Friday, August 27, 2010

ሶማሊያ ኢትዮጵያን ስትወረር የወያኔ መሪዎች “ዜግነታቸው” ሶማሌ አስብለው ነበር

ይድረስ ለጎጠኛው መምህር (አማርኛ) እና ሓይካማ (ትግርኛ) መጽሐፌን ለመግዛት ዕድሉን ያላገኛሁ ካላችሁ በሚከተለው አድራሻ ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ Telephone (408) 561 4836 begin_of_the_skype_highlighting (408) 561 4836 end_of_the_skype_highlighting Getachew Reda P.O.Box 2219 San Jose, CA 95109 ሶማሊያ ኢትዮጵያን ስትወረር የወያኔ መሪዎች “ዜግነታቸው” ሶማሌ አስብለው ነበር ጌታቸው ረዳ www.ethiopiansemay.blogspot.com (ከየወያኔ ገበና ማሕደር ዓምድ)

ይህ ዝግጅት ሁሌም በኢትዮጵያን ሰማይ የህዋ ሰሌዳ እየተዘጋጀ የሚቀርብ የወያነ ትግራይ ነፃ አውጭ ድርጅት የፈፀማቸው ግፎች እና ብሔራዊ ወንጀሎች የሚቀርብበት ዓምድ ነው።በዛሬው ዓምድ የማቀርብላችሁ ካነበብኳቸው የትግርኛ መጽሐፍቶች አንዱ በቅርቡ ለአንባቢ የተሰራጨ ጋህዲ ቁጥር 3 የትግርኛው ዕትም ካገኘሁት እጅግ አስገራሚ የሆነ የተለያዩ የወያነ ትግራይ ገበናዎች የሚዘረዝር ወያኔን ከመሠረቱት 11 ሰዎች አንዱ በሆነው አቶ አስገደ ገብረስላሴ ወ/ሚካኤል ያጋለጠው አዲስ የወያኔ ማሕደር ይሆናል።

አስገደ ገ/ስላሴ በጋህዲ ቁጥር 3 መጽሐፉ ላይ በገጽ 144 ምዕራፍ 12 « የሶማሊ መንግሥት ለወያኔ ሠራዊት ዕድገትና ጥንካሬ ያደረገው ዕርዳታዊ አስተዋጽኦ » በሚል ርዕስ የሚከተለውን ሰነድ ባጭሩ ጨምቄ ከትግርኛ ወደ አማርኛ ተርጉሜ ለአማርኛ አንባቢዎች አቅርቤዋለሁ። የዘመን አቆጣጠሮቹ እንደምታውቁት በቋንቋችን ስጽፍ ማሳሰቢያው በፈረንጅ አቆጣጠር ካላልኩበት በቀር በኢትዮጵያ አቆጣጠር መሆኑን ሁሌም ተገንዘብልኝ። በዙህ ሰነድ ውስጥ በትርጉም ስሕተቶች ለሚመጡ ጉዳዮች ሃላፊነቱ የኔው እንጂ የደራሲው አይደሉም።

« ከሶማሌ መንግሥት ጋር ግንኙነት የተጀመረው ወያኔ ሱዳን ውስጥ ጽ/ቤቷን ከከፈተችበት ከ1969 መጨረሻ ጀምሮ ነው። የግንኝነቱ አመሰራረት የተጀመረው ሱዳን ውስጥ ከነበረው የሶማሊያ ኤምባሲ ሲሆን፤ጥቂት ሳይቆይ ከሶማሊ መንግሥት ጋር በቀጥታ ግንኙነቱን መሠረተ። ግንኙነቱ እንደተመሠረተ ማንኛውም የውጭ አገር ግንኙነትና እንቅስቃሴ፤የወያኔ አባሎች ወደ ውጭ አገር ለሥራ ጉዳይ ሲንቀሳቀሱ በሶማሌ ዜግነትና የሶማሌዎች ስም የያዘ ቪዛ እና ፓስፖርት በመያዝ ነበር የሚንቀሳቀሱት።

የሶማሌ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር በሃይለኛ ጦርነት ተወጥሮ እያለ፤መሳርያ እንደሚያስፈልገውና በዛ ሃይለኛ ውግያ የመሳርያ ቁጠባ ማድረግ እንዳለበትና በችግር እንደተወጠረ እያወቀም ቢሆን ለህወሓት ያደረገው ዕርዳታ ወደር ለውም። በጥቂቱ የሚተለው ነው።

1- ሁሉም የወያኔ መሪዎችም ሆኑ የሕዝብ ግንኙነት ጉዳይ ለማስፋትና ለማጠናከር የሚላኩ ከፍተኛ የወያኔ ካድሬዎች ወደ አውሮጳ፤አሜሪካና ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ሲንቀሳቀሱ ሰላማዊ የዜግነት ዓለም ዓቀፍ ሕጋዊ የመንቀሳቀሻ ሰነድ መያዝ ስለሚኖርባቸው፤ ወደ 50% የሚጠጉ የወያኔ የማዐከላዊ ኮሚቴ አባሎች እና ካድሬዎች የሶማሌ ባለሥልጣኖች / ቪ አይ ቪ/ ቪዛ ተሰጥቶአቸው ስማቸውን ቀይረው በመላው ዓለም እንዲንቀሳቀሱበት የሚያስችላቸው በመፍቀድ በውጭው ዓለም ያለ ምንም ችግር ትልእኮአቸው እንዲያከናውኑ ከፍተኛ አስዋጽኦ አድርጓል።

2- ከ15 በላይ የሚሆኑ የወያኔ ታጋዮች ምግባቸው፤መኝታቸው፤ወጪአቸውና አስፈላጊው በጀት ሁሉ የሶማሌ መንግሥት በመሸፈን አለ የተባለ የከባድ ብረት ማሣሪያዎች፤መድፎች፤ታንኮች፤ሞርታሮች፤ዓየር መቃወሚያ -ሚሳይሎች ታንከኛ፤እና ሁሉም ዓይነት ያካተተ ፀረ ታንክ ፤ፀረ ተሽከርካሪ፤ፀረ ሰው ፈንጂ ለረዢም ጊዜ አሰልጥለውልናል(ገጽ 144) ለምሳሌ እነ ጀላኒ ወዲ ፈረጅ፤ እነ ገብረ ሓፂን፤ብርሃነ አርብጂ የመሳሰሉት ታጋዮች ለአንድ ዓመት ሙሉ 12 ሰዎች ሶማሌ ሄደው ማንኛውንም ዓይነት ከባድ መሳርያ ሰልጥነው ለድርጅቱ ከባድ መሳርያ ስልጠና ወሳኝ ሚና የተጫወተው ይኸኛው ክፍል ነበር(ገጽ18)።

3- እነኚህ ሶማሌ ውስጥ የሰለጠኑ ታጋዮች ወደ ትግራይ ሜዳ በመመለስ የወያኔ ታጋዮችን በሰለጠኑበት የዘመናዊ ከባድ መሳርያዎች ስልጠና አሰልጥነው በርከት ያሉ የከባድ ብረት መሳሪያ ተኳሽ በታሊዮን ቡድን ማነፅ ተጀመረ።

4- የሶማሌ መንግሥት ህወሓት ከውጭ አገር አምባሳደሮች ጋር እንደ አንድ ራሱን የቻለ አገር ተደርጎ እውቅና እንዲያገኝ በማለት ሶማሊያ ዋና ከተማ መቃዲሾ ከተማ ውስጥ እንደማንኛቸውም አገሮች ወያነ ትግራይም ኤምባሲ ጽ/ቤት ተከፍቶለት ከተቀሩት የመላ ዓለም አገሮች አምባሳደሮች ጋር ጎን ለጎን በማስቀመጥ እንዲታወቅ አጽተዋጽኦ አድርጓል።

5- ህወሓት የሶማሌ መንግሥት የሰጠውን ሰፊ የመንቀሳቀስ ዕድል ተጠቅሞ አስፋሃ ሓጎስ የሚባል የወያኔ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ከመላው ዓለም ጋር ለመገናኘት የሚያስችለው የራዲዩ ግንኙነት መስመር በመዘርጋት ከነረዳቶቹ ጋር ሶማሌ ውስጥ አስፈላጊው ግንኙነት ማድረግ ቻለ።

6- ያ ሶማሊያ ውስጥ አምባሲ ተከፍቶለት የነበረው የወያነ ትግራይ አምባሳደር ጽ/ቤቱን እንደ የዘመቻ መምሪያ (ቤዝ/መዋፈሪ) በመጠቀም የደርግን የዕለት ተለት ሁኔታ ዘገባ በማግኘት ብዙ ሥራዎችን እንዲከናወኑ ትልቅ ዕርዳታ አድርገውልናል።

7- ህወሓት ከቻይና መሣርያዎችን በመግዛትም ሆነ የግዢውን ገንዘብ ማስተላለፍ በኩል ሶማሌዎች ዕርዳታ አድርገዋል። መሣሪያዎቹ ከቻይና ተጭነው ወደ ሶማሌ ካቀኑ በሗላ ጭነቱን ተመልሰው የሶማሊ መኮንኖችና ሠራዊቶች እስከ ፖርትሱዳን በመሸኘት ያስረክቡን ነበር። ያ በጥቁር ገበያ /ኮንትሮባንድ ግዢ የተገኘው መሣርያ ግን በጋህዲ ቁጥር 1 እንደገለጽኩት ሻዕቢያዎች ሆን ብለው በሌብነት ዘርፈውታል። “ሆኖም ተጀምሮ ደርግ እስከ ተደመሰሰበት ድረስ በሕግም በኮንትሮባንድም በሶማሌ ስም ከውጭ ዓለም መሳርያ እየተገዛ በኤርትራ በኩል ይተላለፍልን ነበር። ሶማሌ ያደረገልን ዕርዳታ መተኪያ የሌለው ነበር።(ገጽ 16)

8- ለምሳሌ በሶማሌ ቪዛ ዜግነታቸው “ሶማሊያዊ” ተብለው በሶማሊ ቪዛ ሲጠቀሙ ከነበሩት

1- ግደይ ዘርአፅዮን

2- ስብሓት ነጋ

3- አስፋሃ ሓጎስ

4- አደም

5- ካሕሳይ በርሀ/ዶክተር ምስግና

6- ገብረመድህን መሐመድ ያሲን

7- ሥዩም መስፍን

8- መለስ ዜናዊ

9- ወረደ ገሠሠ

10- ጃማይካ ኪዳነ

11- ፀጋይ ጦማለው እና ብዙ በርከት ያሉ ታጋዮችና መሪዎች ነበሩ።

ባጭሩ የሶማሌ መንግሥት የሕዝብ አደረጃጀት ሥራዎች እንዲሁም በመላው ዓለም ውስጥ ያለ ምንም ችግር እንደፈለጉ እንዲንቀሳቀሱ አስፈላጊውን የይለፍ እና የቪዛ የፓስፖርት እና የዜግነት መታወቂያዎች በመፍቀድ፤ከመላው ዓለም መሳሪያዎች እርዳታ እንዲያገኙ እና በግዢ ሚመጡትንም በማሃል አስፈጻሚ በመሆን ለድርጅታችን የሰራዊት ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረገልን የሶማሌ መንግሥት ምስጋና ይገባዋል።

አንዳንድ ሰዎች ኢትዮጵያ በሶማሌ የስያድ ባሬ መንግሥት ስትወረር ህወሓት ወረራው ሕጋዊ ነው በማለት ይደግፍ ነበር። ስለሆነም ህወሓት የኢትዩጵያ ሉኣላዊነት ቅድሚያ አላስቀመጠም (ጉዳዩ አልነበረም) የሚሉ አሉ። ይህ እንዲህ ሆኖ እያለ፤ የወያኔ መሪዎች በተለያዩ መድረኮች “ሶማሌ በ1969/70 ዓ.ም ኢትዩጵያን ስትወር ደርግ ፀረ ሶማሊ ወረራ ሲመክት የደርግን አቋም እንደግፍ ነበር፤ የሶማሊ ወረራ በመኮነን ፀረ ሶማሌ እንንቀሳቀስ ነበር”፡በማለት አቶ መለስ ዜናዊ፤አቶ ሥዩም መስፍን፤ አቶ አባይ ፀሐየ እና አቶ ስብሓት ነጋ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አድምጬአቸዋለሁ፤ በተለያዩ መድረኮችም ተመሳሳይ መግለጫ ሲሰጡ ነበር። እዚህ ላይ በዚህ ጉዳይ እኔ ምስክርነቴን ለማስቀመጥ ከሆነ ህወሓት በትግሉ ወቅት- ትግሉ ተጀምሮ እስኪያልቅ የሶማሌ መንግሥት ያካሄደው ፀረ ኢትዮጵያ የወረራ ጦርነት ኢትዮጵያን የሚደግፍ የተቃውሞ ድጋፍ በጽሑፍም ሆነ በቃል የተጻፉ ወይንም ሲነገሩ በስብሰባም ሆነ በኮንፈረንስም፤በጉባኤዎቻችንና ስብሰባዎቻችን አንድም ቀን ሰምቼ ፤አይቼ ወይንም አንብቤ አላውቅም።ቢሆንም ጉዳዩ ለታሪክ ተመራማሪዎች እንዲተቹበት እየተወኩኝ ታሪኩ ግን እኔ እየመሰከርኩ ያለሁት ይህ ከላይ የገለጽኩት ሃቅ ነው ትክክለኛው ታሪክ።

ለመሆኑ በማን አገር እየኖረ ነው ሶማሌን የኮነነው? የስያድ ባሬ መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ ወረራ ሲፈጽም ህወሓት መቃዲሾ ውስጥ ጽ/ቤት ከፍቶ ሲሰራ ነበር። የት ሆኖ ነው? እንዴት አድርጎ ነው ወረራውን ሲቃወም የነበረው? እንባቢዎች ትዝብቱን ለናንተው ልተው።”

በማለት አስገደ ገ/ስላሴ በጋህዲ ቁጥር 3 (ትግርኛ) መጽሐፉ ላይ በገጽ 144 ምዕራፍ 12 « የሶማሊ መንግሥት ለወያኔ ሠራዊት ዕድገትና ጥንካሬ ያደረገው አስተዋጽኦ » በሚል ርዕስ እነ መለስ ዜናዊ እነ ሥዩም መስፍን፤ስብሓት ነጋ… ኢትዮጵያዊነታቸውን ጥለው ሶማሊዎች ነን በማለት የሶማሊ ዜግነት በመያዝ ከፀረ ኢትዮጵያ ሃይሎች ጋር ሲተሻሹ እና ወረራውን ‘ግፋ በለው እያሉ ያገራቸውን ወታደራዊ የስለላ ምስጢር እየጠለፉ ለጠላት ሲያቀብሉና ሲለዋወጡ የነበሩበትን ሰነድ አጋልጧል። « ጀሮ እያደረ የማይሰማው የለም » የሚባለው ለካ ልክ ነው። መለስ ዜናዊ በእኛ በኢትዮጵያዊያኖች የሚታወቀው « አበበ » ነው፤ ሶማሌ ከሆነ በሗላ « የእስልምና » ስሙ ማን ይበል ይሆን ? ንስሃ አባቱ አባ ጳውሎስ ከስልምና ሲመለስ « ማተብ » አስረውለት ይሆን ? ቱፍ ቱፍ ! ከመዓቱ ይሰውረን ! ሁሉም ቻይ የኢትዮጵያ ሰማይ ማረኝ ጌታየ ! ደጋፊዎቹ እባካችሁ የለመዳችሁት ኩርፍያችሁ በኔ ላይ አትከምሩ « ትልቁን መስቀል ሲሳለም አይቼው ነው ሕገ ክርስትያኑን በመጣሱ ነው ሱባኤ ገብቶ ማተብ አስረውለት ይሆን ብየ የምጠይቃችሁ። ሁሉም ቻይ አምላክ ስንቱን ጉድ ችለህ ይችን ዓለም ታስተዳድራለህ ? ፍርድህ ምነው ዘገየ ?

አሁንም በድጋሜ እንዳትረሱ፦

አዲሱን መጽሐፌን ሓይካማ (ትግርኛ) እና « ይድረስ ለጎጠኛው መምህር » (አማርኛ) ለማንበብ ዕድሉን ያልገጠማችሁ በ408 -561-4836 መልክታችሁን ብትተው የትና እንዴት እንደምታገኙት ማወቅ ትችላላችሁ። getachre@aol.com

Wednesday, August 18, 2010

ጮክ ብለህ የማይለቀስበት ሰሚ ያጣ ኡኡታ!

ይድረስ ለጎጠኛው መምህር (አማርኛ) እና ሓይካማ (ትግርኛ) መጽሐፌን ለመግዛት ዕድሉን ያላገኛሁ ካላችሁ በሚከተለው አድራሻ ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ Telephone (408) 561 4836 Getachew Reda P.O.Box 2219 San Jose, CA 95109

ጮክ ብለህ የማይለቀስበት ሰሚ ያጣ ኡኡታ!

(ከኤርትራዊያን ማሕደር) www.ethiopiansemay.blogspot.com

ይህ ጉድ በኤርትራዊያን ድረ ገጽ ኢትዮጵያንና የመለስ ተቃዋሚዎችን ሥም በማጥፋት ሌት ተቀን ከሚባዝኑ ባተሌ ድረ-ገጾች አንዱ ከሆነው ኣዝማሪኖ ብሎ ራሱን የሰየመ የመለስ ዜናዊ እምባ አፍሳሽ ድረገጽ አንድ ኤርትራዊ ባወጣው እሮሮ የተገኘ ዜና ነበር። አርዕስቱ “ናይ ሞት መንፈስ ኣብ ዙርያ ኤርትራዊያን” (የሞት መንፈስ በኤርትራዊያን ዙርያ) በሚል ርዕስ የሚከተለውን እሮሮው በትግርኛ እንዲህ ብሎ ነበር። “ዓው ኢልካ ዘይብከዮ ሰማዒ ዘይብሉ ኣውያት መንእሰያት ኤርትራ አብ ሃገሮም ብሰላም ንኸይነብሩ እሾክ እግሪ ኮይኑ እንዳወግኤ ለይትን ቀትርን ከም ቁርዲድ ደሞም እንዳመጸየ ብምስምስ ሃገራዊ አገልግሎት መወዳታ ዘይብሉ ናይ በረኻ ናብራ እንዳጮቆነ ዓፊኑ ካብ ዝሓዞም ስርዓት ንምህዳም ክብሉ ፈቆዶ ስደትን፣ ቀለብ ዓሳ ባሕርን ግዳይ ሕጻ በረኻን ኮይኖም የርከቡ ኣለው” - (( ሁኔታችን) ጮክ ብለህ የማይለቀስበት ሰሚ ያጣ ኡኡታ (ነው)። ኤርትራዊያን ወጣቶች አገራቸው ውስጥ በሰላም እንዳይኖሩ የእግር ሾኽ ሆኖባቸው፤ሌት ተቀን እንደ መዥገር ደማቸው እየመጠጠ በአገራዊ አገልግሎት ሁካታ ማለቂያ የሌለው የበረሃ ህይወት (እንዲያሳልፉ) ጨቁኖ፥ አፍኖ ከያዛቸው ሥርዓት ለመሸሽ ሲሉ ወደ ስደት ህይወት በማቅናት በየበረኻው የሃይለኛ በረሃ ሐሩርና በሚሻገሩባቸው ወንዞችና ባሕሮችም የዓሳ ነባሪ ቀለብ በመሆን ለመከራ ተጋልጠዋል።) ይላል።

በቅርቡ የኤርትራዊያን ሰቆቃ በግብፅ በረሃ እና በእስራኤል ድምበር አካባቢ ያጋጠማቸው የጥይት እሩምታ ያነበባችሁት ይመስለኛል። ካሁን በፊት ደግሞ ማለትም አምና La Repubblica የተባለው የኢታሊ ጋዜጣ ማለትም በAugust 2009 /gommone sbarca a lampedusa a bordo salvagenti maltesi/) በሚል ርዕስ ባወጣው ዘገባ 57 ኤርትራዊያን ስደተኞች የያዘች ጃልባ በማልታ በኩል አድርጋ ወደ ኢጣሊያ ወደብ እንደገባች ዘገባው ያስረዳል። እንዲሁም 78 ኤርትራዊያን ከሊቭያ በመነሳት 23 ቀናት ባሕር ውስጥ ያላንዳች ዕርዳታ ከቀዘፉ በሗላ ከነዚህ ውስጥ 73 ሲሞቱ 5 ሰዎች በጣሊያን የባሕር ጠባቂዎች ዕርዳታ ህይወታቸው ሊተርፍ ችሏል ይህ ሁሉ ሲሆን ማልታ አልቀበልም ስትል ወደ ጣሊያን ሲሻገሩሊቪያም አስሮ ሲገርፋቸውና ወደ ኢሳያስ ሊመለሳቸው ሲሞክር ወደ ጣሊያን አገር በመሸሽ ለዚህ ችግር ሞትና አደጋ ተዳርጓል። ወደ ኢትዮጵያ እና ወደ ሱዳን የሚጎርፈውን ወደ ጎን ትተን፤ ከኤርትራ ለመሸሽ ሲሞክሩ በጥይት እንደ ጅግራ የሚገደሉትን ሳንቆጥር ማለት ነው። ይህ ሁሉ ጉድ ለምን መጣ? ይህ ሁሉ መከራና ስደት ዛሬስ አማራ ነው እየፈፀመባቸው ያለው? ኦኖጎች እና ኦጋዴኖች ወይንም ሲዳማዎች ወይም የወያነ ትግራይ የግንጠላ አቀንቃኞችና የአልባኒያ ቅጅ ፈላስፋዎች ከኤርትራ ግንጠላ ወዲህ ምን እየተማሩ ይሆን? ይማራሉ ብየ አልገምትም! ምክንያቱ የዚህ ግንጠላ አቀንቃኞች “ሊሂቃኑ በምቾት ውጭ አገር የሚኖሩ ወይንም ጭፍን ተከታዮቻቸው ውጭ አገር በስደት በምቾት ልጆቻቸውን እያሰተማሩ የሳተላይት ዲሽ ሲነማ እና “በግደለው ቁረጠው አባርረው፤እረደው፤ንቀለው የስድብ ስንኝ” የጠባብ ጎሰኞች ሙዚቃ የዳንስ ውዝዋዜ እና ትርኢት ሕሊናቸው የሚያድሱ (የሚመርዙ) ስለሆኑ፤ አገር ውስጥ ኤርትራም ሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ለተለያዩ ችግሮች የተጋለጡ ዜጎች በየቀኑ የሚጋፈጡት መከራ አይሰማቸውምና ግንጠላውን ዛሬም እየሰበኩ ከንቱ ውዳሴ ሲያሰሙ እየሰማናቸው ነው። ዋሾ መሪዎቻቸው ግን ወደ ምትባለዋ ምድር ሎሌያቸውን እንዲዋጉ ሊልኩ ካልሆነ በስተቀር ሃሳዊ መሲሃኖቹ ግን ራሳቸው አዘጋጅተው ለውግያ አይሄዱም። በመለስ ዜናዊ የሚደገፉት የኤርትራ ተቃዋሚዎችም ሆኑ ኦሮሚያ የሚባል የሕልም አገር እንመሰርታለን የሚሉትም ሁሉ ምስኪኑን ገበሬና እረኛውን ለጦርነት መማገድ እንጂ ራሳቸው በሚያወሩት “በረሃ” ውስጥ ከናቲራ ለብሰው ድንጋይ ላይ ተኝተው ለቁር ለሃሩር ለጥማትና ለ እርዛት አይዳርጉም። ሁሉም ወደ ኬኒያ ወደ ኢትዮጵያ ወደ ሱዳን ወደ አስመራ…የማያልቅ ስብሰባ/ኮነፈረንስ ያካሂዱና ተመልሰው ወደ መከረኛው መጠለያቸው አሜሪካና አውሮጳ ይመለሳል። ምን የሚሉዋቸው ነፃ አውጪ መሪዎች እንደሆኑ ለራሴ ይገርመኛል! ይህ ሁሉ ምስኪን ሕዝብ ለሞት ሊዳረግ የቻለበት ምክንያት በውሸት የተካኑ የግንጠላ አቀንቃኞችና ከዚህ የተያያዘ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፀሙ፤ያዘዙ፤የተካፈሉ የግንጣላ መሪዎች በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቶች ተከሰው ለፍረድ ሲቆሙ ብቻ ነው። ይህ እስካልሆነ ጊዜ ድረስ፤የግንጠላና ጎሰኛ መሪዎች ሕዝብን ለስደት እና ለጦርነት መዳረጋቸው ይቀጥላል። በዚህ ኢትዮጵያውያን የሕግ ባለሞያዎች ብዙ ጊዜ ተማጽኜ አልሰሙኝም። ዶክዩመንቶች የተዘጋጁ ናቸው፤ የሚፈለገው የናንተ የሕግ ባለሞያዎች አንድነትና ፈቃደኛነትን ብቻ ይጠይቃል። አንዳንድ የሕግ ምሁራን ነን ብለው በየ ኢንተርኔቱ ሺህ ገጽ ስለ ሰብአዊ መብት ጉዳይ እና ስለ ዲሞክራሲ እየሞነጫጨሩ በተግባር እንዲተረጉሙት ሲጠየቁ ግን “አይገኙም”! ለምን? ጉዳዩ ግልፅ ነው፡ “ንኡስ ከበርቴው ለራሱ ክበብ” እንጂ ስለ ለገበሬው፤ስለ ወታደሩ ህይውት በጠባቦች ካራ አንገቱ ይታረድ አይታረድ ስሜት አይሰጠውም። ከራሱ ከንኡስ ከበርቴው መደብ በአምባ ገነኖች ወታደር ሲዋከብ ወይም ሲታሰር ግን ጩኸታቸው ዓለምን ያደነቁራል። ለምን? መደብ ከሉጓም ይስባል! የሊሂቁ ስነ ባሕሪና ማንነት አፈጣጠሩ ሊሽረው ብዙ ጊዜ ይፈጃል። ለመሆኑ ኤርትራዊያኖቹ ከዛ ሁላ ጭፈራ እና ትምክህት ስካሩ በንኖ የህ የሞት ተክሊል በራሳቸው ላይ ሲደፋ ዛሬም ስለ ግንጠላውና ስለ ፀረ ኢትዮጵያ እይታቸው ጸንተው የቆዩበት ለምን ይሆን? ከዛ በባሰ ደግሞ ዛሬም ሕዝቧን (ኢትዮጵያን) አክ እንትፍ ብለው ድንጋይ ወርውረውባት ላይመለሱባት ምለው ጥለው ተገዝተው የረገምዋት አገር ተመልሰው ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ለመጠለያ ሲመለሱባት ምንን ያሳያል? በጣም የሚገርመው ደግሞ ኤርትራዊያን ሊሂቃን (ተቃዋሚዎች ነን የሚሉ ጀብሃዎች…) የፋሺስቱ እና የጎሰኛው አገር አጥፊው የመለስ ዜናዊን እርምጃ እና ስነመንግሥት እያወደሱ የወያነ ትግራይን ፋሺስታዊ ጎሰኛ ቡድን ለሚቃወሙ የአንድነት ሃይሎች (ኢትዮጵያዊያን ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችን) ሲዘልፉ በጽሁፋቸው እና በራዲዮን ቃለ መጠይቃቸው ሳዳምጣቸውና ሳነባቸው “እንኚህ ባተሌዎች” የመለስ ዜናዊ አሽከርነታቸው መቸ ያቆሙ ይሆን? እላለሁ። በጣም የሚገረመኝ ደግሞ ኤርተራዊያን ተቃዋሚዎች መለስን ሲያወድሱ “የመለስ ማንንት ተሎ የረሱት ይመስለኛል” ከምሽጋቸው አባርሮ ወደ ስዳን ጠርጎ ያባረራቸውን ሽንፈታቸው ረስተው ፤ጓዶቻቸውን እያነቀ ለኢሳያስ ነብሰገዳዖች ያስረከባቸውን ጨካኝ ባሕሪውን ረስተው፤ ሱዳን መንቀሳቀሻ ምድር ከለከለን በሚል ሰበብ ዛሬም የጎሰኛውን “የዘንድሮ ዲሞክራት አርበኛቸው” የመለስ ዜናዊን የእግር ጫማው ሲልሱት ይታያሉ። ለመሆኑ እነኚህ ሰነፎች እና ትምክህተኞች በመለስ ስር ተጠልለው ኤርትራን ዲሞክራሲ እናመጣለን ሲሉ ልብ ላለው ተመለካች ይገርማል? መለስ ዜናዊ እውን ኢሳያስ ለመጣል ፍላጎት ቢኖሮው እስከዛሬ ድረስ ለምን ቆየ? የጀብሃ ሽምቅ ተዋጊ ኢሳያስን በሃይል ሊጥል ነው ተብሎ ይታሰባል? መለስ ኢሳያስ ሊያጠፋ ፍላጎት ቢኖሮው ጀብሃዎቹን ሰብስቦ ከሗላ ወይም ከፊት አስከትሎ በሰራዊቱ ደምስሶ ለሞላ ኤርትራ ተቃዋሚ ሁሉ ሰብስቦ እወዳታለሁ/ /እሳዋላታለሁ/ተሰውየላታለሁ ለሚላት ኤርትራው ቢያስረክብ የትኛው መንግሥት ነው በመለስ ዜናዊ የሚጮኸው? (ያውም መለስ የሃያላኑ ሎሌ እና ኢሳያስ በዱርየነት ጠባዩ በሃያላኑ ማዕቀብ የተጣለበት!) ተቃዋሚዎቹ ኢትዮጵያ እየሄዱ አለን ለማት ካልሆነ በቀር መለስ ዜናዊ እስከ መጨረሻ ኢሳያስን ይጠላል ብለው ማሰባቸው ሞኞች ናቸው።

የኤርትራው አላያንስ (የተቃዋሚዎቹ ቃል ኪዳን/ ስብስብ) ( በተለያ ስም የሚጠራው የድሮው ጀብሃ) ይህ ስበስብ ሁሉም ባይሆኑ አብዛኛዎቹ የትምክህት/የጎሰኛነት/የስልጣን ጉጉት/እና የገንዘብ ስግነብግብነት/ኮራብሽን እንዲሁም የውሸት ባህሪ የተጠናወታቸው ስለሆኑ አዲስ አበባ ድረስ ኮንፈረንስ አካሂደው “የዲሞክራሲ መሠረት“ ጥለዋል ብሎ ማለት የነዚህ ሰዎች ባህርና የፖለቲካ ማሕደር በቅጡ ያለመረዳት ከመሆኑ አልፎ ተጠልለውበት ያሉት አገር መሪ የፖለቲካ ቅጥ አለመረዳትም ይመስለኛል።

ወደ ስደተኞቹ ልመልሳችሁ-

ከጻሃፊው ርዕስ “ጮክ ብለህ የማይለቀስበት ሰሚ ያጣ ኡኡታ! የሚለውን እሮሮ ስትመለከቱት፤ ኤርትራውያን ሊሸሽጉን ከማይችሉበት የመከራ ጠርዝ በዓለም ፊት መጋለጣቸው እንጂ እንደ እነሱ የትምክህት ባህሪ ቢሆን ኖሮ “ጮክ ብለው እያለቀሱም ነበር/ዛሬም አላለቀስንም” እያሉ ነው። ለዚህ ነው “ጮክ ብለህ የማይነገር ጉድ” እያሉን ያሉት። ጮክ ብለው ሊጮኹ ያልፈለጉበት ምክንያት የታወቀ ነው። ትምክህት፤ውሸት፤ጭካኔ፤ግፍ፤ዘረኝነት መጨረሻ ራስን የሚጎዳ መሆኑ እየደረሰባቸው ባለው ማቆሚያ የሌለው መከራ እያዩት ነው። መከራና ሐፍረት ያልቀመሱ እንገነጠላለን የሚሉ የኢትዮጵያችን ተገንጣዮች ከዚህ ጉድ እና ሐፍረት ምን ተምረው ይሆን? መልሱ ለናንተ ልተው። ከመዓቱ ይሰውረን ማለት ብቻ ነው! እንደምታውቁትና ባይናችሁ (ከባድሜ ጦርነት ጀምሮ) ቅንደተመለከታችሁት የኢትዮጵያ ጠላቶች የጊዜ ጉዳይ እንጂ እንደዘወትሩ በአምላክዋ ጥበብ ትምክህተኞችና ዘረኞች የገዛ ራሳቸው መርዝና ሴራ ሳይወዱ ተመልሰው በራሳቸው እጅ ይጋቱታተል!ጮክ ብለህ የማይለቀስበት ሰሚ ያጣ ኡኡታ! ትላለችሁ፤ትምክህታችሁ፤ውሸታችሁ፤ዘረኝነታችሁ አጉል ዕብጠታችሁ ጀሮኣችሁ ደፍኖ አላሰማም አላችሁ እንጂ ሰሚ መቼ አጣችሁ? www.ethiopiansemay.blogspot.com getachre@aol.com