Friday, August 18, 2017

የምሥራች! በጋሻው ደሳለኝ እግዚአብሔር ሆነ! ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

                        ከአዘጋጁ
ዛሬ በዳግማዊ ጉዱ ካሳ የተላከልንን የተለጠፈው ጉዳይ ባለፈው ጊዜ በመጠኑ አንስቼው የነበረ ዛሬ ሰፋ ባለ ሁኔታ ቀርቧል። ይህንን የሚያሳየን፤ደጋግሜ እንደገለጽኩት ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት የባህልና የሃይማኖት ወረራ ውስጥ እንደተያዘች ነው። በሚቀጥለው አዲሱ መጽሐፌ በመጠኑ ይህንን ወረራ ማን እንዳስገባውና በማንስ ትብብር ሕዝባችን ለኢሉሙናቲ እምነትና ለመሳሰሉ የባሕል ወረርሽን እንደተባበረ ይገልጽል። ወያነ ትግራይ በጌቶቹ እየታዘዘ የኢትዮጵያን ገበሬ በኢሉሙናቲ እምነት እንዴት እንደበከለው ከነማስረጃው እንወያያለን። እስከዛው  ግን ይህንን ያንብቡ፡ መልካም ንባብ።


  


የምሥራች! በጋሻው ደሳለኝ እግዚአብሔር ሆነ!
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልለልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልለልልልለልልልልልልልልልለልልልለልልልልልል…. ኢትዮጵያዊ እግዚአብሔርን እንደማግኘት የሚያስደስት የለም!
                                    ምንጭ - https://www.youtube.com/watch?v=RdvtqjaR3Po
            ይህን ማስወንጨፊያ በሚገባ ያዳምጡ፤ በጋሻውንም ይተዋወቁ - ከዚህ በኋላ የበጋሻው ስም ‹አዲሱ እግዚአብሔር› እንጂ ሌላ አይሆንም፡፡ ለዝርዝሩ ጊዜ ካለኝ ወደፊት እመለስበታለሁ፡፡ አጅሬ በጋሻው ኦርቶዶክስን እንደሸንኮራ መጠጠና ወደ ፕሮቴስታነቱ ጎራ ዞረ፡፡ ያም ተመጦ ባዶ መቅረቱን ባያውቅ ነው፡፡ የጨነረው እርጉዝ ያገባል(ስትወልድበት ገደል ለመግባት) - የባሰበትም እመጫት - እንደበጋሻው ነፍስ የተጨነቀ ፍጡር የማያደርገው የለም፡፡ ግን ማጠንጠኛው “ሲያልቅ አያምር” የሚለው ብሂል ቢሆን ያስኬዳል፤ እንደሰውም፣ እንደሃይማኖትም፣ እንደሥርዓትም፣ እንደዓለምም… ሁሉን ነገር ሲያጤኑት ነቢዩ “ሁሉም ነገር ከንቱ የከንቱ ከንቱ” እንዳለው ነው፡፡ የሆድ ነገር፣ የብልጭልጯ ዓለም ጉዳይ፣ የዝና ስካርና የአንድ ወቅት ገናና ስም መደብዘዝ የማያስከትሉት ሥነ ልቦናዊ ኪሣራ የለም፡፡ ብቻ ባጭሩ ሰዎች ያሳዝኑኛል፤ በዋናነት እንደትልቅ የሕይወት መርህ መያዝ ያለብን ነገር የራሳችንን ሕይወትና ፍልስፍና ከሌሎች ሰዎች ምንነትና ማንነት ጋር ማቆራኘት የሌለብን መሆኑን ነው፡፡ እንዲያ ካደረግን እነሱ ሲወድቁ አብረን እንወድቃለን፤ ሲሰበሩ እንሰበራለን፤ ሲበላሹና ሲግማሙ እንበላሻለን እንግማማለንም፤ ሲሞቱም እንሞት ይሆናል - ቢያንስ በመንፈስና በኅሊናና በሥነ ልቦና [ወምበዴዎቹን ጳጳሣትና ካህናት ተከትለህ የክርስቶስን መንግሥት እወርሳለሁ ብለህ ካመንህ ዕቅጩን ልንገርህ አሁኑኑ ፈተናውን ወድቀሃል፡፡  የአሁኑ ፕሮቴስታንት - ‹ጴንጤ‹ ወይም ‹መናፍቅ› ላለማለት መጨነቄን አስቡልኝ - በጋሻው “አንድን ሰው ከየሱስ ጋር እጅ ለእጅ ካያያዝኩት በኋላ ከኔ ምን ይፈልጋል? ይህ ሰው ስልክ ቢደውልልኝ እንኳን አላነሳም፡፡  ሰውንና ፈጣሪን የማገናኘትና የማያያዝ ዋናውን ሥራየን ጨርሻለሁና…” ሲል ወደ አምላክ ‹አንድ ብቸኛ መንገድነቱን› ስለገለጠልህ በርሱ ብቻ ብታምን ነገ ይሄ ሰው ቢያሰልም ወይም ሺንቶይዝምንና ስፍር ቁጥር ወደሌላቸው -ኢዝሞች ተለውጦ እነቡድሃንና ዳላይላማን ቢቀበል - ይሄም አይቀርም - ትሰበራለህ፤ ገባህ የምልህ ወንድማለም? “እመለስታበለሁ” ባልኩት ነገር ላይ አሁን መናገሬ ምን ነክቶኝ ይሆን ግን? የወሬኛን ሰው ነገር አየህልኝ?]፡፡ …. ለማንኛውም የትንሹ በጋሻውን ዕብደታዊና ሰይጣናዊ ስንክሳር ትተነው ነገር እንዳጀማመሩ አያልቅምና ይህች አሮጊት ዓለማችን ሳያምራባት ወደ ፍጹም ቅጣት የጨዋታው ማጠናቀቂያ ደረጃ መግባቷን ልብ በልልኝ፡፡ ስንቱን አየን? ስንቱንስ ታዘብን? ያገሬ ባላገር እንዲህ ይላል፡-
ምነው አምና በሞትኩ እንዲያ እንዳማረብኝ፤
ሰው እንደበርበሬ ሳይለወጥብኝ፡፡
(ልብ በል፡- ማንም ተለወጠ አልተለወጠ ሁሉም ለራሱ እንጂ ስለማንምና ለማንም ሲል አይለወጥም፡፡)

ቀጣዮቹን አድራሻዎች ቢመለከቱ ደግሞ የዓለማችን ፍጻሜ ከሰሞኑ ምናልባትም ከዛሬ ማታ እንደማያልፍ ይረዳሉ፡፡ ለዚህ ነው ከፍ ሲል “ጊዜ ካለኝ” በሚል በመጨረሻው ምዕራፍ  የምንገኝ መሆናችንን በገደምዳሜ ልጠቁም የፈለግሁት፡፡
1.  https://www.youtube.com/watch?v=to4M3jClUcU (ሱራፌል የሚባል አጭበርባሪ ሐሳይ ነቢይ ሰይጣናዊ ትርዒት)
2. https://www.youtube.com/watch?v=XM5kf_jmf9M (አንድ ደቡቤ አጭበርባሪ ‹ነቢይ›- እንዲህ የኩታራ መጫወቻ እንሁን?)
3. https://www.youtube.com/watch?v=nV1Dpu2O1cQ (‹ነቢዩ› ታምራት ደምሴ በ‹ማዳን ሥራ‹ ላይ- የ‹ነቢያቱ› አበዛዝ!)
4. https://www.youtube.com/watch?v=Kq4eJVu5kW8 (የሴቴኒዝም አምልኮ በዓለም መሪዎች ፊት በግልጽ ሺካኄድ)
5. https://www.youtube.com/watch?v=w6tk9owvmas (ስለ ወቅቱ ‹የዓለም መሪ›ና ስለመለያ ታርጋው 666 …)
6. https://www.youtube.com/watch?v=iOlbrFKtOOQ&spfreload=10 (የዐውሬው የመገበያያ ገንዘብ)

        ከአሁን በኋላ ያሉት ጊዜያት በአብዛኛው የተዓምራት መገለጫዎች ይሆናሉ፡፡ የእነዚህ ተዓምራት ምንጭ ሁለት ናቸው፡፡ አንደኛው ብርሃናዊ ሲሆን ሁለተኛው ጽልመታዊ ነው፤ የአወንታዊና አሉታዊ ኃይሎች (Positive and Negative Energies)የዘመናት ፍልሚያ ዕልባት የሚያገኝበትና በዓይነቱ አዲስ የሆነ ወርቃማ ዘመን የሚብትበት ዋዜማ ላይ መድረሳችንን የሚጠቁሙ ብዙ ዓለም አቀፋዊ ክስተቶች ይታያሉ፡፡ የበጉ ጠቦትና የፍየሉ ሙክት መጋጠሚያ ዐውድማ ተለቅልቆ ካለቀ ብዙ ቆይቷል፡፡ ለሺዎች ዓመታትም አሸናፊው ጎልቶ ያልወጣባቸው መጠነኛ ግጭቶች ሲካሄዱበት ኖረዋል፡፡ የመጨረሻው አርማጌዴዎን ግን በቅርብ እንደሚከናወን ይጠበቃል፡፡ ከፍ ሲል ከተቀመጡትና በሺዎች ከሚቆጠሩ ሌሎች ተመሳሳይ ዶሴዎች የምንረዳው በዚህ አንቀጽ ውስጥ የተቀመጠውን መሪ ሃሳብ የምናልባታዊነት ደረጃ ከፍተኛነት ነው፡፡ የእምዬ ወለላዋ ልጅ ጌ.መ. ኢ. ክርስቶስ “ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም” ብሏላ! መልካም የዘመን ፍጻሜ ያድርግልን፡፡ ለነገሩ ከሁልጊዜ ፈስ የአንድ ቀን ቅዘን ሳይሻል አይቀርም፡፡ “ዘጠኝ ሞት መጣ” ቢሉት “አንዱን አስገባው” አለ አሉ አንዱ - “አንዱን መርጠህ አስገባው “እንኳን አላለም፤ ለሞት ደግሞ ምን ምርጫ አለው፡፡ አሃ፣ አለው እንጂ! በወያኔ መሞትና በሰው ልጅ መገደል አንድ ነው ሊባል ነው? በወያኔ መገደልን ለጠላትም አይስጥ! እውነቴን ነው የምለው ሞት የፈረድኩበት ጠላት ቢኖር በወያኔ ከሚገደል ምሕረት ባደርግለት ይሻለኛል፡፡ ሰይጣን ራሱ ከወያኔ ስንትና ስንት የማሰቃያ ሥልቶችን እንደተማረ ከራሱ ከሰይጣን በስተቀር ማንም አያውቅም፡፡ ሕወሓታዊ ‹ቶርቸር› ሲዖል ውስጥም አይታወቅም፡፡ ከወያኔ አንጻር ሰይጣን ገር/የዋህ ፍጡር ነው፡፡ አድራሻየ ቢያስፈልግዎ - ma74085@gmail.com

No comments: