Sunday, June 27, 2010

ይድረስ ለጎጠኛዉ መምህር አዲስ መጽሐፍ ደራሲ ጌታቸዉ ረዳ

ሁለት መጻህፍት ገበያ ላይ ዉለዋልደራሲ ጌታቸዉ ረዳ (408)561-4836 getachre@aol.com መግብያ ቀደም ብሎ ያሳተምኩት የትግርኛ መጽሐፍ በሕትመት ብልሽት ምክንያት መስተካከል ያለባቸዉ ገጾች በማስተካከል ላይ እንዳለሁ በወያኔዉ ታጋይ በአታኽልቲ ሓጎስ የተጻፈ “አይንተሓማመ”-የሚል መጽሐፍ አንድ የኔ ቤተሰብ ከመቀሌ ይዞልኝ መጥቶ እሱን አንብቤ ስጨርስ ስለ መጽሐፉ ጎሰኛነት አዉሮጳ ሃገር ለሚኖር ወዳጄ ሳነጋግረዉ፤ ወዳጄም በማከል “ማንም ይሁን ምን በወያኔዉ ታጋይ በመምህር ገብረኪዳን ደስታ የተጻፈ የትግራይ ሕዝብ እና የትምክሕተኞች ሴራ ከትናንት እስከ ዛሬ”መጽሐፍ በጣም አስቀያሚ የሆነ መጽሐፍ ታትሞ አያዉቅም ፤እሱን ፈልገህ ማንበብ ይኖርብሃል”ሲለኝ የመጽሓፍ ምንነት ካሁን በፊትም ከሌሎች ሰዎች ተነግሮኝ ስለነበር፤መጽሐፉን ፈልጌ ለማንበብ ጉጉት አድሮብኝ ስፈልግ ብዙ ጊዜ ፈጅቶብኝ እዚሁ ሳንሆዜ ከተማ የሳንሆዜ ቤይ ኤርያ የኢትዮጵያ ራዲዮ ዋና አዘጋጅ ወዳጄ ኢንጂኔር አበበ ሃይሉን ስጠይቀዉ በእጁ እንደሚገኝ እና እንደሚሰጠኝ ቃል ገብቶልኝ፤ ሰጥቶኝ -ከመጀሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ ያሉት አንድ ባንድ ለማንበብ ሞክሬ የመጽሐፉ ጸረ አማራነት፤ትምክሕቱና የተዛባ የታሪክ አቀራረቡ ህዋሳቶቼ ክፉኛ ስለተፈታተኑት ከገጽ ወደ ገጽ ስሸጋገር ጥርሴን ነክሼ በመከራ ነበር አንብቤ የጨረስኩት። ደራሲዉ መምህር ገብረኪዳን ደስታ “በ1998 ዓ.ም. የጻፈዉ “የትግራይ ሕዝብና የትምክሕተኞች ሴራ ከትናንት እስከ ዛሬ”መጽሐፉ አጼ ምኒልክን በትግራይ ደመኛነት፤በከሃዲነት፤ለባዕድ ያደሩ ቅጥረኛ፤ወደ ዓድዋ የዘመቱት በወቅቱ ከማንኛቸዉም አካባቢ በጥሬ ገንዘብ (ብር)እና በከብት ቀንድ ሃብት ሓብታም የነበረችዉን ትግራይ ለመዝረፍ እና በጎሳ ፤በነገድ፤በቀለም ልዩነት የማያምነዉ ንፁህ የትግራይን ሕዝብ የአዉራጃዊነት ስሜት እንዲያድርበት በማስተማር እርስ በርሱ እንዲጋጭና ሃያልነቱን ለማዳከም እና ለማንበርከክ አቅደዉ በትግራይ ሕዝብ ብዙ በደል ፈጽመዋል በማለት ይከ’ስሳቸዋል።ደራሲዉ ምኒልክን በጸረ ኢትዮጵያዊነት እና በሃገራዊ ክሕደት የኮነናቸዉን ያህል በአዲስ አበባ ከተማ በየወሩ እና በየቀኑ የሚታተሙ የግል መጽሄቶችና ጋዜጦችም እንዲሁ “ጋዜጦቹ የትምክሕተኞች ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ የሚታተሙ ናቸዉበማለት የግል ጋዜጦችን ይከ’ሳቸዋል። ጋዜጦቹ በትምክሕት ሃይሎች የሚዘጋጁ ሲላቸዉ “በጀግኖች (የወያኔ ታጋዮች) የዓመታት ተጋድሎና የሕይወት መስዋዕትነት የተገኘዉን የዲሞክራሲ መድረክ ሕዝባችን እርስ በርሱ ለማናቆርና ለማተራመስ ተጠቅመዉበታል” ሲል ይወነጅላቸዋል። ስለዚህም ይላል “ተጋዳላይ” ገበረኪዳን “እነዚህ አህጉራዉያን ትምክሕተኞች በትግራይ ሕዝብ ላይ የሚነዙት የጥላቻና የዕልቂት መርዝ ከዕለት ወደ ዕለት እየከፋ በመሄዱ ነዉ በመጠኑም ቢሆን ማንነታቸዉ ለማጋለጥ በትግርኛ ቋንቋ የጀመርኩትን ስራ ትቼ ይህንን መጽሐፍ በአማርኛ ቋንቋ ለመፃፍ የተገደድኩት። “የያዘዉን ከወረወረ ፈሪ አይባልም” እንደሚባለዉ ነዉና እኔም የትግራይን ሕዝብ ደመኛ ጠላቶች ማንነት በማጋለጥ በኩል ማድረግ የምችለዉን ነገር በማድረጌ የመንፈስ እርካታ ይሰማኛል። ከዚያ በሗላ ግን የትግራይ ምድር ያበቀለቻቸዉ ምሁራን የታሪክ ተወቃሾች ላለመሆን የትምክሕተኞችን የዉሸት ብዕር በማሽመድመድ የትግራይን ሕዝብ ሐቀኛ ታሪክና ማንነት በአግባቡ እየመዘገቡ ለቀጣዩ ትዉልድ የማስተላለፍ ህዝባዊ ግዴታ አለባቸዉ። በሌላ አነጋገር “ትግሬ ታሪክ ይሰራል እንጂ ታሪክ አይጽፍም”የሚሉትን የትምክሕተኞች የትናንቱ ፌዝ ነገና ከነገ ወዲያ በትግራይ ምሁራን የሚሰነዘር ተሳልቆ ሆኖ መቀጠል አይኖርበትም…”(ገ/ኪዳን ደስታ -በምጽሓፉ መግብያ ላይ ካሰፈረዉ)። በማለት የትግራይን ምሁራን ዉሸት እንዲዘግቡ፤ጸረ አማራነት ፤ ጸረ አንድነት እና ጸረ ኢትዮጵአዊነትን የሚሰብኩ መጻሕፍቶች እንዲጽፉ ተማጽኗል። እኔም በትግራይ ተወላጅነቴ አሁን ያለዉ ወጣት ትዉልድና መጪዉ ትዉልድ የመጽሐፉን አደናጋሪነት እና መሰሪነት፤ትምክሕትና ጠባብ የጎሰኛነት ስሜት እንዳይመርዘዉ የእነ ገብረኪዳን እና የወያኔ የዉሸት ቅስቀሳዎች፤አናካሽ ስለቶቹ እንዳይቀጥሉ ሕብረተሰቡ በራሱ ጐሰኞች ላይ የጠነከረ እና የጠራ አቋም ለመዉሰድ እንዲረዳዉ የበኩሌን ሃላፊነቴን ለመወጣት ይህ መጽሃፍ ለትዉልድ ኣስተላልፌያለሁ። እኔ አክሱም ተወልጄ ፤ አክሱም አድጌ፤ እትብቴ አክሱም አፈር ላይ ተቀብሯል።የአክሱም ተወላጅ ነኝ። አከላቴ ሁሉ የተገነባዉ በአክሱም ዓየር ዉሃ እና እህል፤ባህል፤በበጎ አክሱማዊ የሃይማኖት ስነምግባር ታንጾ ያደገ፤ አሁንም መንፈሴን ያነፀዉ አክሱማዊ ቅብኣ ሜሮን ጠረኑ አልለቀቀኝም። ሕሊናየ ሁሉ ትናንትም ዛሬም አሁንም ለወደፊቱም እዛዉ ባደግኩበት እትብቴ አድሮ ጥዋት አሜሪካ ተመልሶ አገኘዋለሁ። ወያኔ የመሰረቱ አብዛኛዎቹ አብሮ አደጌ ወይንም የትምህርት ጓዶቼ ናቸዉ። ገብረኪዳንም እንዲሁ እንደ እኔ የትግራይ ተወላጅ ዓድዋ ተወልዶ ዓድዋ ያደገ ነዉ። ሁለታችንም ያደግንበት መንደር በመኪና የ30፡00-የሰላሳ ደቂቃ ርቀት ነዉ። ስለዚህ ትግራይ እና የትግራይ ስቃይ እና ብልጽግና የምናዉቀዉ እኩል ነዉ። ልዩነታችን በኢትዮጵያዊነታችን ላይ ያለዉ እይታና ራዕይ ነዉ።አሁን ወያኔን የሚመሩ እና የሚከተሉዋቸዉ አብሮ አደጎቼ፤- ገና አብረን ስናድግ እንዲህ ዓይነት የታሪክ ዓመጽ ይፈጽማሉ የሚል ሕልምም ምልክትም አይታያቸዉም ነበር (በጣም ከጥቂቱ በቀር)። እንዴት እንዲህ የጠላት አስደሳችና አስፈጻሚ ሊሆኑ እንደቻሉ ለኔ እንቆቅልሽ ነዉ። ልዩነታችን በሁለት ተቃራኒ እምነቶች እና እይታዎች የተሰመረ ነዉ። በማሃላችን የለየን በቀይ መስመር የተሰመረ የሞትና የሽረት ትንንቅ የሚካሄድበት የመግደያ መስመር አለ። በመግደያዉ መስመር ላይ ኢትዮጵያን ለመግደል የሚያጠምዱበት ሙት የመግደያ መሬት ነዉ። ቅራኔየ አገሬን ከመግደያዉ መስመር ለማስገባት ሌት ተጠቀን ከሚጥሩ ከሃዲዎች ጋር ነዉ። ልዩነታችን የርዕየተ ዓለም ልዩነት ብቻ ሳይሆን አገርን በመግደልና በመከላከል ላይ ያለ ልዩነት ነዉ። ትግራይ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ነች የሚል ቅዠት ቃዥቶ ፯ በመታገያዉ ደብተሩ ላይ ያስተማረ፤ ራሱን ከድቶ የትግራይን ሕዝብ ለማስካድ ከሚቃዠ ቡድን እና፤ ስልጣናችን ከተቀማን ኢትዮጵያን እንበታትናታለን፤ትግራይን ከኢትዮጵያ እንገነጥላለን፤ መንድር መንደራችንን እንይዛለን ከሚለዉ አገር ገዳይ፤ እትብትና የቤተሰብ ሐረግ ከበጣጠሰ እና ዛሬም ትግራይን እና ሌላዉን ለመበተን ዛቻዉ ያልበረደለት ጸረ አማራ ሃይል ከሆነ የጥላቻ ቡድን ጋር ነዉ። ልዩነታችን ጎሰኝነትን ለማስፋፋት ብዙ ሺሕ የትግራይ ወጣቶችን ሕይወት በጦርነት ማግዶ ለጥቂት የወያነ ትግራይ “ዘበናይ መሳፍንቶች” የስልጣን ማመቻቺያዉ ካደረገ ቡድን ጋር ነዉ። ትግሌ አገሬንም ሆነ እትብቴ የተቀበረባትን ከተማና ቤተሰቦቼን እንዳልጎበኝ በጠመንጃ ከሚያስፈራሩኝ ሕግ አልባ የወያነ ትግራይ መሳፍንቶች ጋር ነዉ። ባጠቃላይ ትግሬነቴን በመግፈፍ “ሸዋዉያን ተጋሩ”በሚል ስም ሰይሞ በአማራዉና በትግሬዉ መካከል ጥላቻና ጎሰኛነትን መመርያዉ ካደረገ የትግሬነታችንን ትዉልደ ሐረግ ሰጪ እና ከልካይ አድርጎ ራሱን ከሾመ አጥንት ቆጣሪ ጎሰኛ ቡድን ጋር ነዉ። ምኒልክ የሸዋ ሰዉ ናቸዉ፡ ሸዋነታቸዉ እንደ የትግራይ ጠላት አያስቆጥርባቸዉም። ምኒልክም ሆኑ የሸዋ፤የጎጃም፤የወሎ፤የጎንደር አማራዎች የትግራይ ደመኞች ሳይሆኑ “የክፉ ቀን ወዳጅ”መመክያ እና “በክፉ ቀን ድረሱልን ተብለዉ የደረሱ፤ ትናንትም ዛሬም ለወደፊቱም ለትግራይ ሕዝብ አጋርነታቸዉ የማይታጠፍ ኢትዮጵያዉያን፤ የትግራይ ሕዝብ የደም፤የስጋና የአጥንት ዘመዳሞች ፤የባሕል እና የሕሊና ትስስሮቻቸዉ ከአንድ ዘር ኢትዮጵያዊ ትዉልድ እና አገር አብራክ የተወለዱ ናቸዉ።ስለሆነም “የትግራይ ህዝብና የትምክሕተኞች ሴራ ከትናንት እስከ ዛሬ”ዳራሲ ተጋዳላይ መምህር ገብረኪዳን ደስታም ሆነ የሚያመልከዉ የራሱ ድርጅት “ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ” በአማራዉ ሕዝብ እና በጠቅላላ ላገሪቱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ላሳዩት የትምክሕት ባሕሪያቸዉና ንቀት እንዲሁም ለአናካሽ ሴራቸዉ ሁሉ ይቅርታ መጠየቅ ይኖርባቸዋል እላለሁ። የትግራይ ነባር ታሪካችን ወያነ ከሚያስተምረዉ የተዛባ ትምህርት እጅግ ተቃራኒዉ ነዉ።የአክሱሟ ታቦተ ጽዮን በጠላት ስትፈለግ ለአክሱም መኳንንቶች፤ቀሳዉስቶች፤ንጉሡ እና ለንጉሣን ቤተሰቦቹ የሸዋ ሕዝብና ዋሻ ነበር አጋር ሆኖ በአክብሮት አኑሮ ከጠላት የተከላከለዉ። አምበሳ ዉድም በሃይለኛዋ ጠላት በአገዋ ንግሥት እንዲገደል ሲፈለግ ከአክሱም ሸሽቶ መጠለያዉ ያደረገዉ ያዉ ሸዋ ነበር። ታዲያ ሸዋ ወይንም የአማራ ሕዝብ እንዴት በጠላትነት ተቆጥሮ በወያኔ የዘረኛ መርሕ ያላመንን አንዳንዶቻችን የትግራይ ተወላጆች “የሸዋ ትግሬዎች” ተብለን ሸዋን አንደ ዓይነተኛ ጠላት ተቆጥሮ የቅጽል ስም ይሰጠናል? በዚህ አጋጣሚ ለትግራይ ተወላጆችና ምሁራን የማስተላልፈዉ መልዕክት ሌላዉን በዘረኝነት እየከሰሱ የራስን ጉድፍ ሳያዩ በሌላዉ ዓይን ላይ የሚታየዉን ጉድፍ ለማመላከት የሚጥሩት ወያኔዎች ለ36 ዓመት ያስተጋቡትን ጸረ አማራ ቅስቀሳቸዉ ፰ እንዲያቆሙ ይረዳ ዘንድ የትግራይ ተወላጆች ግልጽ አቋም እንዲይዙ እጠይቃለሁ። ጸረ አማራነታቸዉና አልፎም በትግራይ ዉስጥ በአዉራጃዊነት ባምቻ ጋብቻ በአጥንት በደም በወረዳ በወንዝ ትስስር በጎጠኛነት የተለከፉ መሆናቸዉ እኛ ወያኔን በምንቃወም የትግራይ ተወላጆች ብቻ ሳይሆን ወያኔን ከመሰረቱ ከፍተኛ መሪዎች እና አብዛኛዉ ታጋይ የነበረ ሁሉ በግልጽ የወያኔ ዘረኛነት አጋልጠዋል። ወያነ ትግራይ በስማችን ብዙ ወንጀል ፈጽሟል። ወያነ ትግራይ እጅግ ሲበዛ ጐሰኛ እና ፋሽስታዊ ድርጊቶችን አከናዉኗል። በሃገር ክሕደት ቀዳሚዉን ማሕደር ይዟል።የትግራይ ተወላጆች ቆም ብለን ማሰብ እና ኢትዮጵያዊነታችንን፤ሉዓላዊነታችን እና ሰንደቃላማችንን ያረከሰዉን ወያኔን መቃወም የታሪክ ግዴታችን ነዉ።
ወደ መጽሐፌ ይዤያችሁ ከመግባቴ በፊት ወያነ ትግራይ የአማራዉን ሕብረተስብ የሚጠላ ጐሰኛ አይደለም ብለዉ ወያነ ትግራይን ለመከላከል የሚሞክሩ የወያኔ አማኞች ሊኖሩ ስለሚችሉ ማስረጃዉን ለማቅረብ እንዲመች ወያኔን ከመሰረቱት የመጀመሪያዎቹ መስራች ታጋዮች አንዱ አስገደ ገብረስላሴ “ጋህዲ” በተባለዉ በቅጽ 2 የትግርኛ መጽሐፉ ላይ የሰጠንን አንዲት ጠቃሚ መረጃ ወደ አማርኛ ተርጉሜ ካቀረብኩ በሗላ፤ የወያኔ ታጋይ ገብረኪዳን ደስታ “የትግራይ ሕዝብና የትምክሕተኞች ሴራ ከትናንት እስከዛሬ” በሚለዉ ጎሰኛ መጽፉ ላይ የአማራዉ ሕብረተሰብና አጼ ምኒልክን “የትግራይ ደመኞች” በማለት የከሰሳቸዉን ክሶች ተቀባይነት እንደሌላቸዉና መጀመሪያ ወያኔ የራሱን ጎሰኛ እና ፋሺስታዊ ባሕሪ መፈተሽ እንደሚኖርበት የተከራከርኩበትን ወደ “ይድረስ ለጎጠኛዉ ምመህር”መጽሐፌ ይዤያችሁ እገባለሁ።
<<ህወሓት በ1969 ዓ.ም. የካቲት ወር ወደ በረሃ ሲወጣ የብሔር ጭቆና እና የመደብ ጭቆና በመቃወም የብሄሮች መብት በራስ የመወሰን መብት ለማረጋገጥ እኩልነትና አንድነት የተረጋገጠባት ኢትዮጵያ ለማምጣት ያለመ ነበር። ከጥቂት ጊዜ በሗላ የተገለጸዉ ዓላማዉን ሰርዞ <<ጥያቄያችን ሃገራዊ ጥያቄ ሆኖ ከባዕድዋ ቅኝ ገዥ ኢትዮጵያ ነፃ ወጥተን ነፃ አገር ለመመስረት ነዉ እየታገልን ያለነዉ። “ምስ አምሓሩ ሓቢርካ ምንባር አይካኣልን”ከአማራዎች ጋር አብረህ መኖር አይቻልም (ጋህዲ ቁጥር 2 ገጽ 136)”>>የሚል መተከል ቀረበ።(ጋህዲ ቁ 2 ገጽ 136-የትግርዉን ቅጅ ይመልከቱ)። እንደዉም ከነጭራሹ ይላል አስገደ ገብረስላሰ በጋህዲ መጽሐፉ ላይ << እንደ እነ ኢዲዩ እና ኢሕአፓ ያሉ በትግራይ መሬት ዉስጥ የሚንቀሳቀሱ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ሽምቅ ተዋጊዎች “ከአገራችን” ይዉጡልን እነኚህም የትግራይ ጠላቶች ናቸዉ፡ ብለን ለትግራይ ሕዝብ እናስተምረዉ። ጥያቄያችን “አገራዊ” (የኮሎኒ ጥያቄ) ስለሆነ ከእነኚህ ድርጅቶችም የጊዜ ጉዳይ እንጂ ዉለን አድረን ጦርነት መግጠም ስለማይቀረን፤ልክ እንደ ደርግ እነሱም ጠላቶቻችን ናቸዉ።ከነጭራሹ “አማራዎች” ከአገራችን ይዉጡልን…>> (ጋህዲ ቁ 2 ገጽ 137 )
<<…በማለት ኢትዮጵያዊ ፓርቲዎች በገዛ አገራቸዉ ትግራይ ዉስጥ የመንቀሳቀስ መብታቸዉን የሚጻረር/የሚያግድ አቋም ይዞ ተንቀሳቀሰና፤እንዳለዉም ከተጠቀሱት ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች አመቺ የመምታትና ከሕዝቡ የመነጠል ሁኔታና ሴራ እስኪያመቻች ድረስ ድርድር እናድርግ እያለ ሲደራደር ቆይቶ ራሱን ካደላደለ በሗላ፤ አቅሙን ገንብቶ አስተማማኝ ደረጃ ደርሶ፤ መጨረሻ ወደ ጦርነት በመግባት ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ከተባሉት ሁሉ የነበረዉ ቅራኔና ግንኙነት በጦርነት ደመደመዉ”>> ጋህዲ ቁ-2-ገጽ 137 ትግርኛዉ ቅጅ)። <<ኢህአፓ በአጋሜ አዉራጃ ዉስጥ በአሰፈ ሰበያ እና በወረዳ ጉሎ ሞዀዳ በወያነ ትግራይ የጠባብነት ጨረታ አሸናፊነት ተበልጦ ከትግሉ ከወጣ በሗላ ።ከዚያ በሗላ የጠባብ ብሔረተኝነት በሽታ በመላዋ ትግራይ እንደ ተላላፊ በሽታ ተስፋፍቶ ወደ ሕዝቡ በመተላለፉ አብዛኛዉ የትግራይ ሕዝብ ፀረ አማራ ተንቀሳቀሰ።”>> (አስገደ ገ/ስላሴ የወያኔ የመጀመሪያ መስራች አንዱ፦ ጋህዲ ቁ/2 ገጽ 155 የትግርኛዉ ቅጂ 2001 ዓ.ም.) ዉድ አንባቢ ሆይ! ይህንን.እጅግ-አሳፋሪ፤ፋሺስታዊ፤ጸረ-ኢትዮጵያ፤ጸረ-አንድነት፤ሃገራዊ-ክህደት፤ጠባብ ጐሰኛነቱና ትምክህቱን ስንመለከት፤“ትግራይ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ነች!” “አማራዎች ከትግራይ መሬት መዉጣት አለባቸዉ!” “እኛ ትግሬዎች ከአማራ ሕዘብ ጋር መኖር አንችልም!” በማለት የትግራይን ሕዝብ ኢትዮጵያዊነት በመካድ በመመርያዉ አስፍሮ ያስተማረ ወያኔ ሌላዉን ትምክሕተኛ ወይንም ዘረኛ በማለት አፉን ሞልቶ የሚናገርበት ሞራል አለዉን? ወደ ታሪኩ ይዤያችሁ ልግባ። ደራሲዉ ሐምሌ 1 2002 ዓ.ም getachre@aol.com www.ethiopiansemay.blogspot.com ጌታቸዉ ረዳ P.O.Box 2219 San Jose, Ca 95109 ይድረስ ለጎጠኛዉ መምህር ዋጋ $20.00 ጠቅላላ ከነመላክያዉ ሓይካማ! (ትግርኛ - ሌላ ይዘት ያለዉ መጽሓፍ ነዉ) $15.00 ከነመላክያዉ ጠቅላላ ትግርኛዉ ለሁለተኛ ጊዜ ታርሞ የታተመ ነዉ (ከፊተኛዉ በጣም ይለያል)።

Monday, June 7, 2010

በኢትዮጵያ አስደንጋጩ የባሕል ወረርሽኝ

የወያኔ ገበና ማሕደር (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ) በኢትዮጵያ አስደንጋጩ የባሕል ወረርሽኝ ከቀድሞ የኢትኦጵ ጋዜጣ ባልደረባ

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገራችን ኢትዮጵያ አስደንጋጭ ብሎም አሳሳቢ የባሕል “ወረርሽኝ” ስር እየሰደደ መጥቷል። ኢትዮጵያዊያን የምንኮራበትና ደረታችንን ወጥረን የምንናገርበት እንዲሁም ሌሎች ጠንቅቀዉ የሚያዉቁልን ኩሩ የባሕል እሴታችን ከወደ አናቱ መናድና በግልጽ መገንዘብ ጀምሯል። ክርስቲያን ይሁን ሙስሊም፤ባሁላ ሆነ ፕሮቴስታንት፤ካቶሊክ ይሁን ጆሆባ…ብቻ የፈለገዉ ሃይማኖት ተከታይ በእኩልነትና በመከባበር ተቻችለዉ በመኖር የምትታወቀዉ አገራችን የተደቀነባት “ምዕራብ” አመጣሽ የተጨማለቀ ወራዳ “ቆሻሻ” አድማሱን እየለጠጠ በከፍተኛ ደረጃ እየበከላት ይገኛል። በስልጣን ላይ ያለዉ ፈላጭ ቆራጩ የመለስ ዜናዊ አስተዳደር፤ ለአገር ክብር፤ ለዜጎች መብትና ነፃነት ለባሕልና ታሪክ የሚሰጠዉ ግምት የተንጠፈጠፈ ዝቃጭ ዓይነት በመሆኑ አሁን እየተንሰራፋ ላለዉ ወረርሽኝ ቅንጣት ታክል ይቆረቁረዋል ተብሎ በጭራሽ…በጭራሽ…በጭራሽ!... አይታሰብም። እንዲያዉም ለነዚህ የባሕል ወረርሽኝ አደጋዎች የእጅ አዙር ድጋፍ በተዘዋዋሪ መንገድ እየሰጠ ያለበት ተጨባጭ እዉነታ እንዳለ ታይቷል። የመለስ ዜናዊ መርሕ “ማንም ግለሰብና ቡድን በኢትዮጵያ ምድር ያሻዉን የዘረፋ ወይም ሙስና ስልት ማራመድ ይችላል። ያሻዉን እምነት ማራመድ በቡድን ተደራጅቶም መንቀሳቀስ ይችላል። ነገር ግን በአራት ኪሎ ቤተመንግሥት ዙርያ የተሰመረዉን ቀይ መስመር ማለፍ አይቻልም” የሚል ነዉ። የህ ማለት ማንም ግለሰብና ቡድን በመለስ መንበረ ስልጣን ዙርያ ከመጣና ፖለቲካዊ ይዘት ያለዉ የተቃዉሞ አቋም ሲያራምድ ከታየ አደጋ ሊከተለዉ እንደሚችል በማያሻማ መልኩ ደንግጓል። በገሃድ የሚታይ በመሆኑ ማስረጃዎች መዘርዘር የሚያስፈልገዉ አይመስለኝም። የመለስ የዘቀጠ “አቋም” ይህ ስለሆነ ነዉ አደጋዉ እየከፋ የመጣዉ “የባሕል ወረርሽኝ ምንድነዉ?’ ለምትሉ ዝርዝሩ ይኸዉላችሁ።በ ኢትዮጵያችን በተለይም በመዲናችን አዲስ አበባ ግብረ-ሰዶማዊነት ከሚታመነዉ በላይ እየተስፋፋና በአስደንጋጭ መልኩ በግልፅ አደባባይ መዉጣት ከጀመረ እነሆ አምስት አመታት ደፈኑ። በተለይ ከ1998 ዓ.ም. ወዲህ እየተስፋፋ የመጣዉ የግብረሰዶማዊያኑ ብዛት ከዕለት ወደዕለት መጥቷል። ከተጠቀሰዉ ጊዜ አንስቶ በአዲስ አበባ መሰማት የጀመረዉ ዜና “የ10፤9፤8…ዓመት ዕድሜ ያላቸዉ ታዳጊ ሕፃናት አንድ የካናዳ ዜግነት ባለዉ ግለሰብ (ነጭ) በደረሰባቸዉ መደፈር ለከፍተኛ የስነልቦና ኹከት እንደተዳረጉ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነዉ። በተለያዩ የመደለያ ስልቶች በማባባል ታዳጊ ሕፃናቱን “አሜሪካና ዉጭ አገር እንወስዳችሗለሁ፤ገንዘብ እመድብላችሗላሁ…” እያለ ሃያ (20) ታዳጊ ሕፃናት እንደደፈረ የችግሩ ሰለባዎች በነፃዉ ፕሬሰ በሰጡት ጥቆማ በወቅቱ ተጋልጧል። ታዳጊዎቹ ከ10 እስከ 14 የዕድሜ ክልል ሲሆኑ፤የስነልቦና ቀዉስ የተፈጠረባቸዉ በዕድሜ ከፍ እያሉ ሲሔዱ ነበር። ያ ወንጀለኛ ለአንድ ወር ታስሮ በዋስ በመለቀቁ ከአገር መዉጣትና ማምለጥ እንደቻለ ወቅቱ ተገልጿል። የሚገርመዉ ስለሰለባዎቹ ታዳጊዎች ጉዳይ ሰምተዉ እንዳልሰሙ የሆኑት የመንግሥት መገናኛ አዉታሮች “ጅብ ከሔደ…” እንደሚባለዉ ዜናዉን እየተቀባበሉ ያሰራጩትና በባዶ ሜዳ ሲቦርቁ የታዩት ወንጀለኛዉ ከአገር ከወጣ በሗላ ነበር። ይህ ግለሰብ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በኬኒያ ባንዳንድ የምስራቅ አፍሪካ አገራት ተመሳሳይ ወራዳ ወንጀል ሲፈፅም እንደቆየ ተደርሶበታል። አሁን ያለዉ ተጨባጭ እዉነታ ደግሞ ከተገለጸዉ በላይ አስጊ ሆኗል። ግብረሰዶማዊያን ማሕበር (ቡድን) እስከ መደራጀት ደርሰዋል። ከላይ እንደጠቀስኩት የመለስ አስተዳደር ምን አቋም እንዳለዉና እንደሚከተል ጠንቅቀዉ የተረዱ ግብረሰዶማዊያን የ2000ዓ.ም. ሚሊኒየም በማስታከክ “ሕጋዊ ዕዉቅና ይሰጠን” እስከማለትና የመለስ ዜናዊን በቀጥታ እስከመጠየቅ ደርሰዋል። ስለዚሁ ጉዳይ ወይም ጥያቄ “ሪፖርተር” ጋዜጣ የዜና ሽፋን በወቅቱ ሰጥቶታል። በዚህ ዙርያ ንዴት የተንጸባረቀበት ምላሽ የሰጡት ፓትርያሪክ አቡነ ጳዉሎስ “ይኸ ክቡር ባሕላችንን የሚበርዝ ቆሻሻ ጥያቄ ነዉ።ግብረሰዶምና ግበረሰዶማዉያን የፈጣሪን ሕግጋት የተላለፉ ናቸዉ። መዝቀት ጭምር ነዉ። ወራዳነት ነዉ>> ሲሉ አጣጥለዉታል። እንደ አቡኑ ባይሆንም የካቶሎክና የእስልምና ሃይማኖት መሪዎች የተለሳለሰ ተቃዉሞ በወቅቱ ሰንዝረዋል። ግብረሰዶማዉያኑ በዚህ ብቻ አልተገቱም። በአገር ዉስጥ ከሚታተሙ የኪነጥበብና ማሕበራዊ ነክ የግል መጽሔቶች ሳይቀር ሕብረተሰቡን የሚንቁ ጽሑፎችን ማዉጣት ይዘወል። አንድ “ቢኒያም” ነኝ ያለ ግበረሰዶማዊ ባወጣዉ መጣጥፍ- በአዲስ አበባ ብቻ 7 ሺሕ (ልብ በሉ ሰባት ሺሕ ነዉ!) ግብረሰዶማዉያን በአንድነት እንደተሰባሰቡና ማሕበር እንደመሰረቱ፤ለሚመለከተዉ የመንግሥት አካል ሕጋዊ ዕዉቅና እንዲሰጣቸዉ ጥረት እያደረጉ መሆኑን (ግብረሰዶማዉያንን (Gay) ገይ በሚገልጽ ሁኔታ በአዲስ አበባ ዕምብርት (በስማቸዉ መሆኑ ነዉ) ትልቅ ናይት ክለብ ለመክፈት አስፈላጊዉ ዝግጅት መጠናቀቁና ለዚህም የሚያስፈልገዉ ገንዘብ በበቂ ሁኔታ መመደቡን፤ አባላቱ ያቋቋሙት ማሕበር የፋይናንስ ችግር የሌለበት መሆኑን፤የበለጠ ለመደራጀት ሲሉ የአባላት ቁጥር በየፊናዉ እየመለመሉና እያበራከቱ መሆኑን እዉቅና ካገኙ በሗላ በስማቸዉ ጋብቻ የሚፈፅሙበት የሃይማኖት ተቋማት (ቸርች) እንደሚመሰርቱ፤ በ2000 ዓ.ም. ጀርመን ከሚገኝ ወንድ ጓደኛዉ ጋር የጋብቻ ስነስርኣት አከናዉኖ መምጣቱን…በሰፊዉ ከዘረዘረ በሗላ አያይዞም “ሕብረተሰቡን እያግለን፤ግብረሰዶማዉያንን ማግለል ይቁም” እያለ በጽሑፍ ዘላብዷል። ይኸዉ ግለሰብ በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ይዘት ያለዉ መጣጥፍ በመጽሔት ያቀረበ ሲሆን በዛዉ ጽሑፍ ያካተተዉ ተጨማሪ ጉዳይ በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች የመዝናኛ ክለቦች ተከፍተዉ በስራ ላይ እንዳሉና ግብረሰዶማዉያን በአንድነት ተሰባስበዉ እንዲዝናኑ ሲባል ታስቦበት የተከፈቱ መሆናቸዉን አክሎ ገልጿል። በጽሑፉ የምሽት ክለቦቹን አድራሻ ያልገለጸ ቢሆንም “ዋና ዋና” በሚባሉ ስፍራዎች እንደተከፈቱና ቁጥራቸዉም የተወሰነ መሆኑን አመልክቷል። አስደንጋጩ የግብረሰዶማዉያኑ ተግባር ከላይ የተገለጸዉን ይመሰላል። እነ መለስ ዜናዊ ላገራችን ባሕል ትኩረት መስጠት፤ የአገራችንን ባሕል በመጥፎ ባሕሪዎች እንዳይበከል የመንከባከቡን ሃላፊነት መዉሰድ ግድ የላቸዉም። ይኸዉም በመረጃ አስደግፎ ቸልተኝነታቸዉን መጥቀስ ይቻላል። “7ሺሕ ግብረሰዶማዉያንን እወክላለሁ” ሲል የፃፈዉ ቢኒያም የተባለዉ ግለሰብም ሆነ ፅሑፉን ያተመዉ መጽሔት በመንግሥት የተጠየቁበት ሁኔታ የለም። የሃይማኖት መሪዎችም በዚህ ዙርያ ትንፍሽ አላሉም።መፅሔቱ አልተጠየቀም ስል ሃሳቦችን የማንሸራሸር መብቱ ይገፈፍ፤ይገደብ፤ይሰቀል…ማለቴ አይደለም። ነገር ግን እንዲህ ያለዉን ባሕል አርካሽ ጽሑፍ ይፋ ሲሆን እነ መለስ ወጣቱን ህብረተስብ ምን ያክል በቁም እየገደሉትና ለወራዳ ርካሽ ወረርሽኝ አሳልፈዉ እየሰጡት እንዳሉ የሚያስረዳዉ በሌላ ጋዜጣ ላይ የወሰዱት እርምጃ በቂ ማነፃፀርያ ነዉ። የኦሳማ ቢን ላዲንን ፎቶ በጋዜጣህ ላይ ልታትም ነበር” በሚል ከማተሚያ ቤት ጋዜጣዉ እንዲታፈን ያደረጉት እነ መለስ ዜናዊ አዘጋጁን የሁለት ዓመት እስራት አከናንበዉታል። እንግዲህ ይታያችሁ የአሜሪካ የሚዲያ ተቋማትን ጨምሮ በመላዉ ዓለም ያሉ መገናኛ ብዙሃን ስለ ቢን ላዲን ሳይዘግቡና ምስሉን ሳያሳዩ ወይም በጋዜጣ ሳያትሙ የቀሩበት ቀን ቢኖር በጣም ጥቂት ነዉ ቢባል አልተጋነነም። የመለስ የግል ይዞታ ተድረጎ የተወሰዱት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ራዲዮና የፓርቲዉ ልሳናት አሁን ድረስ ቢንላዲንን የተመለከቱ ወቅታዊ ዘገባዎች ይፋ ከማድረግ የቀሩበት የለም። ሃቁ ይኸ ቢሆንም የቢን ላዲን ፎቶ ልታትም ነበር የተባለዉ ጋዜጠኛ አዘዲን የሁለት ዓመት እስራት ሲፈረድበት ባሕል ወረርሽኝ አደገኛ ነቀርሳ ግን ያሻዉን እየለቀለቀ ወጣቱን ራሱ እንዳለዉ በገንዘብ ሃይል እየደለለና እየበከለ አገራችንን ቆሻሻ አዘቅት ዉስጥ እየከተታት እየታየ “መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ” ዓይነት የተባባሪነት ምላሽ በነመለስ በኩል ተሰጥቷል። ሌላዉ ነጥብ “አታግልሉን” የምትለዉ አስገራሚ አባባል ትጠቀሳለች። የ ኤች አይ ቪ ኤድስ ሕሙማንና የስጋ ደዌ የአካል በሽተኞች… የመሳሰሉት “አታግልሉን፤መድልዎ ይቁም!” እያሉ በአጽንኦት ማሳሰባቸዉ አግባብ ነዉ። ነገር ግን በኢትዮጵያ ያልነበረና ትዉልድን የሚበክል ቆሻሻ የተሸከሙ የባህል ነቀርሶች ተመሳሳይ የመብት ጥያቄ ሲሰነዝሩ መታየታቸዉና በለየለት ድፍረት “አታግልሉን” ማለታቸዉ ሲታይ እነ መለስ ዜናዊ አባሪ ተባባሪ ሆነዉ በምን ደረጃ ሕዝብን በጅምላ እያዋረዱ እንደሆነ የሚያስገነዝብ ጭምር ነዉ። በሌላ ረገድ ግብረሰዶማዊዉ ግለሰብ በደፈናዉ የጠቀሰዉ የምሽት መዝናኛ ስፍራ በተመለከተ በግሌ ለማጣራት ጥረት አድርጌያለሁ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርካታ የሕብረተሰብ ክፍሎች ስለግብረሰዶማዊያኑ መሰባሰቢያ ባር እንዲሁም ስለ እንቅስቃሴያቸዉና ከጀርባ ስለሚደረግላቸዉ ዳጎስ ያለ ድጋፍ (ምንጭ) ለይተዉ እያወቁ ነዉ። አሽቃባጭ የሆነዉ “ሪፖርተር” ጋዜጣም አንድ ሁለቴ ባወጣዉ ወረርሽኙ ዋናዉ “አስኳል” የት ቦታ እንዳለ በደፈናዉ ገልጿል።ከባሕላችን ያፈነገጡ ርካሽ ተግባራት በሕብረተሰባችን እንዲስፋፋ እየተደረገ መሆኑን የጠቆመዉ ጋዜጣዉ፤ አክሎም በሸራተን ሆቴል በመሸጉ ቱጃሮች በሚለገስ ከፍ ያለ ገንዘብ አማካይነት አደገኛዉ እንቅስቃሴ እየተንሰራፋ መሄዱን አጋልጧል። በሸራተን ዋናዉ ርካሽ ተግባር እንደሚፈጸም አያይዞ የጠቀሰዉ ጋዜጣ ጉዳዩን በደፈናዉ “ርካሽ የወሲብ ተግባር” ከማለት ዉጭ የግብረሰዶማዊነት መሆኑን ያለመግለጽ ለትዝብት ያደረገዉ አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኖ ነበር። እንደተገለጸዉ አስኳሉ ሸራተን የሆነዉ ወረርሺኝ በይፋ ከከፈታቸዉ የምሽት መዝናኛ መካከል የሚከተሉት ይገኛሉ። በአካል ጭምር ተገኝቼ ያረጋገጥኳቸዉ ቦሌ ቴሌ መድሃኒያለም ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ የሚገኘዉ “ሸገር“ ሕንፃ ሦስተኛ ፎቅ በሰፊ አዳራሽ (ሁለት ቦታ ተከፍሎ) ተከፈተዉ “ሻምፒዮን” ወይም በሌላኛዉ መጠሪያዉ “ዲቫይን” የተባለዉ የግብረ ሰዶማዉያን መዝናኛ በዋናነት ይገኛል። የባሩ ባለቤት በአሜሪካ ለረጂም ዓመት የኖረና በ1999ዓ.ም. እንግሊዝ-ለንደን ከተማ ከወንድ ጓደኛዉ ጋር “ጋብቻ” መስርቶ እንደተመለሰ ተረጋግጧል፡፤ ለጋዜጠኛነት ስራየ እንዲሁም ባሕላዊ ወረርሽኝ ለመከላከል ባለብኝ ግዴታ በመነሳት ወደተጠቀሰዉ ባር በእኩለ ሌሊት አመራሁ። የገጠመኝ ሁኔታ ከሰማሁት የበለጠ ነበር! በምሽት ደብዛዛ የብርሃን ጨረር የተሞላዉ ይህ ባር እንደነገሩ ሁለት ቦታ ተከፍሏል። እንደ ዊስኪና ሌሎች የአልኮሆል መጠጦች በዉድ ዋጋ የሚቸበቸቡበትና በዲጄ በሚለቀቁ የዉጭ ዘፈኖች ታጅበዉ የሚደነስበት ሲሆን፤ በሌላኛዉ ክፍል ደግሞ እጅግ ከደበዘዙና ብዙም የብርሃን ጨረር ከማይፈነጥቁ አምፑሎች በመታገዝ ግብረሰዶማዉያን የሚፈጽሙት የሚያቅለሸልሽ አፀያፊ ተግባር የሚፈፅሙበት ነዉ። ከሰኞ በቀር በሁሉም የሳምንት ቀናቶች ይህ ወራዳ ተግባር ይፈጸማል።በጣም የሚገርመዉ ፈረንጆች ወንድ ለወንድ ፤ሴት ለሴት ሆነዉ (ካፕል- ካፕል መሆኑ ነዉ) እየተላላሱ በሚያጠይፍ አኳሗን መመልከቴ ነበር። “ይሕች ያልታደለች፤ተቆርቋሪ መንግሥት ያጣች አገር… ድሕነት አሳሯን የሚያሳያት አልበቃ ብሎ፤ የነርሱ ቆሻሻ ባሕል ማራገፊያ መሆኗ ስታይ ያቃጥላል” አልኩ በወቅቱ ለራሴ ። የእኔን ሃሳብና ቁጭት የሚጋራ ድፍን ሙሉ አገር እንደሆነ አልጠራጠርም። በሌላ ቀን ጥቆማ ወደ ደረሰኝ መዝናኛ ስፍራ አመራሁ። ቦታዉ ከቦሌ ትምህርት ቤት ሽቅብ እንደተጓዘ “ቦሌ ኬክ ቤት”ን ያገኛሉ፡ ከኬክ ቤቱ በግምት 200 ሜትር ርቀት ላይ ከመንገዱ ግራና ቀኝ በመደዳ ከሚገኙ በርካታ ባር ቤቶች ከቀን በኩል ቅድሚያ የሚያገኙት “ላጌቶ” የተባለዉን የግብረሰዶማዉያን መናኻርያ ባር ነዉ። በሚታይ ጉልሕ ጽሑፍ የመዝናኛዉ ታፔላ ተሰቅሏል። በግራዉንዱ አልፈዉ ባሩ ወደ ሚገኝበት አንደኛ ፎቅ ይደርሳሉ። ከእነሱ በቀር ሌላ ተጨማሪ ሌላ ሕንጻ የለም። የባሩ ባለቤት አስመራ የቆየና “ላጌቶ” የሚል ተመሳሳይ መጠሪያ የሰጠዉ መዝናኛ ከፍቶ እስከ ዘጠናዎቹ አመታት አጋማሽ ሲሰራ እንደቆየ ከራሱና ከኤርትራዉያን ጭምር ማረጋገጥ ተችሏል። አስመራ ያለዉ መንግስት በግብረሰዶም ዙርያ ጠንካራ አቋም ያለዉ ሲሆን በዚህ ርካሽ ተግባር ተሰማርቶ የተገኘ ማንኛዉም ግለሰብ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ በሞት እንዲቀጣ ይደረጋል። ይህ ግለሰብ ሻዕቢያ ሲደርስበት አምልጦ በየመን በኩል አዲስ አበባ ይገባል። አስመራም አዲስ አበባም የሚታወቅበት መጠሪያ ስሙ “ላጌቶ” በባሩ ስያሜ ነዉ። ይህ ማለት ( Gay-ጌይ) የሚለዉን ለማመላከት ነዉ የሚሉ አሉ። በየዕለቱ በዚህ ባር አካባቢ ፖሊሶች አይጠፉም። ግለሰቡ ኤርትራዊነቱን ሸሽጎ “ሻዕቢያ ሊገድለኝ ሲል ያመለጥኩ የትግራይ ተወላጅ ነኝ” እያለ ከማደናገሩ በተጨማሪ ሴት “ጥንዶች” ወይም ‘ሌዝቢያን’ በብዛት አይጠፉም። ለመግለጽ የሚቀፉ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የሚታየዉ ኤርትራዊዉ እና ግብረሰዶማዉያኑ አባላቶቹ በሚለቀቀዉ ዘፈን (ዘፈኖቹም የነጭ እና የሻዕቢያ ናቸዉ)ጣልቃም ከ አየአቅጣጫዉ”አሞሬ”…አሞሬ” የሚሉት ቃላት ይወረዉራሉ። ትርጉሙን ስጠይቅ “ፍቅረኛየ” ማለት እንደሆነና የ“Gay”ዮቹ ቋንቋ እንደሆነ ተረዳሁ። ሽንት ቤት ሳመራ ባየሁት ነገር አስታወኩ! ወዴት ያመራን ይሆን? Published on www.Ethiopiansemay.blogspot.com questions email editor at getachre@aol.com