge not destroying a bridge. Ato Getachew in any obituaries, you will see names, names and strange names. Lastly, what does Ras Hailu mean? Please, explain to me. I want to learn. I would suggest that you read my article entitled ” call me by my address, solutions with DEBTERAW, III” dated on October 23, 2008. I think it will indicate who we are first and then build a United States of AETHIOPIA (USAE)or something of that sort. Ato Germame Neway thinks that it is loaded and he does not believe it is appropriate to discuss with what he calls his “enemies”. And I am a believer who discusses with my enemies more than with my friends.
እንግዲህ ከላይ እንዳነበባችሁት ኦነግ አገሪቱን ከወያኔ በበለጠ የጦር ሃይሉን የማንቀሳቀስ አቅሙ እንደሌለዉ ሁላችን ብናዉቀዉም፦ የተወልደ (“የኦቦ አራዳ ሻዉል”)- *ኦነግ* አስተዳደሩን የሲቭል አና የትምህርት ዘርፎችን ለመምራት የጓጓዉ አማርኛን እና የግዕዝ ፊደላችነን ለማጥፋት በቅኝ ገዢዎች ፊደል “የላቲን” ቋንቋ ለመተካት ሆን ብሎ እንደተሟሟተበት እና የልቡ እንዳደረሰለት እየታወቀ “ኦቦ ኣራዳ ሻዉል” ተባለዉ ጸረ ኢትዮጵያ ግለሰብ ግን ከላይ እንደጻፈዉ “ኦነግ የተረከበዉን ያስተዳደር ዘርፎች “ዲሞክራሲያ” ለመገንባት እና ሰላም ፈላጊ እና ሰላማዊ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት መሆኑን ለማሳየት እንጂ የጦር ሰዉ ቢሆን “የወያኔዉን የመከላከያዉ ሃይል በመቆጣጠር ያዝዘዉ ነበር” ሲል ሊነግረን ሞክሯል። ሞኝን ሞኝ ቢሉት ሹመት ይመስለዋል። ሰዉየዉ “ብልጣብልጥ-ሞኝ” መሆኑን እያወቅነዉ “ሞኝ” ብንለዉ - “ሹመት” ይመስለዋል እና እንቀጥል።
ወያኔ የማረካቸዉ/ (በሽግግሩ ጊዜ የበተናቸዉ 18,000 የኦነግ ታጣቂ) በሌንጮ ለታ እና በሌሎቹ ጸረ-ኢትዮጵያ ግለሰዎች የሚመራዉ የኦነግ ታጣቂ ሰራዊት በኦሮሞ የኢትዮጵያ ክፍላተሃገሮች (አሱ ዩናይትድ ስቴትስ ኦፈ “ኤ’’ ኢትዮጵያ ይለዋል) ’አካባቢ የአማራዉን፤የትግራዩን እና የጉራጌ ገበሬዎች እና የሰፈራ ጣብያዎች ህጻናት ሳይቀሩ በአንድነት/በጀምላ ሰብስቦ በእሳት የጋዩት በእነዚህ በኦነግ ጦር መሆኑን እየታወቀ እና ሰብአዊ ተመጓቾች የዘገቡት “የዘር ማጥፋት” ወንጀል የተፈጸመዉ በዚህ በኦነግ ጦር እንደሆነ እየታወቀ- ግለሰቡ/(Obo Arada Shawl) ወንጀለኛዉን የኦነግ ጦር 18,000 OLF soldiers were captured. The 18,000 were not soldiers of dictatorship but soldiers of DEMOCRACIA. በማለት ሲከራከር- የኦነግ ጸረ ኢትዮጵያነት እኛ ብቻ ሳንሆን መሪዎቹ በቅረቡ “በተሳሳተ መንገድ ህዝቡን ይዋሹት” እንደነበረ አምነዋል።
ይህ ግለሰብ የማንነቱ መለያ ቁልጭ ባለ መንገድ ሲነግረን _ እናንተ ወንድሞቼ ከእንግዲህ ወዲህ በመድረካችሁ ብታስተናግዱት እኔ ለድረ-ገጻችሁ የነበረኝን ከበሬታ እንዳለ ሆኖ “በናንተ ድረ ገጽ ግን እንደማልሳተፍ ግልጽ ላደርግላችሁ እወዳለሁ። ሰዉየዉን ብታስተናግዱት አንባቢ ለናንተ የነበረዉ ከበሬታ እንደሚቀንሰዉም በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ።በተለይም ይህ ግለሰብ መድረካችሁን ለመጠቀም የኢሕአፓን ስም እና ታጋዮች ጣልቃ እያስገባ የጸረ አንደነቱን መልእክት ስለሚያስተጋባ ኢሕአፓዎች ለድረገጽ አዘጋጆቹ ብታሳስቡዋቸዉ ለድረጅታችሁ ክብር እና ስም ለመጠበቅ ያመቻችሗል።
ክቡራን ወገኖቼ ሆይ፦ እንደምታዉቁት ጌታቸዉ ረዳ በትግሬነቴ ብቻ ሳይሆን በ ኢትዮጵያዊነቴ እድሜየ በሙሉ የኮራሁበት አገሬ ኢትዮጵያ መሆኑን ታዉቃላችሁ። በ ኢትዮጵያዊነት እና ለኢትኦጵያ በመቆሜ ብዙ በጣም ብዙ በርካታ ጠላቶች አፍርቻለሁ።አገርን በመጨቆን ላይ ያሉት ብዙ የጥንት ወዳጆቼም በዚህ ፖለቲካ ሳቢያ ተለይቻቸዋለሁ። ያ ተነሳሁበት ኢትዮጵያዊነት ግቡ አስከ መታ እና አገሬ በነጻነት አስኮነረች ድረስ የጠላቶች ጉራ እና ዛቻ ከቶዉንም አልበገረኝም ለወደፊቱም አይበግረኝም።ከመጤፍም የምቆጥረዉ አይደለም። የወያኔ ጀሌዎች፤የሻዕቢያ ጀሌዎች የኦነግ ጀሌዎች “ጌታቸዉ” የሚለዉ የኢትዮጵያ ስም ሆነ የአማርኛ ቋንቋን ለማጥፋት በተለያዩ ጊዜያት “በዘፈንም፤በጽሁፋቸዉም፤በንግግራቸዉም፤በትያትርም” የቻሉትን ያህል የአማራን ስም ለማንኳሰስ ብዙ- እጀግ ብዙ ጥረዋል።ግን ኢትዮጵያዊነትን መስበር አልቻሉም።
አሁንም ከላይ እንዳነበባችሁት በኢትዮጵያዉያን ወላጆቼ የተሰጠኝን መጠርያ ስሜ እና የወላጆቼን መጠርያ ስም በዚህ ዘረኛ ግለሰብ ሲያንኳሰስ እና ሲናናቅ በማንበቤ የማዝነዉ እኔ ሳልሆን በእኔ እና በወላጆቼ ስም በመቀለዱ እናንተ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቼ ምንኛ እንደሚሰማችሁ እርግጠና ነኝ። እኔ እማ ዘረኛነቱንም ዘለፋዉንም እደሜየ ሙሉ በእነ ተወልደ ዓይነቱ የኤርትራ ዘረኞች፤ በላያችን ላይ ለብዙ አመታት ስለወረደብን ለምጀዋለሁ። የዘረኖች ጫጫታ አዲስ አይሆንብኝም። የሚያሳዝነዉ ግን የተለያዩ ስሞች የያዙ ራሳቸዉን መከላከል የማይችሉ ህጻናት እና በቀላሉ የሚሰበር ልብ የያዩዙ ጎልማሳ ሴቶች እና ወንዶች “የ አማርኛ ስማ በመያዛቸዉ ብቻ” በምን የሕሊና ስቃይ እየተራመዱ እንደሆነ የምታጡት አይመስለኝም።
ቀለም ቀመስ ሙሑራን ምንኛ በዘር ፖለቲካ ተዘፍቀዉ የራስ ቂልነታቸዉ ላልተማረዉ ህብረተሰብ እያንጸባረቁ እንደሆነ ከእናንተ የሚሰወር አይመስለኝም። (የአማራዉ ሕዝብ ከየት ወደየት የሚለዉ የዘረኛዉ የአንዳረካቸዉ መጽሃፍ ምንኛ ሕዝቡ እንደበከለዉ ዉጤቱ ተምሬአለሁ በሚለዉ “ኦቦ አራዳ ሻዉል” በተባለዉ ዘረኛዉ ኤርትራዊ ወልዱ ተወለደ የዘረኝነት ምርቱ እያፈሰዉ መሆኑን ማየት ይቻላል።
To Getachew:-You should accept that you are not alone to born out of two nationalities or nations. Geta plus Redaie i.e Lord and Helper don’t match. What a confusion! You cannot be a master and a servant at the same time. Or you should give us a separate explanation GETA for who or SERVANT for whom?
ወንድሞቼ- ዘረኛዉ ኤርትራዊ “ራስ ሃይሉ” የብዕር ስሙ “አቦ አራዳ ሻዉል የተባለዉ ከላይ የተጠቀሰዉ ግለሰብ - በእኔ እና በወላጆጄ እንዲሁም በአያቶቼ ቅድመ ቅደመ አያቶቼ እና አያቶቹ ሲገለገሉበት የቆዉ ኢትዮጵያዊ ስም (what a confussion!በማለት የራሱን አዛዉንታዊ ኩታራ ጨንቅላት ሊገልጽ ሞክሯል) ወላጆቼ ስም ስያወጡልኝ ወይንም አያቶቼ የወላጆቼን ስም ስያወጡላቸዉ “ግራ አልተጋቡም”። ስም ሲወጣላቸዉ እና ስም ሲያወጡልኝ የማንንም ዘረኛ ፈቃድ አላስፈለጋቸዉም ነበር።ለዘረኞች የሚንበረከኩም አልነበሩም።
የኢትዮጵያን ጀግኖች እየመሩ በጣልያን እና በድርቡሽ በሁለተኛ እና በመካከለኛ ደረጃ አዋጊ ጀኔራሎች ሆነዉ የድረቡሽን ምሽግ የበረገዱ ሁለቱም አያቶቼ ማንም ዘረኛ ደፍሮ ስምህ ለዉጥ ወይንም ስምህ አላማረንም ብሎ ከፊታቸዉ የሞከረ ፍጡር አልሰማንም። የሱ አያቶችም ከአያቶቼ ግምባር ፊት ቆመዉ ደፍረዉ ስምዎትን እና ማዕረግዎን ስም ይለዉጡ ብለዉ ይሞክሩት ነበር ብየም አልገምተዉም። አያቶቹ አንደ አያቶቼ የተከበሩ ጨዋ ኢትዮጵያዉያን ነበሩ የሚል ግምት ስላለኝ።ትናንት ከትናንት በስቲያ ለዘረኞች እና ለወራሪዎች ለታሪክ አፍራሾች ያልተንበረከኩት አያቶቼ በእኔ ዘንድ ሲደርስ የእኔ ስም እና የወላጆቼን “ስም ሲያነብቡ” “የማይጥማቸዉ” የዛሬ የዘመናችን ዘረኞች አነሱ በሚፈቅዱልኝና በሚመርጡልኝ ስም እንደማልጠራ በድጋሚ ዘረኞች እንዲያወቁት ላረጋግጥ።
ኢትዮጵያዉያን ወላጆቻችሁ የሰጡዋችሁን ስም አላማረንም እያሉ በዘረኝነት ጨዋታ እየገቡ በሌላ በኩል ደግሞ “ስለ ሕዝብ ጉዳይ እና ስለ ፖለቲካ” ላዉራ እና ልጻፍ እያሉ በ አደባባይ የኢትዮጵያዊነት ስም እና ኢትዮጵያን አርበኞችን ሲኮንኑ እና ሲያናንቁ ካሁን በፊት ያነበብናቸዉ ዘረኞች ከእኔም ሆነ ከሌሎች ኢትዮጵያ ታጋዮች ጋር ሲከራከሩ ፦ በዘር በሽታ በመለከፋቸዉ ወይንም ትላልቅ ዕዉቅ ሲቪክ ማሕበራት የመምህራን ማህበራትን በሚመሩ ታጋይ መሪዎች ላይ የማይገባ የዉርደት ዘለፋ ሲዘልፏቸዉ ተደምጠዉ በራሳቸዉ ቅሌት ፈጣን ዉድቀት እየጋበዙ ከመድረኩ ተሎ እንዴት ይወገዱ እንደነበሩ ሁላችሁም የምታስታዉሱት የቅርብ የኢንተርኔት ሰሌዳዎች ትዉስታ ነዉ። ይሄኛዉም በጸረ ኢትዮጵያዊነቱ እና በዘረኛነት አቋሙ ከመድረካችሁ በማስወገድ የአስተዳደር እርምጃ እንደምትወስዱበት አደራየ የጸና ነዉ።ድረ ገጸቻችሁ የ እነኒህ ግለሰቦች ማጀብ ከቀጠለ ግን እጣዉ እነሱን ሚከተል ይመስለኛል።
እስኪ ይሄነን አሱ አምርሮ የሚጠላዉ የትግራይ ሕዝብ እና ከትግራይ ሕዝብ አስበልጦ የሚወድደዉ የኦሮሞ ሕዝብ በማወዳደር ትግራይን Biologically/by nature“ስልጣን ናፋቂ፤የስልጣን ስስታም፤አወተሪታቲቭ/ጨቋኝ፤ገዳይ ፈላጭ ቆራጭ ያለዉን እና የኦሮሞ ሕዝብ ግን Biologically/naturally born Democrat ያለዉን ዘረኝነቱን እና ቂልነቱን አንብቡልኝ።Germame & Getachew are in the business of ETHIOPIA WILL PREVAIL AND I AM IN THE BUSINESS OF TRUTH WILL PREVAIL የራቀ መፈክር በማስመሰል መርሆአችንን በማንኳሰስ “ኢትዮጵያ” -ዉሸት”- ሆና “ በ ኢትዮጵያ ቦታ የተካዉ “ትሩዝ” ዊል ፕሪቨይል” ብሎታል። ኢትዮጵያ እና ዉሸት አንድ አድርጎ “ዕዉነት” በሚለዉ ተክቶባታል። ኢድየም/ቅኔኞች የምታዉቁት ይመስለኛል። የመለስ ዜናዊ ቅኔ ተመልሶ ዞሮ በ እነዚህ ዌብሳይቶች በግልጽ መነገር መጀመሩ ነዉ። WOLDU TEWOLDE' S DEFINATION FOR ETHIOPIA IS FAKE AND OUR SLOGAN ETHIOPIA WILL PREVAIL IN HIS WORD IS FAKE AND HE STANDS FOR TRUTH APART TO THE COUNTRY CALLED ETHIOPIA AS IF ETHIOPIA WILL PREVAIL THE SYMBOL OF FAKE. አንድ በሉልኝ።
የኦነጉን ሰዉየ ጸሁፍ ለሚድያ ጥራት ከተጻፉት ብዙ ብለግናዎች ብዙዎቹ (ፐሮፋኒሲ) ሰርዤዋለሁ።የኦነጉን ሰዉየ ጸወሁፍ Getachew’s disadvantage is that he was born in authoritative community whereas Fayyis’s advantage is because he came from democratic culture. The end result is that Getachew’s community has used their dictatorial nature for power whereas the Fayyis community are using their democratic nature ። አንድ በሉልኝ። እንግዲህ ከዲሞክራቲክ ማህበረስብ የተወለደዉ ተወልደ እየመሰከረለት ያለዉ የኦነጉ ጀሌ ዲሞክራሲያዊ ጽሁፍ ከላይ ተመልክታችሁታል። አቶ ተወልደ ህዝብን በዘር ፈጀ የኦነግ ሰረዊት እና አመራር አስከ እነ ፖሊሲዉ የመደገፉ መብቱ ነዉ። ህዝቡን እያወደዳደረ ትግሬዎችን በተፈጥሮ ስልጣን ሱሰኞች እና ፈላጭ ቆራጮች ማድረጉ ግን ከትብቅና አልፎ “ዘረኝነትን በሚዲያ ማንጸባረቁ” ኢትዮያዉን የሚወዱለት አይመስለኝም። ድረ ገጸች ይህነን ሲያነቡ ሰዉየዉን ማስወገድ ነበረባቸዉ። የኦሮሞ ሕበረተሰብም ሆነ የትግራይ ህብረተሰብ በታሪካቸዉ ዲሞክራሲ የሚባል አሰራር እንዳልነበራቸዉ እና ሴቶችን የሚበድል መጮቆን (ጾታ) ቀለምም (ቆዳ) ሆነ ለዕድሜ ብቃት ወይንም (የወንድ ብልትን በመስለብ ለስልጣን/ለትዳር ብቁነት ማስመስከርን) ለስልጠን በግድያ እና ሕብረተሰብን በ ሌላዉ ህብረተሰብ ንበረት እና ቤተሰብ አመጽ እና ዘረፋ መሰማራትን፤ በተወሰኑ የሙያ ዘርፎች የተሰማሩትን መዝለፍ/ለጋብቻ መከልከል….የመሳሰሉ ሰዉን እና ሕብረተሰብን የሚለያይ ስርዓቶች የመሩ እንጂ “ዲሞክራሲያ/ዲሞክራሲ” የሚባል
እንዳልነበራቸዉ እኔ ባነበብኩት ታሪክ መከራከር እችላለሁ -ካሁን በፊትም በበቂ ማስረጃ ተከራክሬአለሁ። በዚህ ጥሪ ላቅርብ የሚከራከር ካለ ዝግጁ ነኝ! የኦሮሞ ህዘባችን በተፈጥሮ ዲሞክራት ሆኖ ከተፈጠረ ደስ ይለኛል እንጂ አይከፋኝም።ነገር ግን እኔ እና እኔን የወለዱኝ የትግራይ ወላጆቼ እና ቅድመ አያተቼ ፈጣሪያቸዉ ፈላጭ ቆራጭ ገዳዮች፤የስልጣን ጉግት እና ተሻሚ፤ፍትሕ አልባ _አዉቶሪተቲቭ ሆነዉ አልፈጠራቸዉም። ሆነዉ በተፈጥሮ እንዲያ ሆነዉ እንዲወለዱም አልፈልግም። ልዩነታችን ይሄ ነዉ። ህዝብን ማሳነስ ፤መዝለፍ እየተበራከተ እየሄደ ነዉ ስላችሁ አብዛኛኦቻችሁ “ቸል- በሉት” የሞኞች ንግግር ነዉ እያላችሁ እዚህ ድረስ ደርሰናል፦ እያደገ ሲሄድ እንደ እሳት ሰደድ ዘረኝነት ምን እንደሚያስከትል፤ ለናንተ ለብልህ አንባቢ አልነግርም።
ልጨርስ ነዉ-፤
በጣም አስፈላጊ እና አስገራሚ እና ሁላችንም አስተማሪ የሆነ ነገር ላስነብባችሁ እና ልሰናበታችሁ። ከላይ በማስረጃ የነገርኳችሁ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከሰርጎ ገቦች፤አስመሳዮች እንዲነቀቅ እና እኛኑን መስለዉ የተሰለፉበት ጸረ-ኢትዮጵያ ተልእኮአቸዉን ማክሸፍ ይጠበቅብናል። አንድነታችንም እየመነመነ የሄደዉ በሰርጎ ገብ ወኪሎቻቸዉ እንደሆነ እንወቅ። እኛን መስለዉ ጸረ- አንድነት የሆኑ ሃይሎች እንዴት እንደሚገቡ እና በሁለት ገጽታቸዉ ምን እንደሚመስል ለማስረጃ ከሰበሰብኳቸዉ የሚከተለዉን ማስረጃ ትምህርት እንዲሆነን የሚከተለዉ ደብዳቤ ለኔ የላከልኝን ጸረ- ኢትዮጵያ ኤርትራዊ ሰዉ “የትግራይ ተወላጅ” በመምሰል በመጀመሪያዉ ደብዳቤዉ እኔን “ምን እንዳለኝ” እና ከወር በሗላ ቆይቶ ደግሞ ኤርትራዊ ሆኖ በመቅረብ- የትግራይ ሰዉ በመምሰል ሲከላከልለት በስሙ ሲነግድበት የነበረዉን የትግራይን ሕዝብ ተምልሶ ምን ዓይነት ዘለፋ እንዳወረደበት ማስተማሪያ እንዲሆነን አንብቡት። አነሆ_ From: henok kahsay Subject: commentTo: getachre@sbcglobal.netDate: Friday, December 5, 2008, 3:05 AMHey Getachew:You see man, all the nasty paragraphs you write about this valiant, brave and capable people of TIGRAY simply tells how the memory of your defeat (EPRP's defeat) at the hand of this same people is haunting you throughout your life. Poor Getachew. Yes, you were a big predicament on our struggle that has a clear and tenable strategy and end. So we had to kill you one by one in the battle. So we did that. Just bitter though it is take it. It is a reality. You were a curse to this country, so we had to get rid of you, man. So we did these in all the places you probably remember. Well I am sure you do remember each and every one of them. How can one forget places of defetas that have left an ever haunting effects. We had to fight and win you. We did this at Mereto, Bizet, and finally at your main place Asimba.As a result, we are enjoying everything at our threshold: everything from factory to companies, from transportation to agricultural products. Everything everything. there is nothing that we miss thanks to our struggle that beat you and EPRP.As to the complaint of the fighters at Guna after clearing Derg from Tigray, the organization, TPLF/EPRDF convinced the fighters and return them to their trenches to keep fighting. So what does this show? I think you must be a blockhead to miss the secret.It was simply because TPLF/EPRDF had the conviction that the whole Ethiopian people have to be freed from the yoke of the Derg. The organization had a broad based view and was not a rarrowist, as you wrote it in your Amharic text. So the bottom line isWE WERE SUBJECTED TO EXTREME OPPRESSION AT THE HAND OF THE DERGWE GOT ORGANIZED AND WENT TO DEDEBITWE GOT ARMEDWE FOUGHTAND AS A RESULT, WE WON.AND AS YOU SAID EVERYTHING IS AT OUR DISPOSAL (HULUM BEDEJACHIN, HULUM BEJACHIN)- min tameta err dibn belWhat do you say to this, Getachew ehapaw. henok kahsay" : getachre@sbcglobal.netThursday, December 11, 2008 1:48 AMNow you started crying for the RED SEA.Heyyyyy what abtih agebah sile Red Sea. It is Eritrean and only Eritrean property. Do not you know that we defeated you in 1991 and took our ports by force.dedeb Agame
From: henok kahsay Subject: commentTo: getachre@sbcglobal.netDate: Sunday, September 7, 2008, 8:15 AMHelloYou know every thing you write and post is really really silly, silly and non-sense. I think you too sound a big jilla jil. You must be one of the EPRP soldiers butted and badly beatten at Mereto and Asimba in 1971 E.C. The pain you suffered at that time in the hand of the gallant TPLF fighters does not seem to go out of your tormented mind. It will continue harrassing you until you give your last breath. That could be the reason why you are spending your time calling the name of weyane from dawn to dusk. Am I right, old man?Henok, wedi weyane //
በተለያየ መልኩ እኛን መስለዉ በስመ ዲሞክራሲ አንድነታችንን ለመፈታተን ዘረኝነትን የሚያስፋፉ ከሚዲያዎቻችን ከመቅጽበት አቋም በመዉሰድ መድረኩን ነፍገን እናስወግድ፡ Ethiopia will Prevail!

Thursday, January 1, 2009

ጭካኔ 17 -ጭካኔ 18 እና ላዉንቸር የተባሉ አድማ በታኝ ልዩ ሃይሎች ጌታቸዉ ረዳ ከወያኔ ገበና ክፍል 3 -ካለፈዉ የቀጠለ በመጀመሪያ እንኳን ለአዲሱ የፈረንጆች ዓመት አደረሳችሁ! ይላል የኢትዮጵያ ሰማይ የህዋ ሰሌዳ።ዓመቱ ኢትዮጵያን በጠላትነት ሲፈርጃት እና ታሪክ አዛብተዉ ራሳቸዉን አታልለዉ የዋህ ከብት እረኞች ኢትዮጵያዉያን ኦሮሞዎችም በማይዘለቅ እሳት አስገብተዉ ለ40 ረዢም ዓመታት ለሞት እና ለዉርደት ራሳቸዉንም(መሪዎችም ጭምር) ለስደት ዳርገዉ አገር አልባ አድረገዋቸዉ ከረዥም ዉርደት በሗላ ወደ ሰብአዊ ሕሊናቸዉ በመመለስ የመሰረቱት እና የገነቡት “ኦነግ”ን በማዉገዝ ወደ ጤናማ ማሕበረ ሰብ እና ጤናማ ፖለቲካ በመመለሳቸዉ ለኢትዮጵያዉያን ሆነ ለራሳቸዉ ለኦነግ መስራቾቹ ጥሩ ጅምራ እና ተስፋ ሰጭ በመሆኑ በዚህ የፈረንጆች “አዲሱ ዓመት” ኦነግን ኮንነዉ ለተዉት እና በማታለል ባልሆነ የፖለቲካ ዕምነት ተዘፍቀዉ ኖረዉ ሕሊናቸዉን ነጻ ያወጡ ሁሉ “እንኳን ድስ አላችሁ! መልካም አዲስ ዓመት!” ይሁንላችሁ እያልኩ፤
-በዚህ አጋጣሚ ባዶ የቀረዉ የኦነግ ድርጅንት ለመጠቀም በመኔሶታ/አሜሪካ እና በአዉሮፓ ከተሞች የሚኖሩ ስለ ኦሮሞ ኢትዮጵያነት ታሪክ ያልተማሩ የኦነግ ዉሸት ፕሮፖጋንዳ ያታለላቸዉ የዋህ ወጣት የኦነግ ተከታዮችን “ገንዘብ” ለመበዝበዝ የሚሯሯጡትን “የቁም ሙታን ዉሸተኞችን” ወጊድ ብላችሁ አገራችሁ ኢትዮጵያ እንጂ “መኔሶታ ወይም ስቴክሆልም” ያለመሆኑ ተረድታችሁ፦ “ለሻዕቢያ ኮሎኔሎች ዉሃ አመላላሽ እና እንጨት ፈላጮች” ከመሆን እንድትድኑ፤ አጋጣጣሚዉን ተጠቅማችሁ “ከዉሸት ቀፎ” ራሳችሁን አስወጡ። ፖለቲካዉ ካልሰራ፤ ሌላ ፖለቲካ መለወጥ ደመብ ነዉ። “ባለህበት ርገጥ” -እዛዉ መዘፈቁ እንደ “ማሙሽ” ራስን ማታለል እና መበደል ነዉ። ከወደቁ በሗላ መፈራገጥ ለመላላጥ!! እነ “አሰፋ ጃለታ” የአሜሪካን *ሳብ-ወይ* “ሳንድ-ዊች” እየገመጠ ልጆቹን እያስተማረ ራሱን ከመከራዉ ከልሎ በአሜሪካን ጎዳናዎች እና ዩኒቨርሲቲዎች እያዝረጠረጠ “ሌንጮን እየኮነነ” “ግፋ በለዉ” ሲላችሁ <ኦሮሚያ የሚባል “አገር” ነጻ ለማዉጣት ና ወደ ጦር ሜዳ ምራን፤አብረሀን እንሂድ በሉት! የም ቢሆን “ባለ ሃሞት” ሄያጅ ካለ ማለቴ ነዉ።>- ያኔ የቃሉን እዉነትነት ትሰሙታላችሁ>> “መልካም አዲስ ዓመት” (ካዉንት ዳዉኑ ይቀጥል! Let the Countdown contiunue!Who is Next?)::
ወደ ዋናዉ ርዕሳችን እንግባ። ባለፈዉ ክፍል ሁለት በወያኔዉ ስርዓት በአዲስ አበባ ፖሊስ የወረዳ 20/ የምርመራ ሹም እና አዛዥ የነበሩት የመቶ አለቃ አበረ አዳሙ መኮንን የነገሩን ወያኔ አብደል መጂድ ሑሴን እና የወያነዉ ጀነራል ሓለፎም አርአያን የመግደል ሙከራ እና ግድያ እንዴት ለፖለቲካ መጠቀሚያዉ ለማድረግ እንደሞከረ አስረድተዉናል። ዛሬ በዚህ ክፍል ደግሞ ስለ ሕግ የበላይነት በወያኔ አተሮጓጎም እና ጭካኔ 17፣ ጭካኔ 18፣ ላዉንቸር ወዘተ…የተባሉ ልዩ ሃይሎች ለአድማ ብተና ሲሰማሩ በሰለማዊ ሰልፈኞች ላይ “ላዉንቸር” እንዲጠቀሙ ነጻነት እንዳለቸዉ የጠቆሙበት ቃለ ምልልስ ነዉ። አንዳንዶቹ ከንግግር/ከቃለ መጠይቅ የተወሰዱ ስለሆኑ ለስርዓተ ንባብ አመች ሁነዉ ሳይገኙ ሳያቸዉ ለንባብ እንዲመች አስተካክየ አቅርቤአቸዋለሁ። እንቀጥል፦
"ሕግ ማለት ምን ምን ማለት ነዉ? ሕግ ማለት ጉዳዮችን በበላይነት ያለ አድልዎ ህብረተሰቡን የሚያገለግል የሕዝብ ተቋም ነዉ። አንዳንድ ባለሞያዎች ሕግ ማለት ለገዢዉ መደብ የሚያገለግል የማስከበሪያ ተቋም ነዉ ይሉታል። የሗላኛዉ ትርጉም “ሕግ ማለት ለገዢዉ መደብ የሚያገለግል ማሳሪያ ነዉ” የሚለዉ ለኢሕአዴግ ይሰራል። ለድርጅቱ መገልገያ ስላዋለዉ። የዜጎችን መብት እናከብራለን በሚሉት አገሮች ግን የሕግ ትርጓሜ “ሕግ” ማለት ምን ማለት ነዉ? ሕግ ማለት ማሕበራዊዉን ፖለቲካዊዉን እና የአስተዳደራዊ ተቋማቶችን ለዜጎች በእኩል የሚያስተዳድር ተቋም ማለት ነዉ። ሕግ ማለት በኢሕአዴግ ኢትዮጵያ -ሕግ- *የበታች* ነዉ፤ ፖለቲካዉ ደግሞ *የበላይ* ነዉ። ሕግ ያለዉ ታች ነዉ፡ ፖለቲካዉ ደግሞ እላይ ነዉ ያለዉ። ሕግ የበላይ ቢሆን ኖሮ የዜጎችን መብት በፖለቲካ አመለካከት ምክንያት ሕግ እንዲጣስ አይፈቀድም ነበር።
የሕግ የበላይነት ቢኖር ኖሮ እነ ስየ አብርሃ እስረ-ቤት ሲገቡ ብቻቸዉን አይገቡም ነበር። አብረዉ እነ አቶ መለስ ዜናዊም ጭምር ነበር የሚገቡት። ምክንያቱም የፈጸሙት ወንጀል ዕኩል ነዉ።ምክንያቱም ለመከሰሳቸዉ ምክንያት ሙስና ፈጽመዋል ከተባለ ያን ያህል ከባድ እና ሰፊ ወንጀል ከተፈጸመ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ሙስና እንዳይስፋፋ/እንዳይፈጸም ባለመከላከላቸዉ እኮ በሕግ ያስጠይቃቸዋል (ሌላዉን ጉዳቸዉን ትተን ማለት ነዉ)።
እነ ስየ አብርሃ፤ አሰፋ አበርሃ፤ እነ አባተ ኪሾ ቢተዉ በላይ ወዘተ..ወዘተ.. የሚባሉ ባለስልጣናት ያ ሁሉ ከባድ ከባድ የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል ከተባሉ፤ ያን ሁሉ ብሄራዊ ጉዳትና ጥፋት እንዳይፈጸም የመቆጣጠር ሃላፊነት ያለዉ ማነዉ? ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነዉ። ስለዚህ ሙስናዉን እና ከባድ ከባድ ወንጀሎችን እንዳይፈጸሙ በወቅቱ በላመቆጣጠራቸዉ እና ባለመከላከላቸዉ በስራቸዉ ላይ እንዝህላልነት ስላሳዩ በብቃት ማነስ ብቻ ከሃላፊነታቸዉ መወገድ ብቻ ሳይሆን ለሙስና በር ከፍተዉ በማመቻቸታቸዉ በሕግ ያስጠይቃቸዋል። ሃላፊነት መዘንጋት በሕግ ፊት ያስጠይቃል።
አንድ ጦር አዋጊ ምሽጎችን ካልተቆጣጠረ ለጠላት ጥቃት ምቹ ሁኔታ ከከፈተ በጦር ሜዳ ሕግ ያስጠይቀዋል። ይሄም አስተዳደራዊ ሕግ አለዉ። የሕግ የበላይነት ባለመኖሩ ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሳሽም ጠያቂም የላቸዉም።የሕግ የበላይነት ቢኖር በዚህ መንገድ ለግል ጥቃት እስር ያስገቡዋቸዉ ብቻ ሳይሆኑ የህወሓት መአከላዊ አመራር አባሎች እንዳለ በሙሉ ተለቅሞ አስር ቤት ይገባ ነበር።
እነ ታምራት ላይኔ ብቻቸዉን ያጠፉት ነገር አይደለም። አንዴ ሱካር አንዴ ምን እያሉ ሰማቸዉን በማራከስ ራሳቸዉን ንጹህ ለማድረግ ከመሃላቸዉ ለማጥቃት የፈለጉዋቸዉን ግለሰቦችን መርጠዉ ወደ ህዝቡ ወላፈን በመወርወር ራሳቸዉን ንጹህ እና እዉነተኞች ለማድረግ ተንጫጩባቸዉ።
ቀደም ብየ እንዳልኩት የሕግ የበላይነት ቢኖር ኖሮ ሁሉም ተለቅመዉ እስር የመግባት ዕድላቸዉ በእርግጠኝነት ማስረገጥ ይቻላል። አንድ እታች እጅግ በጣም እታች ያለዉ “ተራ ዜጋ” (በሕዝብ ቋንቋ) እና እላይ ያሉት በ“ዲፕሎማቲክ ኢሚዩኒቲ” የሚታዩ ከፍተኛ ባለስልጣናት ዜጎች አሉ። ተራ ዜጋ እና “ዲፕሎማቲክ ኢሚዩኒቲ” ያለዉ ዜጋ ለምሳሌ እንደ አቶ መለስ ዜናዊ የመሳሰሉት ሰዎች በሕግ ፊት ሲቀርቡ ሁሉም እኩል ናቸዉ።
በሃገሪቱ ዉስጥ ለተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ረገጣ፤ በሃገሪቱ የተፈጸሙ የተለያዩ የሙስና ተግባሮች እና የንብረት ምዝበራዎች፤ ቅድም ስጠቅሳቸዉ የነበሩት በእነ “አቶ ተስፋየ ናሁ ሰናይ” ጋር በመሆን (የኢትዮጵያ መንገዶች ዋና ስራስክያጅ ባለስልጣን) ትራክተሮች-ቡልደዘሮች የመሳሰሉት ከባድ-ከባድ ንብረቶች ከወደብ እንደ መጡ ወደ ሌሎች ክልሎች ከመሄዳቸዉ በፊት-ወደ ትግራይ እየሄዱ ለትግራይ ክልል መገልገያ እንዲዉሉ የተደረገዉ የሕግ በላይነት ያልተከተለ አድላዊ አሰራር ስንመለከት አሰራሩ “ሙስና ነዉ”! “ምዝበራ ነዉ”! “አድልዎ የተከተለ አሰራር ነዉ”። ይህንን ያደረጉት ደግሞ እነ “አቶ ተስፋየ ናሁ ሰናይ” እና እነ “አቶ መለስ ዜናዊ” ናቸዉ። የሕግ የበላይነት ቢኖር ኖሮ እነዚህ ሰዎች ለምን አልተጠየቁም? ምክንያቱም የሕግ በላይነት የለም።
በአንድ አገር የሕግ የበላይነት ካለ ሰብአዊ ዲሞክራሲያዊ መብት ይከበራል፤ በሙስና የተዘፈቁት ባለስልጣኖች ሁሉ ከተራ አስከ ዲፕሎሚቲክ ማዕረግ የያዙ በምዝበራ በአድልዎ ፍርድ በማዛባት የተዘፈቁ ሁሉ በሕግ እኩል ይዳኛሉ። በኢትዮጵያ ይህ የለም። አቶ መለስን መክሰስ እና ፍርድ ቤት ማስቆም አይቻልም! ያገሪቱ ሕግን በመጫምያቸዉ በመርገጥ አሳቸዉ ከላይ ሆነዉ ህጉ ግን ከታች በስራቸዉ ስለሚደፈጠጥ ነዉ። ፖለቲካዉ ደፍጣጭ-ሕግ ተደፍጠጭ!
በጣም የሚገርመኝ፦ በኢትዮጵያ ዉስጥ የሕግ የበላይነት በሌለበት ሃገር “ማልቲ -ፓርቲ” ሲስተም/ስርዓት እናሰፍናለን ብሎ ለይስሙላ አዉጆ “ዲሞክራሲ” አለ ብሎ ለዓለም ሲዋሽ “ድርቅናዉ-ድፍረቱ” ግርም ይለኛል! ከሕግ እና ከ “ማልቲ- ፓርቲ ዲሞክራሲ” የትኛዉ ይቀድማል? ይህንን ሰብአዊ፤ የማሕበረሰብ የሕግ ሙሁራን ይተቹበት፡ ለነሱ ልተወዉ።
እኔ በፖሊስ ሙያየ ግን ትንሽ ልበልበት። የቱ ነዉ መቅደም ያለበት- ሕግ ወይስ ዲሞክራሲ? አንድ ዳኛ የሚዳኘዉ በሕግ ነዉ። ዜጎች የሚዳኙት በሕግ ነዉ ወይስ በማልቲ-ፓርቲ ሲስተም? ሕግ ሰዎችን መብት ማስጠበቅ ካልቻለ፤ እንዴት “ዲሞክራሲ” የዜጎችን መብት ሊጠብቅ ይችላል። ዲሞክራሲ ሕግ አይደለም። ሕግ የዲሚክራሲ ጠባቂ ነዉ። ጠባቂ በሌለበት ደካማዉ ተቋም በራሱ መቆም እና መከላከል አይችልም። ሕግ እና ዲሞክራሲ አለ ባሉን የኢትዮጵያ ምድር ዜጎች ይደበደባሉ፤ይዘረፋሉ። መደብደብ አልቀረለትም፤መገደል አልቀረለትም። እነዚህ ሁሉ ሰብአዊ መብቶች ናቸዉ። ነገር ግን ተጥሰዋል። እነዚህ ሰብአዊ መብቶች በሚጣሱበት አገር ላይ “መናገር፤መጻፍ መሰብሰብ መቃወም እና መደራጀት” የምትችለዉ በየትኛዉ ታምራዊ መንገድ ነዉ? የትኛዉ ነዉ መቅደም ያለበት? እነዚህ የሚሰሩት እኮ ሕጉ ሲሰራ ነዉ። ዲሞክራሲ የሚንቀሳቀሰዉ “በሕግ የደም ስር ዉስጥ ነዉ” ።ቀዳሚዉ ተቋም መሰረቱ እየተጣሰ ስለ ሁለተኛዉ መንፈስ ስለ “ማልቲ ፓርቲ” ላዉራችሁ ሲለን ‘የንቀቱ፤የማይምነቱ ብዛት’ *ክት* የለዉም።
እኛ ፓርቲ እና ዲሞክራሲ መመስረት መብት አይነሱ ማለታችን አይደለም። እያልን ያለነዉ- የሕግ ተቋማት ዜጎችን ያገልግሉ፡ ነዉ የምንለዉ። መብቴ ተከብሮልኛል፤ ገዢዉን መደብ በድምጽ አሸንፈዋለሁ ወደ ሚለዉ ፖለቲካዊ እምነት የሚከደዉ እኮ ሕጉ ሲሰራ ነዉ። የዲሞክራሲ መብታችን ከመጠየቃችን በፊት እንደ ዜጎች “ሕጋዊነታችን” በሕግ ጥላ ስር ምን ያህል አጥልሎናል? ሕግ የዲሞክራሲ ምርኩዝ ነዉ፡ ሙርኩዙ ከተሰበረ ዲሞክራሲ አይሰራም፤እሩቅ መራመድ አይችልም።
ባለፈዉ የኢህአዴግ የመጀመሪያ አመታቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ፍትሕ ፍለጋ የጎጃም ገበሬዎች ከጎጃም በእግር በመከራ ተጉዘዉ አዲስ አበባ ድረስ በመምጣት ያካባቢያቸዉ አስተዳደር በብልሹነቱ ሕግ በመጣስ ተጭኖናል፤ፍትሕ ኩፍኛ ተዛብቷል በማለት አቤቱታቸዉን ባሰሙበት ወቅት፦ የአዲስ አበባ ወጣት ተማሪዎች ከጎናቸዉ በመቆም ምግብ እና ዉሃ ከማቅረባቸዉ ሌላ በአብዩቱታዉም ጭምር ሰላማዊ ሰልፍ በመደገፍ አብረዋቸዉ ስለጮሁ፦ -አስቀድሜ በቃለመጠይቁ ላይ “መዶሻ” የሚባሉ ልዩ ታጣቂ የሰዉ ጭንቅላት ለመፈርከስ ለመቀጥቀጥ በሰለጠኑ ልዩ ሃይሎች ተይዘዉ ራስ ቅላቸዉን በሰደፍ እና በዱላ እየተቀጠቀጡ “ሸጎሌ” በሚባለዉ ቦታ ታፍሰዉ ታስረዉ “ሌሊት-ሌሊት” እየተደበደቡ በዛዉ ብርድ በላያቸዉ ላይ “ዉሃ” እየተደፋባቸዉ፤ በዉሃዉ ብዛት ከረጠቡ በሗላ በማግስቱ አፈር በበዛበት መረት እና ጠጠራማ መሬት እንደ አህያ “ተንከባለል!” እየተባሉ በአመድ ላይ እንዲንከባለሉ በማድረግ ዉሃዉ እና አመዱ ልብሳቸዉን በጭቃ ለዉሶ “ተነስ፤ተኛ፤ተንከባለል፤ሩጥ!!” እያሉ የትምርት ቤት ህጻናትን በጭካኔ እየተቀጠቀጡ ለስቃይ ተዳርገዉ፤ አንዳንዱም ለአካለ ጎዶሎነት ተዳርገዋል። ይህ ተግባር የሚፈጽሙት ደግሞ እነ “ገዛኢ-ገብረአነንያ” ናቸዉ። ገዛኢ ገብረአነንያ ደግሞ ሌቦች እና ወረበሎችን መሳሪያ እያስታጠቀ ዝረፉ እያለ ሲያሰማራቸዉ ነበር ብለን አስቀድመን የተወያየንበት የወያኔ ከፍተኛ ፖሊስ ኮሚሽነር ነዉ።
እናንተ “ትምክህተኞች” እያለ በ18፣ 19፣ 20 የዕድሜ ክልል ዉስጥ ያሉት ህጻናት ተማሪዎችና ልጃገረድ ተማሪዎችን በዱላ ቀጥቅጧቸዋል። በብረት ሰደፍ እየገጩ “ይቅርታ ጠይቁ!” “አጥፈተናል ብላችሁ እየፈረማችሁ ጠይቁ!!” እያለ ካስጨነቃቸዉ በሗላ፤- “አጥፍተናል መንግስት በድለናል ብለዉ ተማሪዎቹ ጽፈዋል ተብሎ፡ በአዲስ አበባዉ ከንቲባ በአቶ ዓሊ አብዶ የይቅርታ ጽሁፍ ተናጋሪነት በኩል “ጥፋተኞች ነን ይቅርታ ይደረግልን” ብለዋል ተብሎ ሕግን በመጣስ ለሕዘብ እንዲነገር በሕዝብ መገናኛ አስተላለፉት።
እንግዲህ ተማሪዎች የመሰብሰብ እና የሰላማዊ መንገድ ተከትለዉ ከገበሬዎቹ ጋር ቆመዉ አቤቱታቸዉን ለዓለም ማስተጋባት መብታቸዉ መሆኑ እየታወቀ- ፍዳቸዉ እንዲያዩ ፤አካላቸዉ እንዲጎድል ከተደረገ ሕግ ተጥሷል እና የሕግ የበላይነት የለም። ቢኖር ኖሮ ተማሪዎቹ ባልታገዱ፤ሲታገዱ እና ሲጎዱ መክሰስ እና መብታቸዉን ማስከበር “ካሳ” መጠየቅ መብታቸዉ ይሆን ነበር። መንግስት እና አድማ በታኝ ፖሊሱ ተማሪዎች እና ለገበሬዎቹ እንዲሁም ለተማሪዎቹ ወላጆች “ይቅርታ” መጠየቅ ነበረበት። አልሆነም። ለምን? ሕግ ከታች ፖለቲካዉ ከላይ ሆኖ ወያኔ ሕጉን እንዴት ለራሱ መገልገያ ስለሚጠቀምበት ነዉ።
ፖሊሱን ስትፈልግ “ግደል” ስትፈልግ “ዝረፍ” እያለ በዜጎች ሕይወት እና ኑሮ ነጻ እርምጃ ያስወስዳል። የፖሊሱ ሃይል ለግል መገልገያዉ አድርጎታል። አንድ ተከሳሽ ከፍርድ ቤት እንዲቀርብ ለጥያቄም ሆነ ‘ክስ’ ተመስርቶበት መጥሪያ ከማግኘቱ በፊት- ፖሊሱ ከእላይ ካሉት ባለስልጣኖች ታዝዞ ይዞ ለድበደባ ይዳረገዋል። ይደደበድበዋል! አካሉ ያጎድለዋል! ፖሊሱ የፈለገዉ አድርጎ ሲለቀዉ “ጠያቂ” የለዉም።
ስለዚህ ዲሞክራሲ ለማስፈን ፤ዜጎች ሰላማዊ አድማ ሲመቱ - የሰለጠነ አግባብነት ያለዉ አድማ በታኝ (መበተን ሕጋዊ ሆኖ ከተገኘ) የፖሊስ ሃይል በቦታዉ መንግስት ሲያሰማራ ነዉ ዲሞክራሲ ተከብሯል ሕጉ እየሰራ ነዉ የሚባለዉ። የኢሕአዴግ በታኝ ፖሊስ ግን የሚሰለጥነዉ “እርምጃ” እንዲወስድ ነዉ። “መበተን” ሳይሆን የሚያዉቀዉ “መግደል” ነዉ። መበተን እና መግደል ልዩነቱ ጭራሽ አያዉቀዉም። መግደል እና መበተን ለየብቻ ናቸዉ። ዓለም አቀፍ ሕጉ የሚለዉ አድማዉ የዜጎቹ እና የአገሪቷን ሕልዉና የሚፈታተን ከሆነ አስጊነቱ ታይቶ “በትን” ነዉ የሚለዉ እንጂ “ግደል” አይልም። የወያኔ ፖሊስ ግን ልዩ ነዉ። “በታኝ” ሳይሆን “ገዳይ” ነዉ። ”Special Commando” ነዉ። ወደ ጦር ሜዳ የሚሄድ ልዩ ኮማንዶ ነዉ የሚመስለዉ። የተለያየ ስም አለዉ። ጭካኔ 17፤ጭካኔ 18፤ ላዉንቸር ወዘተ …የሚባሉ ሃይሎች አሉት።እነዚህ ለአድማ ብተና ሲሰማሩ ላዉንቸር ይዘዉ ተኩሶ የመግደል ትዛዝ እና መብት ተሰጥቷቸዉ ተጠቅመዉበታል።
ላዉንቸር- በጦር ሜዳ ዉስጥ የሚተኮስ ከባድ ጥይት ነዉ። ወያኔ ግን በሰላማዊ ዜጎች ላይ በ አድማ ወቅት ተኩሰዉ ህጻናትን እና ተማሪዎችን እንዲገድሉበት ይታዘዛሉ። እነዚህ ጭካኔ 17፣ ጭካኔ 18 ፤ላዉንቸር እና ወዘተ የሚባሉ ቡድኖች አድማን ለመበተን ሳይሆን የሚሰለጥኑት ለመግደል ነዉ። ይህ ደግሞ የዜጎችን መብት የሚጻረር ነዉ። ለዜጎች ያልቆመ ለሕግ የበላይነት ለማስከበር ሳይሆን የተቋቋመዉ የገዢዎች መገልገያ እንዲሆን ሆን ተብሎ የተዋቀረ ነዉ። ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶች እንዲከበር ከመሰረቱት እና ከፈረሙት መሃል አንዷ ናት። ያችን አገር ነዉ ወያኔ እየገዛት ያለዉ። በዚህ አንጻር በፖሊስ እና በደህንነት ክፍሎች ዜጎች እየታፈኑ በጭካኔ ያለ አግባብ ሕግ አልባ እየተያዙ እንዲሰወሩ እና እንዲገደሉ እንዲደበደቡ እና እንዲጨፈጨፉ በተፈቀደበት ተጠያቂነት በሌለዉ ሕግ አልባ ስርዓት የምንኖር መሆኑን እያወቅነዉ “የማልቲ-ፓርቲ” ሲሰተም ከመሰረቱት አገሮች አንዷ በኢሕአዴግ የምትመራ ኢትዮያጵያ ናት ብሎ ሳያፍር ለዓለም ሲዋሽ የ“ሕግ” እና ከሕግ ጋር ንክኪ ያላቸዉ ምሁራን እና ባለሞያዎች ዉሸቱን ሲያደምጡ ልቦናቸዉን ምን ያህል እንዳሳዘነዉ የሚያዉቀዉ ያዉቀዋል።ወያኔ ያችን አገር የሚመራት በእንደዚህ ዓይነት የሕግ ረገጣ ነዉ"። በሚቀጥለዉ ክፍል 4- ስለ ታጋዮቹ መልሶ ማቋቋም እና በንግድ ቤቶች እና በክራይ ቤቶች የታየዉ አድልዎ ይቀርባል። ይቀጥላል…